Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 57.97K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 506

2021-03-18 21:45:07
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ 2,057 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘዋል

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ #ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 8,055 የላብራቶሪ ምርመራ 2,057 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 330 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 181,869 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,602 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 145,349 ሰዎች አገግመዋል።

የዛሬ መጋቢት 9 ሁኔታ ፦

- 600 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች

- በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ 2,057 ይህ 26% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ ነው (#እስካሁን_ከፍተኛው) በማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበን አናውቅም ፤

- 10 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 8 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦

1. ሲዳማ-45%
2. ድሬዳዋ-40%
3. አዲስ አበባ-26%
4. ኦሮሚያ- 31%
5. ደቡብ- 20%
6. አማራ- 20%
7. ቤንሻንጉል-29%
8. ሐረር- 23%

@ethio_mereja_news
@etho_mereja_news
2.1K viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 18:38:12 የቴድ ቡናማው አሟሟት ከጓደኛው አንደበት/ጓደኛው ሲያወራ እንባ ተናነቀው/ከፖለቲካ አታገናኙት



736 views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 16:22:04
#ዜና_ዕረፍት

ባለስልጣኑ ተገደሉ።

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን የሄበን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ በሪሶ ቡልዬ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በየተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

አቶ በሪሶ ትላንት ምሽት 1:30 ነው በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈው።

የሄበን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አቶ በሪሶ ለህዝቡ ሰላም እና እድገት ቀን እና ማታ ሲለፉ የነበሩ የህዝብ አገልጋይ መሆናቸውን አውስቶ በህልፈታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@etho_mereja_news
1.4K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 14:49:14
Good news

አሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም አገራት ካልጋበዟት በስተቀር አገራቱን ለማደራደር ጣልቃ እንደማትገባ አስታወቀች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ “ቴን” በተባለ የግብጽ የሳተላይት ቴሌቪዥን ላይ በሚሰራጨው “ፔን ኤንድ ፔፐር” ዝግጅት ላይ በዙም ተጋብዘው በሰጡት ማብራሪያ፤ የአባይ ወንዝ ለግብጽ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ለሱዳንም በጣም ጠቃሚ ወንዝ መሆኑን አሜሪካ ታምናለች ብለዋል። በአገራቱ መካከል ያለው ልዩነት በውይይትና በድርድር እንዲፈታ አገራቸው ድጋፍ ማድረጋን እንደምትቀጥል ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ አሜሪከ ሶስቱም አገራት ጥሪ ካደረጉላት የሚጠበቅባትን አዎንታዊ ሚና ለመወጣት ዝግጅት እያደረገች መሆኗን ነው የገለጹት። አሜሪካ በግድቡ ዙሪያ ያሉ አለመግባባቶች መፈታታ ያለበት በሶስቱ አገራት ብቻ ነው የሚል አቋም እንዳላት የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ አገራቸው በሶስቱ አገራት ጥሪ ካልቀረበላት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ አስታውቀዋል። (ዋልታ)
33 views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 14:08:11 ቻይና አሜሪካን አስጠነቀቀች!

ከሰሞኑ አሜሪካ የጦር መርከቦቿን ወደ ታይዋን የባህር ሰርጥ አስጠግታለች፡፡
ይህ አካባቢ ታይዋንን ከቻይና የሚለይ አካባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የአሜሪካ የጦር መርከቦች በዚህ አካባቢ የሚሰማሩ ከሆነ ቻይና ወደ ታይዋን እንደፈለጋት የምታደርገዉን ጉዞ የሚገድብ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ፡፡

ድርጊቱ ታይዋን ራሷን የቻለች ሀገር እንደሆነች እንዲሰማት የሚያደርግና እንደዛም እንድታስብ የሚገፋፋ በመሆኑ በፍጹም ተቀባይነት የለዉም ስትል ቻይና አሜሪካን ወቅሳለች፡፡

ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብና በአካባቢዉ የተጠጉ የጦር መርከቦቿን እንድትመልስም አስጠንቅቃለች፡፡
አሜሪካ በበኩሏ አካባቢዉን የመቆጣጠር ሃላፊነቱ የቻይና ሳይሆን የታይዋን ነዉ ስትል ገልጻለች፡፡

ሁለቱ ሀገራት በታይዋን ጉዳይ በተደጋጋሚ እየተወዛገቡ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡(ፕሬስ ቲቪ)

@ethio_mereja_news
@etho_mereja_news
183 views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 13:54:03 በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ሓይሎች ምክንያት የሚደርሰዉን ሰብአዊ ቀዉስ የፈደራልና የክልል መንግስታት በመተባበር እንዲያስቆሙ አብንና ባልደራስ ጠየቁ፡፡

አብንና ባልደራስ በቀጣዩ ምርጫ በትብብር ለመስራት መፈራረማቸዉን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መግለጫቸዉም በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ሓሎች ምክንያት ዜጎች ለሞት፤ አካል ጉዳት፣ መፈናቀል እየተዳረጉ ነዉ፤ከፍተኛ ንብረትም እየወደመ ነዉ፤ይህን ለማስቆምም የፌደራል እና የክልል መንግስታት ተግተዉ እንዲሰሩም ጠይቀዋል፡፡

በሁለቱ ፓርቲ አመራሮች መካከል ለወራት ሲካሄድ የነበረዉ ድርድር ተጠናቆ ምርጫዉን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ የሚያስችል ስልት መቀየሳቸዉንም በዛሬዉ እለት በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡

ከዚህ በፊት በጋራ አብሮ ለመስራት ያልቻሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች፤ አሁንም ጊዜዉ ባለመርፈዱ ፍላጎት ካላቸዉ ለመቀበል ዝግጁ ነን ብለዋል ፓርቲዎቹ፡፡

ፓተርቲዎቹ አሁን የፈጠሩት ህብረት ለሌሎች አርአያ መሆን የሚችና ከትናንት የተሻለ የፖለቲካ ባህል ማሳያ ፈር ቀዳጅ እንደሚሆንም አመልክተዋል፡፡

ከምርጫዉ በኋላም ትብብሩ ጎልቶ የአገሪቱን ህዝብ ለዘመናት የቆየ የፍትህ ትግል ዳር ለማድረስ እንቀሳቀሳለን ነዉ ያሉት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ አመራርነት ለመስጠት ከወዲሁ አብረን ቆመናል ብለዋል፡፡

አብን እና ባልደራስ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ እራስን በራስ የማስተዳደር ዲሞክራሲያዊ መብት አክብረዉ ከሚቀበሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ትብብር በመፍጠር ዜጎች በፌደራል መንግስት ዉስጥ ዉክልና እንዲኖራቸዉ ጥምረቱ ሚና ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

ፓርቲዎቹ ያላግባብ ተወንጅለዉ ለእስር የተዳረጉትንና የመምረጥና የመመረጥ መብታቸወን የተፈጉት የባልደራስ አመራሮችም በአስቸኳይ ይፈጡልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የትግራይ ክልልን በተመለከተ ባነሱት ሃሳብ፣ ትህነግ በለኮሰዉ ጦርነት በትግራይ ክልል ባለዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ የንፁሃን ዜጎች ደህንነት እንዲጠበበቅና የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይደርስ ልዩ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
763 views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 13:03:51 የቡና ጥቅም እና ሊያስከትለው የሚችለው አስደንጋጭ ጉዳት



1.0K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 12:37:07
ባልደራስ እና አብን የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ!

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ፓርቲዎቹ የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው ለመስራት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያን ከፅንፈኛ ሀይሎችና አስተሳሰቦች መታደግ የሚያስችል ዓላማ ይዘው ጥምረት መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነትም ተፈራርመዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.7K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 11:28:41
በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ ትምህርት ቤት አንድ ርዕሰ መምህር መፀዳጃ ቤት ወድቆ ለጠፋበት ስልክ የ11 ዓመት እድሜ ያለውን ተማሪ እጁን ጉድጓድ ውስጥ ከቶ ስልኩን እንዲያወጣለት ማስገደዱ ቁጣ ፈጠረ

በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆነው የ49 ዓመቱ ሉቤኮ ማጋንዴላ መፀዳጃ ቤት ወድቆ ለጠፋበት ስልክ የ11 ዓመት እድሜ ያለው ተማሪን መፀዳጃ ቤቱን ቆፍሮ ስልኩን እንዲያወጣለት አስገድዷል።ተማሪው ይህንን ካደረገለት 200 የደቡብ አፍሪካ ራንድ ወይም 14 የአሜሪካ ዶላር እንደሚሰጠው ቃል ይገባለታል።

ይህንን ድርጊት የፈፀመው ርዕሰ መምህር በዋስትና ከእስር ቢለቀቅም ድርጊቱ ቁጣ ፈጥሯል።የተማሪው አያት በርዕሰ መምህሩ ድርጊት የተነሳ ልጃችን በሌሎች ተማሪዎች መሳለቂያ እሆናለሁ በሚል ስጋት ወደ ትምህርት ቤት መሄድን ፈርቷል ሲሉ ተደምጠዋል።

የምስራቃዊ ኬፕታውን የትምህርት ባለስልጣናት የተማሪዎ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት በመሄድ በድርጊቱ ማዘናቸውን እንደሚገልፁ አስታውቀዋል።

የ11 ዓመቱ ተማሪ ስልኩ ገብቷል ወደተባለበት የመፀዳጃ ጉድጓድ በጉልበቱ ተንበርክኮ ሲፈልግ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ተሰራጭቷል።የሞባይል ስልኩ ያልተገኘ ሲሆን ለተማሪው ድካም ርዕሰ መምህሩ እሰጥሃለው ካለው ገንዘብ ቀንሶ 50 ራንድ ሰጥቶታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2.8K viewsedited  08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-18 10:45:19 ፑቲን ገዳይ ነው፤በአሜሪካን ምርጫ ራሺያ ጣልቃ ለመግባት በመሞከሯ ዋጋ ትከፍላለች ሲሉ ጆ ባይደን ዛቱ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደተናገሩት በአሜሪካ የ2020 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሩሲያ ለትራምፕ የሚያግዝ የምርጫ ጣልቃ ገብነት እንደነበራት በአሜሪካ የደህንነት ቢሮ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዋጋ ይከፍላሉ ብለዋል።


የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ቢሮ ማክሰኞ እለት ባወጣው ባለ 15 ገፅ ሪፖርት መሰረት የሩሲያ መንግስት በ 2020 የአሜሪካ ምርጫ ተፅዕኖ ለመፍጠር መንቀሳቀሱን ይፋ አድርጓል፡፡በተለይም የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ሩሲያ ሰርታለች፡፡

በጆ ባይደን ላይ አሳሳች እና ተአማኒ ያልሆኑ ውንጀላዎች በሩሲያ መንግስት ተደግፎ ሲሰራ እንደነበረ ተነስቷል፡፡

ባይደን በትላንትናው እለት ከኤቢሲ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት የፑቲን አስተዳደር በዚህ ጉዳይ እጁ እንዳለበት ሙሉ ለሙሉ ማረጋገጥ ከተቻለ ዋጋ ይከፍላል፤የእጁን ያገኛል ብለዋል።

ፑቲን በመተቸት የሚታወቀው አሌክሲ ናቫሊን ነርቭን በሚየጠቃ ንጥረ ነገር መመረዝን ተከትሎ አሜሪካ ከቀናቶች በፊት በአራት የሩሲያ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጥላለች።ሩሲያ ግን እርምጃው በውስጥ ጒዳይ ለመግባት የተሞከረ ስትል አጣጥላዋለች።(በስምኦን ደረጄ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.1K viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ