Get Mystery Box with random crypto!

ኤሽታኦል

የቴሌግራም ቻናል አርማ eshtaol_today — ኤሽታኦል
የቴሌግራም ቻናል አርማ eshtaol_today — ኤሽታኦል
የሰርጥ አድራሻ: @eshtaol_today
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 222
የሰርጥ መግለጫ

ክርስቶስን መስለን በመንፈሳዊውም ሆነ በምድራዊ የላቀ ህይወት እንዲኖረን የሚረዳንን ከመንፈሱ የሆነ እውነትን ከቃሉ ምንቋደስበት የምንፈወስበት #የደስታ #የእረፍት #የሰላም channel ነው

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-20 07:56:28 በየመንደሩ እንደ ሸቀጥ ሱቅ እየፈሉ ስላሉ ቸርቾች ( ሁሉም አደሉም) የተጻፈ ግጥም
ለሁሉም ያጋሩ።

ርዐስ #እስኪ #ስም #አውጡለት

ቤቲ ከኳየር ተጣልታ፥
ማስጠንቀቂያ ፈርታ።
ጆኒ ከዩዝ ቲም ተኳርፎ፥
የአገልግሎት እገዳ ሸሽቶ።
እማማ ከናቶች ህብረት ተቀያይመው፥
ከመታረቅ ቂም በልባቸው አዝለው።
አባባ ከመሪዎች ተጣልተው፤
ጭቅጭቅን ተሰላችተው፤
እረፍትን ፈልገው ።
ፓስተር ደሞዝ አንሶት፥
ስለስህተት ትምህርት ክትትል በዝቶበት፥
እቺም ደሞዝ ሆና አለቃ በዛባት እንዳለው ጥበቃ፥
ፓስተሩም እንዲህ አለ እኔም በዚህ ደሞዝ በዛብኝ ግምገማ፥
ፓስተር እንዲህ አሰበ፥
ሚወዱኝን ሰዎች ከቸርች ሰብስቤ፥
መሀል ከተማ አማኝ በበዛበት ቤት ተከራይቼ ፥
አንድ አለምአቀፍ ቸርች ከፍታለሁ በርትቼ።

በዚህ ተነሳስቶ፤
ፊርማ አሰባስቦ፤
ግንባር ቦታ ላይ ቤት ተከራይቶ፤
አንድ ስፒከርና አንድ ኪቦርድ ገዝቶ፤
ኪቦርድ ተጫዋች አንድ ወጣት ቀጥሮ፤
ከየቸርቹ ተቀያይመው አኩርፈው ለመጡ በሮቹን ከፈተ፤
ባለራዕይና መስራች ብሎ ራሱን ሾመ።
ሁሉም ተጠናቆ ስም ብቻ ጎደለ፥
ግሪክ እብረይስጥ ሁሉን አገላብጦ ሳቢ ስም ፈለገ፥
አወጣ አወረደ
ያሰበው ስም ሁሉ ስለተያዘበት፥
ስም አውጣልኝ ብሎ ወደኔ መጣና ስም አወጣሁለት።
ያኮረፉ ምዕመናን አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን
የኔን ስለጠላው ስላልተዋጠለት
ስም ጠፋ ባገሩ' እስኪ ስም አውጡለት።

Comment ላይ ሀሳባችሁን በነጻነት አስቀምጡ


ሌላ ቸርች ስትቀላቀሉ ቸርቹ የተከፈተበትን ትክክለኛ ምክንያት እና መሠረት ልናውቅ ይገባል
መሠረቱ ፍቅር ሳይሆን ኩርፊያ ከሆነ
መስጠት ሳይሆን መቀበል ከሆነ
ክርሰቶስ ሳይሆን ግለሰብ ከሆነ
አታተርፉም አትሂዱ

@Eshtaol_today
@Eshtaol_today
79 viewsedited  04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:24:01 እንኳን ደስ አለን
117 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 18:46:13 “እግዚአብሔር፣ ለሚወዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ #ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።”
— ሮሜ 8፥28 (አዲሱ መ.ት)


ዛሬ ሒሳብ ላስተምራችሁ ነው።

በሒሳብ #negative ሲባዛ #negative #positive ነው።

Negative ሲባዛ positive ሲባዛ positive ሲባዛ negative ሲባዛ positive ሲባዛ negative ሲባዛpositive ሲባዛ negative ሲባዛ positive ሲባዛ negativeሲባዛ positive ሲባዛ negative
#Positive ነው::


ክፉውም በጎውም ተያይዞ ለበጎ ማለት እንደዚህ ነው። እንደ ቁጥሩ መልሱ positive እንደሆነው።
145 viewsedited  15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 22:40:49
ሰላም ለናንተ ይሁን ያለፈውን 9 ወር በ ኢትዮጰያ ማሪታይም አካዳሚ የ Marine engineer ወይም የመርከበኝነት ስልጠና በባህር ዳር ከተማ ስወስድ ቆይቼ እግዚአብሔር ፈቅዶ ዛሬ ግንቦት 24 2014 እመረቃለሁ። ያለፈውን 9 ወር በብዙ ከጎኔ የነበረውን የረዳኝን እግዚአብሔርን አመስግኑልኝ።
144 views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 07:37:55 ሰላም ለናንተ ይሁን ያለፈውን 9 ወር በ ኢትዮጰያ ማሪታይም አካዳሚ የ Marine engineer ወይም የመርከበኝነት ስልጠና በባህር ዳር ከተማ ስወስድ ቆይቼ እግዚአብሔር ፈቅዶ ዛሬ ግንቦት 24 2014 እመረቃለሁ። ያለፈውን 9 ወር በብዙ ከጎኔ የነበረውን የረዳኝን እግዚአብሔርን አመስግኑልኝ።
138 views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 09:24:32 የግጥም ስብስቦች ቀጥታ ከመድረክ የተቀዳ ባህርዳር ሙሉ ወንጌል
ወንድማችሁ ሳሚ ነኝ
151 viewsedited  06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 09:24:08 በባህርዳር ሙሉወንጌል የፋሲካ አዳር ፕሮግራም ላይ ያቀረብኳቸውን ግጥሞች በጥሩ የድምጽ ጥራት ይኸው ለናንተ።

ስሟቸው ስትወዷቸው ለምትወዷቸው ሁሉ አጋሩ
134 views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 09:16:45 "የሐዋርያት የእምነት መግለጫ
እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በአንድ ልጁ፣
በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣
ከድንግል ማርያም በተወለደ፣
በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣
በተሰቀለ፣ በሞተ እና በተቀበረ፤
ወደ ሲዖልም በወረደ፡፡
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሣ፡፡
ወደ ሰማይም በወጣ
ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣
ከዚያም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በሚመለስ፣
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ፣
በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን፣በቅዱሳን አንድነት
በኀጢአት ስርየት፣
በሥጋ ትንሣኤ፣
በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡ አሜን፡፡"
142 views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 22:08:37 በቅርቡ የፋሲካ አዳር ላይ የቀረቡ ግጥሞችን በድምጽ እልክላችኋለሁ።
መልካም ምሽት
117 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 22:02:24 በቅርቡ የፋሲካ አዳር ላይ የቀረቡ ግጥሞችን በድምጽ እልክላችኋለሁ።
መልካም ምሽት
111 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ