Get Mystery Box with random crypto!

አንቺየ... (ታደሰ ደምሴ) እንዲያ... አንቺን ፍለጋ ስባክን~ ተሳልቀሽ ስትሰወሪኝ 'አይኖችሽ | ታደሰ ደምሴ

አንቺየ...
(ታደሰ ደምሴ)

እንዲያ...
አንቺን ፍለጋ ስባክን~ ተሳልቀሽ ስትሰወሪኝ
"አይኖችሽ እራቡኝ" ላልሁሽ~ገጽሽን ላላይ ስትነፍጊኝ

በንጹህ ልቤ በወደድሁ፣
በአንድያ አሳቤ ባፈቀርሁ፣

ካንቺ ከፍ አልልም ብየ~ ለመውደድ አጎብዳጅ ስሆን
አንቺኑ አግኝቸ ልባረክ~ ለፍቅርሽ ሳጣው እራሴን

ከጠማኝ ልሳን አፍልቀሽ ድንበር ተላልፈሽ ስትዘልፊኝ
በራቡኝ አይኖችሽ ግልምጫ የጎሪጥ ቢጤ ስትሾፊኝ

ፍላፃ ጦርሽን አውልቄ ከቀልቤ ልሆን ስቃጠር
ባስብሽ እርም እንዲሆነኝ ለአድባር ተስየ ሲሰምር

ዛሬ ላይ ዘመን ገልብጦሽ
ከትቢያ የፈረጅሽኝን የትናንት እኔን ቢያሰኝሽ

በተራሽ ፍለጋ ስትወጭ ላታይኝ ብደበቅብሽ
ሞገሴን ገዝፎ ብታይው ስለዚህ ለምን ገረመሽ
የዘራሽውን ገብስ እንጂ ያልዘራሽውን መች አጨድሽ

#ሼርርርር

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123