Get Mystery Box with random crypto!

🍂 ዲነል ኢስላም 🕌

የቴሌግራም ቻናል አርማ dinel_islam — 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌
የቴሌግራም ቻናል አርማ dinel_islam — 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌
የሰርጥ አድራሻ: @dinel_islam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.43K
የሰርጥ መግለጫ

♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)ﷻ (ﷺ)
« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...»
ቁርኣን[ 3:104 ]
መወያያ ግሩፓችን ☞ @Dinel_islam_Group
✔ ሀሳብ አስተያየት ካሎት
👉 @DinelIslam1Bot 📩

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-24 07:54:42 አደራ ወንድም እህቶች!

* ሁሌም ተውበት እናድርግ ወዴ አሏህ እናልቅስ*
* የቀልባችን መድረቅ ሊያሳስበን ይገባል*
ሰዎችን አሻግሮ ከማየት እራሳችንን እንምከር
* አላህን በድብቅም በግልፅም እንፍራ*
ሞት እንዳለብን እናስታውስ
ሞት አለ
ሀቂቃ ከፊት ለፊት ሞት አለ
ሞት

*ሞት ያልመከረውና ያልገሰፀው ልፍ ወየውለት*
* የቀብር ጥያቄና ቅጣት አለ*
*ያ አላህ በራህመትህ*
* ሲራጥ አለ አስበው *
* የስራ ሚዛን አለ*

* ጀሀነም እያጓራ ከፊት ለፊታችን ድቅን የሚልበት ቀን አለ*
* ኧረ ስንቱ ልጥቀስ*
*ይህ ሁሉ እያለብን ባልሰማ ላሽ ብለናል*
በወንጀል ላይ ወንጀል እንደርባለን
መች ይሁን የምንነቃው

* ሀቂቃ ሁኔታችን ያሳዝናል*

*ቆም ብለህ አስብ*
*ነገ ዋጥፋቴ መልሱኝ ወደ ዱንያ አንዴ *ብለህ ከመጮህህ በፊት አሁን ጊዜው አለህ*

* ጉድለትህን ጠግን*
* ከወንጀልህ ተመለስ*
* ከኢባዳ መዘናጋትን ተው*
* ግድ የለሽ አትሁን*
* የአሔራ ቤትህን በኢማን በተቅዋ በመልካም ስራ ገምባ*

*እኖራለሁ ብቻ ሳይሆን እሞታለሁም በል*
*ማረፊያህ ጀነት ይሁን ጀሀነም ገና አልተረጋገጠም*

*አላህ ሆይ እኔንም ወንድም እህቶቼን ማረን ቀጥ ብለው ያንተን ትእዛዝ ከሚፈፅሙት አድርገን ያረብ አሚን

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.8K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:08:30 ለሸይኹ እንዲ ብሎ ጠየቃቸው... "አማኝ(ሙእሚን) መሆኔን በምን አወቃለው"??
ሸይኹም ይህን ቁርአን አነበቡለት...

إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُهُۥ زَادَتْهُمْ إِيمَٰنًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

..ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ يُنفِقُونَ

....እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው፡፡

أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُؤْمِنُونَ حَقًّا

እነዚያ በእውነት አማኞች እነሱ ብቻ ናቸው፡፡

ያረቢ ካሚል የሆነ ኢማን ወፍቀን

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.4K views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 09:07:03 ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የረገሟቸው የሆኑ 10 ሴቶች..

እነሱም
1. ጅስሟን የምትነቀስ ተነቃሿም ነቃሿም!

2.ቅንድቧን የምተቀነደብ ቀንዳቢዋም ተቀንዳቢዋም!

3.አርቲፊሻል ፀጉር የምትቀጥል ቀጣይዋም ተቀጣይዋም!

4.ባሏን የምታስቀይም የምታናድድ የሱን ሀቅ የማትጠብቅ!

5.በአለባበሷም ሆነ በማንኛውም ነገር ከወንድ ጋር የምትመሳሰል!

6.ቀብር የምትዘይር!

7.ሰው ሲሞት እየጮሀች እያለቀሰች ልብሷን እየቀደደች ሰውን የምታስለቀስ!

8.ባሏ 3 ጊዜ ፈቷት የሸሪአን ህግ ጥሳ ሌላ ሳታገባ እሱጋ የምትመለስ!

9.ጥርሷን የምትጠረብ ለጌጥ ጥርሷን የምትቀይር!

10.ሙተበርጃ ተገላልጣ የምትሄድ የምትራቆት ለአጅነብይ!

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.8K viewsedited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:33:19 መልካም ነገር

ከእለታት አንድ ቀን ኢብኑ አል ሙባረክ (ረ ዓ) አንድ ሰው ከተሰጠው ነገሮች በላይ በላጭ የሆነው ነገር ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ ብስል አዕምሮ ብለው መለሱ።

ጠያቁወቹም እሱ ካልሆነስ አሏቸው
መልካም ስነምግባር በማለት መለሱ።

አሁንም እሱ ካልሆነስ አሏቸው። የሚያማክርው መልካም ጓደኛ በማለት መለሱ። አሁንም እሱ ካልሆነስ አሏቸው።
የረጅም ግዜ ዝምታ በማለት መለሱ።

እሱ ካልሆነስ አሏቸው። ፈጣን የሆነ
ሞት
በማለት መለሱ።

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.6K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 08:38:57 ከአቡበክር ረዐ ደጃፍ ህዝብ ይንጋጋል። አንዳች ግራ ያጋባቸው ጉዳይ እንዳለ ሁኔታቸው ያሳብቃል፦«አንተ የነቢ ምትክ! ሰማይ ዝናብ አቁሟል፣ ምድር ቡቃያዋን አግታለች ህዝብህ ሊያልቅ ነው»

ነቢያቸው ሙቶ የቲም የሆኑትን ህዝቦች አቡበክር በሀዘን እየተመለከታቸው፦«ሂዱ ፤ ትዕግስ አድርጋችሁ ጠብቁ አላህ በዚህ ምሽት መልካም ዜና እንደሚያሰማኝ ተስፋዬን ጥዬበታለሁ»

...ህዝብ ይህን ካደመጠ በኋላ በአሚራቸው ተስፋ ጥለው ወደየመጡበት ተበታተኑ። ቀኑ ተጠናቅቆ ሰማዩ ሊጠቁር መቅላት ሲጀምር 1 ሺህ የሚሆኑ ግመሎች የንግድ ሸጠሸቆጦችን እና ቀለቦችን ጭነው መዲና ተከሰቱ።

...የመዲና ነዋርያን የንግድ ሸቀጦቹን ሲመለከቱ ተገልብጠው በመውጣት አቀባበል ያደርጉላቸው ጀመር። ግመሎቹም የጫኑትን ሸቀጥ ይዘው ወደ ባለንብረቱ ዑስማን ቤት አቀኑ።

ግመሎች የጫኑትን ጭነት ከዑስማን ቤት እንዳራገፉትም ነጋዴዎች ሸቀጡን ለመረከብ የዑስማንን ቤት ተንጋጉበት።

ዑስማን፦«ምን ፈልጋችሁ ነው?»
ነጋዴዎች፦«ለምን እንደመጣን አንተም ታውቃለህ፤ ህዝቡ ምን ያህል እንደተቸገረ ትረዳለህ»
ዑስማን፦«በምን ያህል ትርፍ ትገዙኛላችሁ?»
ነጋዴዎች፦«ሁለት እጥፍ አድርገን እንገዛሀለን»

ዑስማን፦«አይ ከዚህ በላይ ተሰጥቶኛል»
ነጋዴዎች፦«እሺ 4 እጥፍ እንስጥህ»
ዑስማን፦«ከዚህም በላይ ተሰጥቶኛል»
ነጋዴዎች፦«5 እጥፍ እናድርግልሃ!»

ዑስማን፦«ከዚህም በላይ ተሰጥቶኛል»
ነጋዴዎች፦«በከተማዋ ያለነው ነጋዴዎች እኛው ነን ማንም እኛን አልቀደመንምም፤ ታድያ ማን ነው ከዚህ በላይ የሰጠህ?»

ዑስማን፦«አላህ በእያንዳንዱ ዲርሀም 10 ሀሰናት ሰጥቶኛል። እያንዳንዱን ሀሰናትም በ10 አባዝቶልኛል፤ ከዚህ በላይ ልትሰጡኝ ትችላላችሁ?»

ነጋዴዎች፦«አንችልም»
ዑስማን፦«አላህን ምስክር አድርግያለሁ፤ ግመሎቼ ጭነውት የመጡትን ሸቀጦች በሙሉ ለድሃ ሙስሊሞች በነፃ ለግሼዋለሁ»

ንግግሩን እንዳጠናቀቀም ከግቢው የሚገኘውን ሸቀጥ በሙሉ ለድሆች በማከፋፈል ጀነትን ገዝቶ አደረ። በነቢ ሰዐወ እግር ስር ቁጭ ብለው የታነፁ ከዋክብቶችን የሚያስተናግዱት ጀነቶች ምንኛ ታደሉ!!!

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.9K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:31:08 «ፀሐይ ከምትወጣባቸው ቀናት ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው፣ አደም የተፈጠረው ጀነት የገባው ከርሱም የወጣው በጁምዓ ቀን ነው፣ ትንሳኤ በዚህ ቀን ይቆማል»።ረሱል (ሰዐወ)
አቡ ዳውድና ነሳኢ ዘግበውታል

«በዕለተ ጁመዓ አንዲት ወቅት አለች፣ አንድ ሰው አላህን የፈለገውን ነገር ከጠየቀ የጠየቀው ሐራም እስካልሆነ ድረስ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

«አላህ ዘንድ በላጩ ቀን የጁምዓ ቀን ነው»።ረሱል(ሰዐወ)
ምንጭ:-ሶሒሁል ጃሚዕ (1098ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎﻣﻊ: ‏)

«አላህ ዘንድ ከሰላቶች መካከል በላጭ የሆነው ሰላት የጁምዓ ቀን በጀማዓ የተሰገደ የሱብሂ ሰላት ነው»ምንጭ:-ሲልሲለቱ ሶሒሀህ (1566)

«ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ምሽት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ፣ በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ያወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል»
ምንጭ:-ሶሒሁል ጃሚዕ (1209)
ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠጰ ﷺ : «ﺃﻛﺜِﺮﻭﺍ ﺍﻟﺼَّﻼﺓَ ﻋﻠﻲَّ ﻳﻮﻡَ ﺍﻟﺠﻤُﻌﺔِ ﻭ ﻟﻴﻠﺔَ ﺍﻟﺠﻤُﻌﺔِ ، ﻓﻤَﻦ ﺻﻠَّﻰ ﻋﻠﻲَّ ﺻﻼﺓً ﺻﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋﻠﻴﻪِ ﻋَﺸﺮًﺍ.»
ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎﻣﻊ: (1209)
ሰሉ አለል ሀቢብ.........

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.8K views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 20:30:19 "ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን "

ሱብሀነላህ! እንዴት በምን ሒሳብ አንድ አባ ወራ ባል የትዳር አጋሩ የሆነች ሴት ላይ ያውም የአምስት ወር ፅንስ በሆዷ የተሸከመችን ያውም ሙስሊም የሆነ ሰው እንዲህ ዓይነት ጭካኔ ይፈፅማል !?

ዑማው ግን ወዴት እያመራ ይሆን ግን? የተባለው የተነገረው ቂያማ ደረሰ ይሆን ወላሒ ያስፈራል።ያ ጀማዓ! ለመዘገብም ይሰቃል።

ዜናውን ያገኘሁት ከአረብ ኒውስ ነው።ሀና ሙሐመድ ቁድር
የምትባል የሊባኖስ ትሪፖሊ ነዋሪ የሆነች የ21 ዓመት ወጣትና ባለ ትዳር ነች ልጅ ይከሰታል የአምስት ወር ፅንስ ሆነ ባል አባወራም አቅሜ አይችልም ማስወጣት አለብሽ በፍፁም!አለ።

ሚስትም በፍፁም ሞቼ ነው ቆሜ አለች አተካራ ተነሳ ባል ሚስተር ኤ ኤ የመጨረሻውን ጭካኔ ፈፀመባት ቤት ውስጥ ባለ የጋዝ ሲሊንደር እሳት ለቀቀባት ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

በቃጠሎው ሙሉ ለሙሉ ሰውነቷ ተቃጥሎ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ላይ ነች ያቺ ምስኪን መቶ ፐርሰንት ነዳለች። የተኛችበት አል ሰላም ሆስፒታል ዶክተር ሰውነቷ መቶ ፐርሰንት መቃጠሉን አረጋግጠው የሚቻለውን ህክምና ሁሉ እየሞከሩ መሆኑን ለአረብ ኒውስ የገለፁ ሲሆን በህይወትና በሞት መሐል ነች ሲሉ አክለዋል።

የቤተሰቡ አባል የሆነው አብዱራህማን ሐዳድ በጣም በአስጊ ሁኔታ ላይ መሆኗን ገልፆ የሆስፒታሉ ቢል ራሱ ካሁኑ ወደ ሺህ ዶላሮች እንደደረሰና በየቀኑ የ $ 400 ዶላር ወጪ አለው። የሀና ዓይነት ምስኪን ደግሞ የሚችለው እንዳልሆነ ገልጿል።

በዛ ላይ ደግሞ አሉ ዶክተሩ የሀና የአምስት ወር ፅንስ ሆዷ ውስጥ ሞቷል ያን በኦፕሬሽን ለማውጣት የምናደርገው ጥረትም ለሀና ህይወት ሌላው አደጋ ነው ሲሉ የአል ሰላም ሆስፒታል ዶክተር ተናግረዋል።

ሀና ወደ 15 የደም ቅያሪ platelets transfusions እንደሚያስፈልጋትና ለያንዳንዱ $ 100 ዶላር ይፈልጋል ሲል ሐዳድ ጠቅሶ ሐና ደግሞ ከድህነት በታች የሚኖር ቤተሰብ ነው ያላትና ይከብዳል ሲል ይናገራል።

ዶክተር ጋብሬል አል ሳቢ እስካሁን በየቀኑ ሰርጀሪ እየተደረገላት
እንደሆነና የሰውነቷ አብዛኛው ክፍል በመቃጠሉ በ life support ነው ያለችው ብለዋል።

አላህ ሺፋውን ያምጣላት ግን ለምን!?

"ልጆቻችሁን ድኽነትን በመፍራት አትግደሉ፣እናንተንም እነሱንም የምረዝቀው እኔ ነኝ፤" እያለን አላህ ምን ያህል ዑማው በዓለማዊነት መዘፈቁን ከሚያሳዩ ክስተቶች አንዱ ማሳያ ይህ ነው።
" የሴቶቻችሁን ነገር አደራ!"ነበር ያሉት ሐቢቡና (ሰ ዐ ወ) በመጨረሻው ሐጅ ላይ

ባለቤቷ ሚስተር A A በልዩ ጥበቃ በእስር ላይ ይገኛል።
ሀና ድና እናይ እንሰማ ይሆን!? ወላሁ አዕለም! እሱ ምን ይሳነዋል!?#

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.7K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 20:30:05
1.4K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 08:11:57 ተስፋ.....

ታውቃላችሁ ተስፋ የሂወት ጣዕም ነው። ይህ ጣዕም ሲጠፋ ሂወት ውሀ ውሀ ማለት ይጀምራል። ሂወት ውሀ ውሀ ሲል ደግሞ መኖር ትርጉም ያጣል። መኖር ትርጉም ሲያጣ አለመኖር ይከተላል።

ወንድሞች አማኞች ስጋዊና መንፈሳዊ የሆኑ ውስጣዊይና ውጫዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት በስራና በትምህርት ብቻ አይተማመኑም!አማኞች ቢነግዱ ፣ቢማር፣ ቢመራመሩ፣እምነታቸው የተተከለው በአላህ ላይ ነው።

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.6K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:48:40 ዱንያ ላይ ሳለች በአሏህ ትዕዛዝ ላይ
ቀጥ ያለች ሴት.....


ጀነት በምትገባ ጊዜ ጀነት ውስጥ ከተፈጠረችዋ ኹረል አይን የበለጠ ቆንጆና በላጭ ትሆናለች።
••••••••••••••••••••••••••••••

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.7K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ