Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Neshida & Menzuma

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_neshida
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.99K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ #YouTube ቻናል 👇
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma
ወደ #Facebook Page 👇
https://www.facebook.com/Ethio-Neshida-Menzuma-348031129044029/
ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት(bot) ተጠቅሞ ያድርሱን✍️
👇
@ETHIO_NESHIDA_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-12-15 22:35:03 #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

የታመመ ሀኪሙን ይከጅላል። የተራበ ቀላቢውን ይሻል። የተጠማ የውሃ ጉድጓዱን ይምሳል። የጨለመው ኩራዙን ይለኩሳል። ያፈቀረ ተፈቃሪውን ያሳድዳል። እንዲህ ሆነና አንድ ዕለት ሰይዳችን ከመስጂዳቸው ጎራ ብለው ፀጉራቸውን ሊላጩ ተቀመጡ። ለዚህ የታደለ ሰው ፀጉራቸውን ሊቆርጥ ተሰየመ። ሶሀቦች ሁሉ ታደሙ። አፍጥጠው መጠባበቅ ጀመሩ። ለዘመናት ያልሙት የነበረ ይመስላል። ነብር ታዳኟን አሰፍስፋ የምትጠብቀውን ያህል እነርሱም የረሱልዬን ፀጉር ይጠባበቁ ጀመረ። ሁሉም ለራሱ ከጅሎታል። ሰይዲ ይህንን ጉጉታቸውን ያስተውላሉ። በእያንዳንዱ የፀጉር ዘለላቸው ላይ የተለያዬ ምስጢር አደረጉበት። ለእያንዳንዱ ሶሀባ ነሲቡን ከፈሉለት።

ፀጉር ቆራጩ ሲጨርስ ሰይዲዋ "በሶሀቦቼ መሀል አከፋፍለው" ሲሉ። አዘዙት። ሶሀባው ሁሉ መሻማት ጀመረ። አንድ ዘለላ ፣ ሁለት ዘለላ አንዳንዱ ከዚያም በላይ የደረሰው ነበረ። ከፊሉ ያሸተው ጀመረ። እኩሌታውም ይስመዋል። ሌላው እያየው ያነባል። በተወደደ እቃ ላይ አስቀምጠውታል። ይህንን ሁኔታ ከሩቅ ሆነው ሰይዱና አቡበክር ይመለከታሉ። ከነዚህ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ነገር ተመለከቱ። ቀልባቸውን ገዝቷቸውል። በእርግጥ የአሏህ ስራ እያስገረማቸው ነው። የነብዪ የፍቅር መግነጢሳዊ ሀይል እያደነጋገራቸው ነው። ከእነዚያ ፀጉሩን ከሚሻሙት ሶሀባዎች መሀል አንዱ ሱሀይል ቢን አምር ሆኖ ተመለከቱት። አንድ ፀጉር ሲደርሰው ወዲያውኑ ወደ ዓይኑ አስጠግቶት ተንሰቀሰቀ። ይህንን በተመለከቱ ጊዜ እጅግ አለቀሱ። ቀልባቸውን አንከላወሱ። ምላሳቸውን አላወሱ።

"ትላንት ላይ በሁደይቢያ ስምምነት የነብዩን መልእክተኝነት መቀበል ተስኖት ስማቸውን ከነ ማዕረጋቸው ለመፃፍ የተፀየፈው ሱሀይል ዛሬ ከሶሀቦቻቸው ጎራ ሆኖ በፍቅራቸው ይገረፋል።" አሉ። በእርግጥ መድሀኒቱን አግኝቶ ነው። ለዘመናት የታመመውን ህመም ያሻሩለትን ሀኪሙን አፍቅሮ ነው። ትላንት ሊዋጋቸው ያሰፈሰፈ ሰው ዛሬ ነፍሱን ሊሰጣቸው ተማርኮ ነው። የፍቅር ማዕበል ተማቶት ነው። ከዚህ የበለጠ የፍቅር ምች አላስተዋልንም። የለይላ እና መጅኑንን ታሪክ አልናቅንም ሆኖም እጅጉን የበለጠው አለ። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሰው ሰውን ሲያፈቅር ሶሀባዎች ነብዩን ሲወዱ አየን። በጆሮ የሰማነውን ታድመን ያየን ያህል ተማርከን በልባችን አመንን። አንድ እናክልና የበለጠ እንተዓጀብ!
ሰይዱና ኻሊድ ቢን ወሊድ በአንድ ዘመቻ ከጦር ቆባቸው ውስጥ ያስቀመጡት የሰይዲ ፀጉር ከቆባቸው ጋር ይጠፋባቸዋል። በተፋፋመ ጦር፣ በተጋጋመ ውጊያ ውስጥ ሆነው ባዘኑ። ትዕዛዝ ለጓዶቻቸው አስተላለፉ። ፈልገው ያመጡላቸው ዘንድ አዘዙ። እስኪመጣላቸው ድረስ ታመሙ፣ በጠና ደከሙ። በማይወጡት ለቅሶ ተዋጡ። ጓዶቻቸው ፈልገው አገኙና አመጡላቸው። እርሳቸውም ተደስተው ፈገግ አሉ። "ይህንን ፀጉር ከእኔ ጋር ይዤ በተገኘሁበት ዘመቻ ሁሉ ድል የእኔ ነበረ" ሲሉ ተናገሩ። ህመማቸውን ተፈወሱ። ሀዘናቸውን ተካሱ። ይህ ነው የፍቅር ህክምናው።

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
Atiqa Ahmed Ali
498 views19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 22:34:55
461 views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 22:05:20 الْمَغْرِب Morocco
918 viewsedited  19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 12:55:51
(100 ሺ ሰብስክራይብ አመሰግናለሁ )
https://youtube.co/@AMIRHUSSENofficial

[ لا يَشْكُرُ اللَّهَ مَنْ لا يَشْكُرُ النَّاسَ]
[ሰዎችን የማያመሰግን ሰው አሏህን አያመሰግንም።]

አሰላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዐ እንዴት ናቹ አልሀምዱሊላህ ዩቲዩብ ፔጅ በከፈትኩ በ አጭር ጊዜ ዉስጥ 100 ሺህ ሰብስክራይብ መግባት ችያለዉ። አሌሀምዱሊላህ እዚህ ደረጃ ለመድረሴ የ አንበሳዉን ድርሻ
የምቶስዱት እናንተ ናችሁ። ይህ ደስታ የ እኔ ብቻ ሳይሆን የ ሁላችንም ነዉ!! subscribe ላደረጋችሁኝ፣ ላበረታታችሁኝ ጭምር ነዉ ለዚህም ከልብ አመሰግናቹሀለዉ።

እንዲሁም ከ ጎኔ ሆናችሁ በብዙ ነገር ስታግዙኝ ሆነ ስደግፉኝ ለነበራችሁ ወንድምቼ ፣ የ ስራ ባልደረቦቼ በ እኔም እንዲሁም በ ወዳጅ አድናቂዎቼ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

አመሰግናለሁ
-ቤተሰቦቼን በተለይ እናቴን እንዲሁም ወንድሜ ሰለሀዲንን

-ለ ገጣሚ እና ዜማ ደራሲ አብዱል ማሊክ ላሊ (ጎራዉ)

-ኢትዮ ነሺዳ እና መንዙማ አባላት

- ለ ፉአድ ሸምሱ እና ለመላዉ የ ከዋኪብ አባላት በሙሉ

እንዲሁም ለ እኔ ስኬት ደፋ ቀና ስትሉ ለነበራችሁ ወንድም እህቶች በሙሉ ...

ይህ ደስታ የእኔ ብቻ ሳይሆን የ ሁላችንም ነዉ።

አዲስነትና ለውጥ የኛ አንጻራዊ እውቀት ነው።
አንተ የቻልከውን ካደረስክ በኃል ለውጤቱ አትጨነቅ ።

ከጥረትህ ውጭ ሆኖ ለሚከሰተው ነገርም በሐሳብ ወደኃላ እየተመለስክ '''በሆነ ኖሮ,,, በማለት አትብሰልሰል።

ሰበቡን አድርስ አላህ ያሳካልሀል።
እጅህን ወደ አላህ ዘርጋ እሱ ይቀበልሀል።

አሚር ሁሴን

መልካም ቀን ተመኘሁ!!
826 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 23:18:56 #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

የመካ መኳንንት ግፍ በነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እና ባልደረቦቻቸው ላይ በርትቷል። ዱላ እና ግርፋቱ ያለማባራት እየዘነበ ነው። ያኔ ነብያችን ባልደረቦቻቸውን ከሀበሻ ቀጥሎ ወደ መዲና ይጓዙ ዘንድ አዘዙ። ትዕዛዛቸውም ተፈፀመ። በመዲና የሰፈሩት ሶሀቦች "ሙሐጂር" ተሰኙ። ታዲያ ከእነዚህ ሙሐጂሮች አንዱ የነብያችን ወዳጅ ፣ አጎት እና የጥቢ ወንድም የሆኑት ሰይዱና ሐምዛ (ረ.ዐ) ነበሩ። እንዲያ ከሚሳሱላቸው ተወዳጅ ሠው ተለይተው በመዲና መቀመጣቸው አክስቷቸዋል፣ በጀግንነት ጀብዳቸው ላይ የናፍቆት ካባ ተደርቦ ሸፍኖባቸዋል፤ እጅጉን በናፍቆት ይንከላወሳሉ። ሌት ተቀን ከመዲና ሰዎች እና ሶሀቦች ጋር በመሆን የመዲናን መግቢያ ተራሮች ያማትራሉ። ነብያችንን ናፍቀው ዛፍ እና ቆጡን እየወጡ ይጠባበቃሉ። ጊዜው ራቀባቸው።

ይህ የሰይዱና ሐምዛ ፍቅር በዓይናቸው ባላዯቸው የመዲና ነዋሪዎችም ላይ በርትቶ ታይቷል። "የአሏህ መልዕክተኛ አለ" ተብሎ ተነገራቸው እንጂ በዓይናቸው አልተመለከቷቸውም ፣ ውብ እጆቻቸውን አልዳበሷቸውም ፣ ጨረቃ መልካቸውን አላዩም ፣ ጣፋጭ ንግግሮቻቸውን አላደመጡም። ይህም ሆኖ የፀሀይን መውጣት ተከትሎ ቀድመው የከተማዋ ጫፍ ላይ በመውጣት ይጠብቋቸው ነበረ። በእንዲህ ያለ ሁኔታ በሰኞ ቀትር ላይ ከሩቁ ሁለት ሰዎች የመዲናን ጎራ እያቆራረጡ ብቅ ሲሉ አንድ የመዲና አይሁድ ወጣት ይመለከታል። ናፋቂዎቹ ፀሀዩ ስለበረታባቸው ወደየቤታቸው እየተመለሱ ነበረ። በዚህ ጊዜ "እናንተ የቂላህ ልጆች ሆይ! በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው ነብይ መጥቶላችኋል" እያለ ጮኸ። አንድ ወጣት አማኝም ድምፁን ከፍ አደረገና

"ها هو الرسول. اقبل الهادي البشير"
"እኚያው የአሏህ መልእከተኛ ፣ ቀጥተኛውን መንገድ አመላካቹ እና በመልካም አብሳሪው ነብይ መጡ" ሲል አዋጁን አወጀ። ታዲያ ይህ ወጣት ነብያችን የትኛው ፣ ሰይዲና አቡበክርም የትኛው እንደሆኑ አያውቅም ነበር። ግና ምፃታቸው በራሱ አንዳች የፍቅር መግነጢስ አሳረፈበትና በፍቅር ጥሪ ይጣራ ዘንድ ሳበው። እነዚያ ሳያዯቸው የናፈቋቸው ሰዎች በፍጥነት ወደ እርሳቸው ይገሰግሱ ጀመረ ፣ ሰይዳችንም ወደእነርሱ መጠጋታቸውን አፈጠኑት። ሰይዱና አቡበክር የፀሀዩን ሀሩር ሊከላከሉላቸው ሰይዳችንን በካባቸው አስጠልለዋል። በዚህ ነበረ ጉጉዎቹ የመዲና ሰዎች የሰይዳችንን እና የሰይድ አቡበክርን ማንነት ለይተው ለማወቅ የቻሉት። ሁሉም ወደ ነቢ ተጠጋ። ሰይዱና ሐምዛ ተጠግተው የናፍቆት ጥማቸውን በእቅፍ ጠጅ አረገቡት።

አንሷር ከሙሐጂር በአንድነት ተቀኝተው
طلع البدر علينا
እያሉ አሞገሷቸው። እርግጥም በዚያ ጠራራ ፀሀይ ውብ ጨረቃ ተፈልቅቃ መዲና ላይ ዘልቃለች። በእልልታ ተቀበሏቸው። ናፍቆታቸውን አቀዘቀዙ። በፍቅር ተገርፈው ፣ በናፍቆት ታስረው ከርመው በእይታ ታከሙ፣ በሰላምታ ተፈወሱ።
እጅግ ናፍቆት፣ እጅግ ፍቅር፣ ፍቅር ይህ ነው። ሳያዩ መናፈቅ።

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
Atiqa Ahmed Ali
669 views20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 11:33:38 Watch "#ያረቢ ሶሊ || ሙባረክ ባህሩ አዲስ የመንዙማ ክሊፕ" on YouTube


553 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ