Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Neshida & Menzuma

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_neshida
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.99K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ #YouTube ቻናል 👇
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma
ወደ #Facebook Page 👇
https://www.facebook.com/Ethio-Neshida-Menzuma-348031129044029/
ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት(bot) ተጠቅሞ ያድርሱን✍️
👇
@ETHIO_NESHIDA_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-10-20 19:55:12 #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ሶለዋት የአሏህ እዝነት መፋሰሻ በሆኑት ነብይ ላይ የሚንቧቧ የደስታ ወንዝ ነው። ከዚህ ወንዝ ጥቂት እየጨለፍን እንጠጣ። የጥፍጥናውን ለዛ በማስከሪያ ጣዕም እንቅመሰው። ለአሏህ የሚሰገድ ሶላት በሙሉ መሪው (ኢማሙ) ነብዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ናቸው። በነብዩ ላይ የሚወርድ ሶለዋት በሙሉ ኢማሙ አሏህ (ጀለ ሸእኑሁ) ነው። ከየትኛውም የዓለም ጫፍ ሆኖ ሶለዋት የሚያወርድ ሠው የአሏህን መሪነት ተከትሎ ነው። ጌትዬው በነብዩ ላይ የሚያወርደው ሶለዋት "መደድ" ነው። እኛ ሶለዋት ባወረድን ጊዜ ከዚህ የጌታችን መደድ እንቋደሳለን። ወደ አሏህ ቁርብ ለመዳረስ ትልቁ በር መሆኑንም ይህ አመላክቷል

إن الله وملائكته يصلون علي النبي
ሲል በታላቁ ሰማይ ላይ አዋጁን አስነገረ። ከኩርስይ ተነስቶ እስከ ዓርሽ በተዘረጋው ሂጃቡ ላይ ግዴታነቱን አስደነገገ። የሶለዋቱን ልቅና እናውቅ ዘንድ ጌትዬው በራሱ ጀመረው። ጉዱ እዚህ ላይ ተምቧልቋል። አሏህ በቀጥታ ትእዛዙን ወደ እኛ አላወረደውም። ከእርሱ የፈለቀውን ሀያል ኑር በመላእክቶች አሳለፈው። ይህ ኑር በእነርሱ ዘንድ አልፎ እና የበረደ ሆኖ ይቆያል። ከእነርሱ ቀዝቀዝ ያለ ጊዜ
يا ايها الذين امنوا صلوا عليه
ተብሎ ወደ እኛ ዘንድ ተወረደ። የሙሓባው ቃጠሎ ነዲድ እሳቱ በሙእሚኖች ላይ ተደረገ። በሸሆቹ ሐድራ ይህንን ኸበር "ጉድ" ብለን ሰማን። ከታላላቆቹ አንደኛው፣ የዘመናቸው ብቸኛው፣ የወልዮች መሪ፣ የቁጥቦቹ አስተማሪ ሰይዲ ዐብዱሰላም አል‐ሚሺሺይ እንዲህ ሲሉ የሶለዋትን ጥራት በአውራዳቸው አፈሰሱ። የነብዩን ማንነት አናውቅምና ልኬታችንን ማሳረፊያ ትምህርቱን ቀረፁልን
اللهم صل عليه صلاة تليق بك منك له كما هو اهله
"ጌታዬ ሆይ በአንተ ልቅና የሚስማማ ከአንተ የሆነን እዝነትህን ለእርሱ ልቅና አስማምተህ አውርድበት" ሲሉ ቅመማቸውን አጣፈጡ። ከወደ ኸሚስ አመሻሽ ቁጥሩ የበዛ
اللهم صل عليه صلاة تليق بك منك له كما هو اهله،وسلم عليه سلاما كاملا كما يلق بجلالك لجماله.
وكمالك كما هو اهله، وآله وصحبه
የሚለውን "ሶለዋቱል‐ሚሺሺያህ‐ከማሊያህ‐መኽዚሚያህ" መደጋገም ኸይራቱ የበዛ ነው። ከጭንቀት መገላገያ ቁልፉ ሶለዋት ነውና። የሪዝቅ ማገኛው ተስሊማት ነው። ነፍስህን ሰላም ማድረግ ብትሻ ፣ መንፈስህን ማደስ ብትከጅል ፣ ሰውነትህን ማበርታት ብትፈልግ በብርቱው ፣ በሰላሙ እና በውዱ ነብይህ ላይ ሶለዋትን አጉረፍርፍ!

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
Atiqa Ahmed Ali
4.2K viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 19:55:02
3.6K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-17 01:24:11 A child showing love & respect for Sayyidunah Rasoolallah ﷺ
4.8K views22:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-17 01:24:05
4.4K views22:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 11:44:00 እሳቸው ከተሟላ ሰውነት በላይ ናቸው!
ሌላ ሰው ሊሰራው በሚችል መልካም ባህሪያቸው እንመራበታለን እንጂ እሳቸውን አንለካበትም!

ሚስጥራቸው አልተገለጠ ደረጃቸውም አልታወቀ ሰው መስለው ባገኘናቸው ልክ የምንወዳቸው... በውዴታችን ልክ ሀያእ የምናደርጋቸው... ከሀያአችን የተነሳም የሚወዱትን የምናደርግላቸው... በፍቅር እንጂ በሌላ መንገድ የማይደረስባቸው ስጦታችን. የፍጥረታት የበላይ ሹም... የዩኒቨርሱ ህልውና ዋስትና ናቸው

አላህ አወድሶ ጨርሷቸዋል... ለራሳችን ስንል በሳቸው ላይ ሶላዋት እናወርዳለን... ሰላምታችንም ቀጥታ ይደርሳቸዋል... መልስ ይሠጡናል በዛም ይደሰቱብናል

ሶላዋታቸው ሁሉንም ይተካል!

اللهم صل على سيدنا محمد الفاتح لما اغلق والخاتم لماسبق ناصر الحق بالحق والهادي الى صراطك المستقيم وعلى اله حق قدره ومقداره العظيم.

Jumma Mubarak
5.6K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 11:43:46
4.7K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ