Get Mystery Box with random crypto!

እሳቸው ከተሟላ ሰውነት በላይ ናቸው! ሌላ ሰው ሊሰራው በሚችል መልካም ባህሪያቸው እንመራበታለን እ | Ethio Neshida & Menzuma

እሳቸው ከተሟላ ሰውነት በላይ ናቸው!
ሌላ ሰው ሊሰራው በሚችል መልካም ባህሪያቸው እንመራበታለን እንጂ እሳቸውን አንለካበትም!

ሚስጥራቸው አልተገለጠ ደረጃቸውም አልታወቀ ሰው መስለው ባገኘናቸው ልክ የምንወዳቸው... በውዴታችን ልክ ሀያእ የምናደርጋቸው... ከሀያአችን የተነሳም የሚወዱትን የምናደርግላቸው... በፍቅር እንጂ በሌላ መንገድ የማይደረስባቸው ስጦታችን. የፍጥረታት የበላይ ሹም... የዩኒቨርሱ ህልውና ዋስትና ናቸው

አላህ አወድሶ ጨርሷቸዋል... ለራሳችን ስንል በሳቸው ላይ ሶላዋት እናወርዳለን... ሰላምታችንም ቀጥታ ይደርሳቸዋል... መልስ ይሠጡናል በዛም ይደሰቱብናል

ሶላዋታቸው ሁሉንም ይተካል!

اللهم صل على سيدنا محمد الفاتح لما اغلق والخاتم لماسبق ناصر الحق بالحق والهادي الى صراطك المستقيم وعلى اله حق قدره ومقداره العظيم.

Jumma Mubarak