Get Mystery Box with random crypto!

ታደሰ ደምሴ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia2123 — ታደሰ ደምሴ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia2123 — ታደሰ ደምሴ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopia2123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ሥነ_ግጥም
ግጥሞችን በዩቱብ ለመከታተል👇👇👇
https://youtube.com/@maryam2116

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-03 20:17:33 «ስለእነፀዲ ስለእውነት ምን መፃፍ እንዳለበት እንጃ!! ፀዲን መፅሃፍ መደብር ነው ያገኘኋት። እውነተኛ ሀቀኛ ግን የምትፈልገውን ጠንቅቃ የምታውቅ ብልህ ነበረች።በዛ ላይ ታነባለች። ለተወሰነ ጊዜ አብረን ካሳለፍን በኋላ ተጋባን። በጊዜ ብዛት የምትቀይረኝ ይመስላት ስለነበር ብዙ ታገሰችኝ። በተለይ ለልጅ የነበራት ፍቅር ግን በእኔ የምትቀይረው ዓይነት አልነበረም እና መለያየት መረጠች። አሁንም ቢሆን ጓደኛሞች ነን። አብረንም ሳለን ጓደኝነታችን ያመዝን ነበር። ከዚህ የተለየ ይሄ ነው የሚባል የተለየ ዓመታት አልነበረም። ሰብሊ ትለያለች በግልፅ ከስምንት ዓመት በኋላ ስለምትካፈለው ንብረት ብላ እንደምታገባኝ ነግራኝ ነው የተጋባነው። ቀጥተኛነቷን እወደዋለሁ። ጭንቅላቷ ያስባል። በባህል ወግ ሀይማኖት ተፅዕኖ ያልሳሳ ራሷን የሆነ ማንነት ነው ያላት። አልጋ ላይ ጎበዝ ናት! እውነት ለማውራት ለማቴሪያል ያላት ጥማት ትንሽ ከመጭነቁ ውጪ የማትሰለች ዓይነት ነበረች። እየቆየች ከእኔጋር ፍቅር እንደያዛት ነገረችኝ። ምላሹን እንደማታገኝ ስታውቅ ሂሳብ ሰራች። በዛ ላይ ዓለምን እየዞሩ ማየት ህልሟ ነበር። እኔ ደግሞ በተቃራኒው መብላት እና መጠጣት እንኳን እቤቴ የሚያስደስተኝ ሰው ነበርኩ። ሰለቸኋት! እንደሷ የመዞር አባዜ ካለበት አንድ ሀብታም ጋር ተጣብሳ ፈታችኝ።» ትንሽ እንደማሰብ ብሎ

«ስለማዕረግ እስከአሁንም ምንም መረጃ የለኝም። እውነት ለማውራት ማወቅም አልፈልግም። እንጀራ እናቴም ብትሆን ከዘመናት በኋላ ቢሮዬ አፈላልጋኝ እስከመጣችበት ቀን ድረስ የማውቀው ነገር አልነበረም። ይቅርታ ልትጠይቀኝ ነበር የመጣችው (በፌዝ ሳቅ አለ) አንተ ላይ ላደረስኩት በደል እግዜያብሄር ቀጥቶኛል። ልጄ እንኳን ይሙት ይኑር አላውቅም! አለችኝ»

«እና ምን አልካት? ይቅር ብዬሻለሁ አላልካትምኣ?» ያልኩት አስቤው አልነበረም። ከት ብሎ ሳቀብኝ
« የምታምኚው አምላክ ይቅር በሉ ይል የለ? አየሽ ቅድም ያልኩሽን? የምናውቀውን ሁሉ አንኖርም እናወራዋለን እንጂ እኔን ለበደለችኝ በደል አንቺ ስላመመሽ ይቅር መባል እንደሌለባት አሰብሽ።» አለኝ ሳቁን እየቀጠለ
«እግዜር ራሱ ይቅር የሚላት አይመስለኝም። ይልቅ ንገረኝ።»
«አላልኳትም። በተቃራኒው ውስጤን በጥሩ እምነት ሞልቼዋለሁ ብዬ ያመንኩትን የተጠራጠርኩት የዛን ቀን ነው። ያቺ ስትራመድ ሞገሷ መንገዱን የሚቀድላት የምትመስል ሴትዮ የእርሷ ያልሆነ ሰውነት እና አለባበስ አጅቧት ቢሮዬ ሳያት የማላውቀው ጭካኔ ነው የተሰማኝ። ዘበኞች ጠርቼ እንዲያስወጡልኝ ሳደርግ እያለቀሰች እንኳን ልቤ ምንም ርህራሄ አልተሰማውም። ለቀናት ስላየኋት ብቻ ስሜቴ ተረበሸ። ያለችበት ሁኔታ እንዳለችው ስቃይ ከሆነ ነፍሴ ደስታን መቃረም ስለሻተች እንዲያጣሩልኝ አደረግኩ። የማይሆን ባል አግብታ ቤቷን እና ንብሯቷን አሽጧት እንደእናቴ ሰካራም ሆና ከንቱ ህይወት እንደምትኖር ሰማሁ። ከዛ በኋላ ያየኋት ባለፈው እቤቴ ስትመጣ ነው። አደጋ እንደደረሰብኝ ስታውቅ ጮቤ እንደረገጠች አልጠራጠርም። ወይም ሽባ ስሆን የሚራራ ልብ ይኖረኝ ከሆነ ልታረጋግጥ ይሆናል። አላውቅም! ማወቅም አልፈልግም! ሳያት ሲኦል ነው ትዝ የሚለኝ!» አለኝ እየዘገነነው።

የሆነ ነገር ትዝ እንዳለው ሰው ብንን ብሎ። « የሆነ ቀን ቁጭ ብዬ ቴሌቭዥን ሳይ ሉሲን አየኋት። (ሳቅ ብሎ) ተዋናይ ሆና! በቲቪ ባየኋት በወራት ውስጥ ታዋቂ ሾው ላይ ኢንተርቪው ስትሰጥ ያልሆነ ነገር ተናግራ ህዝበ ኢትዮጵያ በስድብ ሲቀባበላት ከረመ። ባጋጣሚ ወሬውን ሰምቼ ፕሮፋይሎቿን ሳጣራ እያለቀሰች ህዝቡን ይቅርታ የጠየቀችበት ቪዲዮ አየሁ። የኛ ህዝብ የሚገመት ስድቡን እና ዘለፋውን ጨመረላት። ላገኛት ፈለግኩ ምናልባት ልጅ ስለነበረች ወይም አሁን አወዳደቋ ተሰምቶኝ፤ እድል ሰጥቻት ለምን ያንን እንዳደረገች መስማት ፈለግኩ። አገኘኋት! ያለችኝን አመንኩ። እሷ የእናቴ እና የእናቷ መጠቀሚያ ብቻ ነበረች። በሰዓቱ አባቷ ታሞ ብዙ ብር ያስፈልጋቸው ነበር። ያን እኔም አውቅ ነበር። አባቷን ለማዳን የሚጠበቅባት ያቺን ድራማ መስራት እንደነበር እና የቀረውን ተንኮል እና ማስረጃ እነርሱ እንደሚጨርሱት አሳመኗት። ያን በማድረጓ ለተወሰነ ዓመትም ቢሆን ለአባቷ እድሜ ቀጥላለታለች። የሚገርመው <አንተን ጎድቼ ባይሆን አባቴን ያተረፍኩት እመርጥ ነበር። ምንም አማራጭ በሌለበት ግን አባቴን በመምረጤ አልተፀፀትኩም! ለደረሰብህ ነገር ግን ይቅርታ!> ነበር ያለችኝ። (ፈገግ አባባሉ ስለሆነች የሚወዳት ልጅ የሚያወራ እንጂ መቀመቅ ስላስወረወረችው ልጅ የሚያወራ አይመስልም ነበር።)»

«ልገምት በህይወቷ ውስጥ የሆነ መልካም ነገር አድርገሃል?» አልኩት ከፈገግታው እየገመትኩ
«በጣም ዲፕረስድ ሆና ነበር። ከሀገር ወጥታ የምትማርበትን መንገድ አመቻችቼላት እንግሊዝ ነው ያለችው።» አለኝ
«ግራ የሆንክ ሰው ነህኮ!» አልኩት
«አውቃለሁ!! አትወጂውም ግን አንድ ሀሳብ አለኝ! ምዕራፍ አምስትን እኔ ልፃፈው! አንቺ ከፃፍሽው አስቢው በየመሃሉ የመልስ ምት ልትሰጪኝ ነው። ከፈለግሽ እኔ ልፃፈውና እያነበብሽ ማውራት እንችላለን!! ከዛ ደግሞ ስላንቺ ላንቺው መተረክ ደስ አይልም። ነፃነቴን አጊንቼ እራሴ ልፃፈው እና አንብቢው።» ልደርስበት የጓጓሁበትን ምዕራፍ ለመፃፍ ስለተከለከልኩ ከፋኝ ግን ደግሞ ነፃነት ያለውን አመንኩለት እና ቅር እያለኝም ቢሆን ተስማማሁ። ኮንፒውተሬን ዘግቼ ዝም ተባብለን ፍራሹ ላይ ጋደም እንዳልን ከንፋሱ ጋር ማውራት ያዝንተ
154 viewsBetslot markos, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:12:02 ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት ….. እኔ የቀጠልኩት
(ክፍል ሀያ ……….)

«ትናንትህ ላይ በበደሉህ ሰዎች ነው ዓለምን በሙሉ እየዳኘህ ያለኸውኮ! በዙሪያህ ያሉ ሰዎች በሙሉ እንደእነሱ ናቸው ማለት አይደለም! በተቃራኒው የሆኑ ሰዎች አሉ። አንተ ያደረግከው ለማንም ምንም እድል አለመስጠትን ነው።» ከምሳ በኋላ ፀሃይ ቡና አፍልታ ሳሎን ቡናችንን እየጠጣን ነው ስላለፉት ውሳኔዎቹ የጀመርነውን የሀሳብ ልውውጥ የቀጠልነው።

«ካለፈው ውድቀትሽ ወይም ስህተትሽ መማር ማለት ታዲያ ምንድነው? ትናንቴን አልደግምም ማለት አይደል? ያለፈውን ስህተትሽን አለመድገም አይደል? ያለፈው ስህተቴ አለልክ ሰዎችን ማመኔ ፣ ያለገደብ ራሴን እስኪያሳጣኝ ከሰው ጋር መቆራኘቴ አይደል? ያንን ነው ያስወገድኩት!! የሰዎችን ስሜት ለውጥ፣ ክፋት ወይም ቅንነት ልትቆጣጠሪ አትችዪም። ልትቆጣጠሪ የምትችዪው የራስሽን ስሜት እና ራስሽን ብቻ ነው። ሰዎች ለምን እንደእኔ አልተሰማቸውም ማለት አትችዪም። በጠበቅሻቸው ልክ ሳይገኙልሽ ሲቀሩ እንዴት ማለት አትችዪም! ምክንያቱም እንዳንቺ ጥበቃ ሳይሆን እንደራሳቸው ስሜት እና እውቀት ነው ህይወታቸውን የሚመሩት። እነሱን መቀየር አትችዪም! አንቺ ስለእነሱ ያለሽን መጠበቅ እና ቅርበት ግን መወሰን ትችያለሽ!! ከማንኛውም የሰው ፍጡር ምንም ባለመጠበቅ ውስጥ እና ባለመተሳሰር ውስጥ ራሴን አትርፊያለሁ።»

«በፍፁም ከማንም ምንም አልጠብቅም ወይም በምንም ማንንም አልደገፍም አልያም ከማንም ጋር በስሜት አልቆራኝም ማለት አትችልም። ያንተም ህይወት ከዛ እጅግ የራቀ ነው። ለምሳሌ ከልጆችህ ጋር ያለህን ቁርኝት እየው! ለእነርሱ የምትሆነውን መሆን ለማንምና ለምንም ስትሆን አይቼህ አላውቅም! ሌላ ምሳሌ እንጥቀስ ቢያንስ በትንሹ ከሰራተኞችህ ጥንቅቅ ያለ ስራ ትጠብቃለህ! አንተ ባትኖር እነርሱ እንደማይኖሩት ሁላ እነርሱ ባይኖሩም ያንተ ቢዝነስ የለም!»

«የሆነ ጊዜ ነግሬሻለሁ መሰለኝ። በህይወት ውስጥ ለደስተኛነት ከመኖር ትርጉም ያለው ህይወት መኖር እንደመረጥኩ። ከዛ የጨለማ ውድቀት በኋላ ስነሳ ባለፈው አንቺ እንዳልሽው ደስተኛ ህይወት ለመኖር ዳከርኩ። እኔ ባለፍኩበት ዓይነት መንገድ ላለፈ ሰው ደስታ ከፍርሃት ጋር የተለወሰ ነው። እዛ የዝቅታ ወለል ላይ ደርሰሽ ካላየሽው ምን እንደምል ብዙም ላይገባሽ ይችላል። የሆኑ የሆኑ ጠርዞች አሉ ፍራሃትሽ የሚፈጥረውን ሀሳብሽን እና እውነታውን መለየት የሚያስቸግርሽ ጠርዝ። እሱ ጠርዝ ላይ መቆም አለብሽ ትግል አይጠቅምሽም። ምክንያቱም ያቺን ጠርዝ ካለፍሽ አለቀ። አዲሱን አዲስ መስራት ስጀምር ማን መሆን እንደምፈልግ እና ምን ዓይነት ህይወት መምራት እንዳለብኝ የራሴን የህይወት መመሪያና መርህ መቅረፅ ነበረብኝ። የማንንም ህይወት መኮረጅ አያዋጣኝም ነበር ምክንያቱም ማንም እኔ ያለፍኩበትን መንገድ አላለፈም። ለውጡ ይሄ ነው ያለማንም እርዳታ ሲሆን ራስሽን የሰራሽው ምርጫ አለሽ ምንና ማን መሆን እንደምትፈልጊ። እናም ደስታን ውስጤ ስፈልገው ከፍርሃቴ ጋር የተለወሰ ነበር እና በምትኩ የምኖርለት እና ትርጉም የሚሰጠኝ ዓላማ ላይ ራሴን ቢዚ ማድረግን ተማርኩ። ስለዚህ ልጆቼን እና ስራን እንደ ዓላማ ነው የምወስዳቸው።»

«በዚህ መጠን ትኩረት እና ጊዜ ለምትሰጠው ዓላማ ታዲያ ምንም ዓይነት የስሜት ቁርኝት የለኝም ማለት ትችላለህ?»

«ራሴን አያሳጣኝ እንጂ ትኩረቴን የማሳርፍበት ዓይነት ቁርኝት አይጎረብጠኝም። ጥያቄው የሚመጣው እኔን ጥያቄ ውስጥ ካስገባ ነው። ከራሴ እና ከምንም ወይም ከማንም መምረጥ ካለብኝ ራሴን ነው የምመርጠው። እውነቱንስ እናውራ ከተባለ ማንስ ራሱን አይደል የሚመርጠው?»

«እንዴ በፍፁም ራስህን የምትሰጥለት ሰው አለ። ኤጭ በምን ላስረዳህ ፍቅርን ታጣጥልብኛለህ እንጂ (ይሁን ቀጥዪ ዓይነት በእጁ እና በጭንቅላቱ ንቅናቄ ምልክት አሳየኝ።) እሺ! አይደለም ፍላጎትህንና ስሜትህን ነፍስህን ብትሰጠው worth የሚያደርግ የፍቅር ልክ አለ» ስለው ከት ብሎ ሳቀ

«መቼም ፍቅር እስከመቃብርን ወይም ሮምዮ እና ጁሌትን አትጠቅሺልኝም! ለስሜት ትስስር ብለሽ ሞትን ከመረጥሽ ቂል ነሽ ነው የምልሽ!! እኔና አንቺ እውነቱን አይደል የምናወራው? እስከሞት ልወድ የምችለው ራሴን ብቻ ነው!!» ብሎኝ ዊልቸሩን አንቀሳቀሰ። ስሜቱ ጥሩ ስላልነበር ለሁለት ቀን መጻፋችንን አቁመን ነበር።

«ለምን ዛሬ ቦታ አንቀይርም? እዚሁ እንፃፍ ወይም ውጪ!» አልኩት
«ውጪ አሪፍ!» አለኝ። ለፀሃይ ሳሩ ላይ ፍራሽ እንድታነጥፍ ነግሬያት ኮምፒውተሬን ላመጣ ወደ ላይብረሪ ሄድኩ። ፍራሹ የተነጠፈበት ዛፍ ስር የጥላው ቅዝቃዜ እና የቅጠሉ ቀዝቃዛ አየር እያጫወተን እሱ ትራስ ደራርቦ ተጋድሞ እኔ ቁጭ ብዬ መፃፍ ቀጠልን።

«ምዕራፍ አምስት!» ብሎ ሊቀጥል ሲል ሳላውቀው ጮህኩ።
«እንዴ? አራትን በአንድ ገፅ ልታልፈው አትችልም! ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉኮ! ከዛ ሁሉ ድቅድቅ ጨለማ በኃላ አዲስን በቃ ሰራሁት ብለህ አንባቢን ልታሳምን አትችልም። ኸረ ደግሞ ፀዲን እና ሰብለን እዚህ ምዕራፍ ውስጥ ልናነባቸው አይገባም? ከቤተሰብህ ጋር እና ከማዕረግ ጋር የነበረህ ታሪክስ እንደዛው በእንጥልጥል ይዘጋል? »
«ኸረ ቆይ እሺ (ከት ብሎ እየሳቀ) የት ሄድኩብሽ አለሁ አይደል?» ብሎ ቀጠለ።

« ለተወሰነ ጊዜ የመረጥኩት መንገድ ራሴን በስራ ቢዚ ማድረግ ነበር። ጎን ለጎን ሙያዊ ድጋፍ ያስፈልገኝ ስለነበር ሳይካትሪስት ጋር ክትትል ማድረግ ነበረብኝ። በትክክል የሚጠቅመኝን ህክምና የሚያደርግልኝ ሳይካትሪስት ማግኘት እጅግ ከባዱ ነበር። አንዳንዶቹ ዝም ብሎ መስማት ይመስላቸዋል መሰለኝ ሙያው ማስታወሻ እና እስክሪብቶ ይዘው ያስለፈልፉኛል። አንዳንዶቹ የሚሰጡሽ ምክር ደግሞ ራሳቸው ምክር እንደሚያስፈልጋቸው ያሳያል። የብዙ ሳይካትሪስት ቢሮ እና ፊት ከጎበኘሁ በኋላ በትክክል ሙያውን የሚያውቅ ፣ ለእኔ የሚያስፈልገኝ ህክምና የቱ እንደሆነ የገባው ዶክተር አገኘሁ። ከጊዜ ወደጊዜ ለውጡን የምገነዘበው ዓይነት ነበር። ከህክምናው ጎን ለጎን ራሴን በማንበብ ጠመድኩ። ንባብ ስልሽ እገሌ የሚባለው ደራሲ እንዲህ ብሎ ፅፏል ወይም እንትን መፅሃፍ ላይ ያለው ገፀባህሪ ምናምን እያሉ ጥቅስ ለማጣቀስ የሚረዳ ማንበብ ሳይሆን ልኖረው የምችለው እና ከራሴ ጋር የማዋህደው እውቀት ፍለጋ ነበር የማነበው። ለምሳሌ ሰዎች ያነባሉ። አንድን ርዕስ ነጥለን ብንወስድ ስለይቅርታ እልፍ ጥቅስ ይጠቅሱልሻል። የማይኖሩትን ህይወት ሊመክሩሽ ይችላሉ። ነገር ግን በህይወታቸው ለመጎዳት ምክንያት የሆናቸውን ሰውጋ ይቅርታ ማድረግ ዳገት ይሆንባቸዋል። ያውቁታል እንጂ እውቀታቸው የእነርሱ አካል አይደለም ወይም አይኖሩትም። ከእውቀቴ ከስሜቴ ከህክምናዬ እና ካለፈው ልምዴ ጨምቄ የመኖሪያ መተዳደሪያዬን ፃፍኩ። በየቀኑ ያን ለመኖር ራሴን አሰለጠንኩ። አዲሱ አዲስ የዚህ ውጤት ነው። አለቀ!!» ብሎ ትንፋሽ ሰበሰበ። የምፅፈውን ገታ አድርጌ

«የተነበበ ሁሉ እኮ ግን አይኖርማ?»

«ያስማማናል። የትኛው እውቀት ብትኖሪው እንደሚበጅሽ የምታውቂው አንቺ ብቻ ነሽ!! የምርጫ ጉዳይ ነው።» አለኝና እንደገና ቀጠለ
204 viewsBetslot markos, 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 15:22:38 ኑ በተስፋ እንኑር!
(ታደሰ ደምሴ)

እንዲያ ...በደቦ እየጠጣን ከጠላቤት አለም
በሀሳዊ ትምቢት ሰክረን ያለምነው ህልም

እንዲያ በደመነፍስ...
ከስጋ አምሮት እቶን ወድቀን እየጋየን
ያልኖርነውን ህይወት...
በረከሰ ምላስ ፅድቅ እየወለዠን
የቆጠርነው ሱባይ ተሳልቆ ከከዳን

ኑ! በተስፋ እንደር...
ኑ! በተስፋ እንኑር...

እንበል "መኸር ደርሷል ቀን ይወጣል" ዳግም
ምን ሳይሰምር ቢቀር ተስፋ አይነፈግም!!!

#join
t.me/ethiopia2123
t.me/ethiopia2123
t.me/ethiopia2123
238 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 11:55:09 #ምክንያቱም_ኢትዮጵያዊ_ነን
(ናትናኤል ጌቱ)
.....
አይንጋላችሁ ተብለን ፥ ጸሀያችንን ቢያጠልቁት
ፋኖሳችንን ባህር ውስጥ ፥ እያሰጠሙ ቢያርቁት
ለጨለማው ቀልድ ነግረን ፥ አስቀነው ፈገግ ይላል
የጽልመቱ የሳቅ ፍንጥቅ ፥ ከጻይ ይልቅ ያማልላል
ጨለማውን አናነጋም ፥ ብርሀን ነው እንላለን
ለጨለመች ህይወታችን ፥ ከጽልመት ጧፍ እንሰራለን
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነን !
..........
ለአርባ ቀናት ዝናብ ቢወርድ ፥ የሰማይ መስኮት ተከፍቶ
ምድሪቷን ውሀ ቢሞላት ፥ ሀያል ፈጣሪ ተቆጥቶ
ልክ እንደ ኖህ አንለፋም ፥ ያቺን ቀን ግን እናልፋለን
አንድም መርከብ ሳንሰራ ፥ አሳ ሁነን እንተርፋለን
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነን !!!!
..................
ዘጠኝ ሞት ሲደረደር ፥ ከቤታችን መግቢያ በራፍ
አንዱን ግባ ብለን ከፍተን ፥ ከህይወታችን አንድ ምእራፍ
የሞትን ስም እንጽፋለን!
የጻፍነውን መጻፍ ደግሞ ፥ ለጠላቶች እንልካለን
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነን !
.........
በአሽሙር በትር ለሚነካን ፥ በወግ ሆዱን ለሚነፋ
ያላየውን ለሚያወራ ፥ ሀሰተኛ ቱሪ_ናፋ
ልክ እንደ እባብ ተጠምጥሞ ፥ " ልቀፋችሁ ኑ" ለሚለን
ጭንቅላቱን አንመታም !
በቅኔያችን ስውር በለቅ ፥ አይምሮውን እንነካለን
ምክንያቱም ኢትዮጲያዊ ነን
..........
ልጆቻችን አለት አይተው ፥ ተስፋ ቆርጠው ሲተክዙ
ጠላታቸው ሲበረታ ፥ ዶማቸውን እንደያዙ
" ድሮ ድንጋይ ዳቦ ነበር ፥
እያቦካን የምንሰራው ፥ የእናታችን የሊጥ ቅጂ
እኛ አክሱምን አልተከልንም ፥ ግዙፍ ሙልሙል ጋገርን እንጂ "
በምንለው ተረታችን ፥ የሰሙንን አሳምነን
ከአለት ጋር እያታገልን
የአለቶችን ጽኑ ብርታት ፥ በአንዲት ተረት እንጥላለን
ከዶማችን ብረት በላይ
ተረታችን ጠንካራ ነው ፥ ይሄን እውነት እናውቃለን
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነን
.....
ራብ ሊጥለን ሲመጣ ፥ ሲሞክር ሊበታትነን
በሌማታችን ሳንኮራ ፥ እምነታችንን ቀጥለን
ከተልባ በዳቦ ይልቅ ፥ ተልባ ማሻ አቦን ተማምነን
ስንጠግብ ባናድር እንኳ ፥ ከሞት ሰይፍ እናመልጣለን
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነን!!
.........
በጉልበቱ የሚበልጠን ፥ የማንችለው በጦር አቅሙ
ልናፈሰው ያልተቻለን ፥ የወፈረ ትኩስ ደሙ
ቀብራችንን አመቻችቶ ፥ ከጉድጓድ ላይ እንደጣለን
አጋም ሁነን እየበቀልን ፥ ሰውነቱን እንወጋለን
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነን !
..............
ተደናግጠን አንወድቅም! ፥ ስጋት ደፍሮ አይገድለንም
ሩጫ ላይ አንደኛ ነን ፥ ፈሪዎች ግን አይደለንም
የደቀንነው መዋጊያ ጦር ፥ በጠላት ፊት ቢኮላሽም
የሚያስነውር ድርጊት እንጂ ፥ ሞትን ፈርተን አንሸሽም
በአፍሪካ ቀንድ ብንኖርም ፥ ቀንድ የለንም እንደ ሰይጣን
የነካንን ባላንጣ ግን ፥ አስበርግገን ስንቴ ቀጣን
ጥቁረታችን ምልክት ነው ፥ ከሩቅ አይቶ ለሚለየን
መልካችን ነው ባንዲራችን ፥ ልንቀይረው 'ማይቻለን
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነን !!

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
316 viewsHáŷmî, 08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 10:57:14 Watch "ሰቆቃወ ወለጋ! በአማራነቴ ተዋርጄ በኢትዮጵያዊነቴ የምመካበት ስብዕና የለኝም! " on YouTube


1.4K viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 07:01:56 ለማናቸው ላልቅስ

መጠለያ ሆነው በሌሊት ለቀሩት
ነገን ናፍቀው ሳለ በዛው ላሸለቡት
ህፃን ልጅን አዝላ ድንገት ለቀረችው
ለእናቴ ላልቅስ ደግ ለተባለችው
ወይስ ለአባቴ ለጀግናው ወቶ አደር
ጠላቶቹን ገሎ ለሚሰማው ክብር
ለወንድሜ ይሻላል ለኔ ውድ መካሪ
ሀገሩን ማይሰጠው አሳልፎ ለወራሪ
እህቴስ ማን አላት የተቀጨች ባ'ጭር
ከውስጧ ለወጣው ለእምዬ ፍቅር
ግራ ገባኝ እኮ ለማናቸው ላልቅስ
ማንንስ መርጬ እንባዬን ላፍስስ
ቡርቅ ቡርቅ ሲሎ ከሜዳ ላይ ወጥተው
ለህፃናት ይሆን ለተገኙት ሞተው?
ቤታቸውን ዘግተው ጥናት ላይ ለነበሩ
ለጓደኞቼ ላልቅስ አብረውኝ ለተማሩ
ወይስ ለታመሙ
ከሆስፒታል አልጋ ተደፍተው ለዋሉ
ከህመም መዳንን አጥብቀው ሲመኙ
በከባድ መሳሪያ አፈር ለለበሱ
ኧረ ወገን ከበደኝ ለይትኛው ላልቅስ
የትኛውን ትቼ ለማን እንባዬ ይፍሰስ?
ምግብ ለዘራልኝ ምስኪኑ ገበሬ
ዕውቀት ለመገበኝ ጎበዙ መምህሬ
ለሀገሬው ህዝብ በህይወትም ላለው
ለየትኛው ላንባ ግራ ገባኝ ምነው?
ለቡድኑ ላልቅስ ለዚህ ከንቱ አውሬ
ንፁሀን ለሚገል ከጥንት እሰከ ዛሬ
በጅምላ ታጭቀው ለገቡ መቃብር
ልስጣቸው ይሁን እንባዬን በፍቅር
እኮ ለየትኛው ለማናቸው ላልቅስ
ማንንስ መርጬ ለማን እንባዬ ይፈሰስ
ለራሴ ላልቅስ በአለም ለቀረሁት
ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈፀም ላየሁት
ወይስ ለበላዩ አይቶ ዝም ላለው
መፍትሄ እያለ በሰው ደም ለከበረው
ለምድሪቷ ላልቅስ ለማትረባው አለም
በደም ተጨማልቃ ሁሌ ለምትል ዝም
ለፍትህ ይሁና እንዳላየ ለሚያልፍ
ለበዳዩ እንጂ ለተበዳይ የለው ትርፍ
ኧረ ወገን እባክህ አንዴ መላ በለኝ
ለማናቸው አልቅሼ ለማን ዝም ልሰኝ
ለሞቱት ለመንግስት ወይንስ ለራሴ
ለምድሪቷ ፍትህ ይህን ላየች ነፍሴ
ለጨካኙ ቡድን አልያ ለህፃናቱ
በህይወት ለቀሩት በዚህ አለም ከንቱ
ግራ ገባኝ እኮ ለማናቸው ላልቅስ
የቱንስ መርጬ ለማን እንባዬ ይፍሰስ???

ሰላም (Selito)

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
343 viewsHáŷmî, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:54:31 ጦቢያ...

የቁጣሽ ጅራፍ ይታጠፍ ~
የመቅሰፍትሽ ሰይፍ ይለፈን
በርጉም ሸኮልሽ ስንነደፍ ~
ስላንቺ ማፈሩ ይብቃን

ያ ያኮራሽው ውሽማሽ ~
ከኛላይ ገመዱ ይክተም
ልጆችሽ ቀና ይበሉ ~
ለመርዶ ያጫቸው ይውደም!

እምየ...
መራቆትና መዋረድ~
ሰለቸን በቃችሁ በይን
እዕሬቱንና ሀሞቱን ~
ከጠላን ትናግ ጋችልን
ጸሀይሽ ለእኛ ትገለጥ ~
ጠለ በረከትሽ ይጎብኘን
አሜን!!!

ታደሰ ደምሴ
#ሼርርር

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
347 viewsዴር 33, edited  17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 18:17:41 ሚዛን
""""""""

በሚያሳዝን ፊቱ ወደ እኔ አፍጦ ፣
አንድ ምስኪን መዛኝ መንገድ ዳር ተቀምጦ ፣
ይለኛል ተመዘን ፣
በስንቱ ልመዘን ፣
ሚዛን በበዛበት በዚች በጉድ ሀገር ፣
መመዘኑ ሳይሆን
ኪሎን ማወቁ ነው የሚያስፈራው ነገር ።

ወፈርኩኝ ቀነስኩኝ እያሉ መጨነቅ ፣
ለማይሞላ ኑሮ ሙሉ ቀን መሳቀቅ ፣
ሁሉን በመሰለው በገባው ለሚዳኝ ፣
ፍትህ እና ሚዛን አይደሉም ተጓዳኝ ፣
ሰው ራሱን ቢዳኝ ሰውን መንቀፍ ትቶ
መች ይባክን ነበር የእውነት ፍርድ አጥቶ ።

#በረከትዘውዱ

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
337 viewsHáŷmî, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 15:10:36
ጥበብን ለህዝብ ቁስል ዘይትነት በሚገባ የተጠቀመው በላይ በቀለ በተረኞች ከታፈነ ሶስት ቀናቶች አለፉ። ያለበትኳ እንደማይታወቅ ቤተሰቦቹ እየተናገሩ ነበር እባካችሁ የጥበብ ሰዎች ድምጽ ሁኑት!
#ሼርርር
@ethiopia2123
386 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 17:53:22 Watch "ሰቆቃወ ወለጋ! በአማራነቴ ተዋርጄ በኢትዮጵያዊነቴ የምመካበት ስብዕና የለኝም! " on YouTube


415 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ