Get Mystery Box with random crypto!

በየመንደሩ እንደ ሸቀጥ ሱቅ እየፈሉ ስላሉ ቸርቾች ( ሁሉም አደሉም) የተጻፈ ግጥም ለሁሉም ያጋሩ | ኤሽታኦል

በየመንደሩ እንደ ሸቀጥ ሱቅ እየፈሉ ስላሉ ቸርቾች ( ሁሉም አደሉም) የተጻፈ ግጥም
ለሁሉም ያጋሩ።

ርዐስ #እስኪ #ስም #አውጡለት

ቤቲ ከኳየር ተጣልታ፥
ማስጠንቀቂያ ፈርታ።
ጆኒ ከዩዝ ቲም ተኳርፎ፥
የአገልግሎት እገዳ ሸሽቶ።
እማማ ከናቶች ህብረት ተቀያይመው፥
ከመታረቅ ቂም በልባቸው አዝለው።
አባባ ከመሪዎች ተጣልተው፤
ጭቅጭቅን ተሰላችተው፤
እረፍትን ፈልገው ።
ፓስተር ደሞዝ አንሶት፥
ስለስህተት ትምህርት ክትትል በዝቶበት፥
እቺም ደሞዝ ሆና አለቃ በዛባት እንዳለው ጥበቃ፥
ፓስተሩም እንዲህ አለ እኔም በዚህ ደሞዝ በዛብኝ ግምገማ፥
ፓስተር እንዲህ አሰበ፥
ሚወዱኝን ሰዎች ከቸርች ሰብስቤ፥
መሀል ከተማ አማኝ በበዛበት ቤት ተከራይቼ ፥
አንድ አለምአቀፍ ቸርች ከፍታለሁ በርትቼ።

በዚህ ተነሳስቶ፤
ፊርማ አሰባስቦ፤
ግንባር ቦታ ላይ ቤት ተከራይቶ፤
አንድ ስፒከርና አንድ ኪቦርድ ገዝቶ፤
ኪቦርድ ተጫዋች አንድ ወጣት ቀጥሮ፤
ከየቸርቹ ተቀያይመው አኩርፈው ለመጡ በሮቹን ከፈተ፤
ባለራዕይና መስራች ብሎ ራሱን ሾመ።
ሁሉም ተጠናቆ ስም ብቻ ጎደለ፥
ግሪክ እብረይስጥ ሁሉን አገላብጦ ሳቢ ስም ፈለገ፥
አወጣ አወረደ
ያሰበው ስም ሁሉ ስለተያዘበት፥
ስም አውጣልኝ ብሎ ወደኔ መጣና ስም አወጣሁለት።
ያኮረፉ ምዕመናን አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን
የኔን ስለጠላው ስላልተዋጠለት
ስም ጠፋ ባገሩ' እስኪ ስም አውጡለት።

Comment ላይ ሀሳባችሁን በነጻነት አስቀምጡ


ሌላ ቸርች ስትቀላቀሉ ቸርቹ የተከፈተበትን ትክክለኛ ምክንያት እና መሠረት ልናውቅ ይገባል
መሠረቱ ፍቅር ሳይሆን ኩርፊያ ከሆነ
መስጠት ሳይሆን መቀበል ከሆነ
ክርሰቶስ ሳይሆን ግለሰብ ከሆነ
አታተርፉም አትሂዱ

@Eshtaol_today
@Eshtaol_today