Get Mystery Box with random crypto!

'የሐዋርያት የእምነት መግለጫ እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አም | ኤሽታኦል

"የሐዋርያት የእምነት መግለጫ
እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በአንድ ልጁ፣
በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣
ከድንግል ማርያም በተወለደ፣
በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣
በተሰቀለ፣ በሞተ እና በተቀበረ፤
ወደ ሲዖልም በወረደ፡፡
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሣ፡፡
ወደ ሰማይም በወጣ
ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣
ከዚያም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በሚመለስ፣
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ፣
በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን፣በቅዱሳን አንድነት
በኀጢአት ስርየት፣
በሥጋ ትንሣኤ፣
በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡ አሜን፡፡"