Get Mystery Box with random crypto!

🍂 ዲነል ኢስላም 🕌

የቴሌግራም ቻናል አርማ dinel_islam — 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌
የቴሌግራም ቻናል አርማ dinel_islam — 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌
የሰርጥ አድራሻ: @dinel_islam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.43K
የሰርጥ መግለጫ

♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)ﷻ (ﷺ)
« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...»
ቁርኣን[ 3:104 ]
መወያያ ግሩፓችን ☞ @Dinel_islam_Group
✔ ሀሳብ አስተያየት ካሎት
👉 @DinelIslam1Bot 📩

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-17 08:10:30 ጭንቅ ላይ ያላችሁ ያአላህ በሉ የተስፋ ቃሉን አስታውሱ እንደ ተራራ የገዘፈው ጉዳያችሁ ለናንተ እነጂ ለሱ ምኑም አይደለም።

ዐለማት ቢጠይቁት ለሁሉም እንደ ፍላጎቱ ሰጥቶ ከሱ ፀጋ መርፌ ከባህር ላይ ምንም እንደ ማይቀንሰው ምንም አይቀንስም ። ስለዚህ ያአላህ በሉ ለሱ ንገሩ ደጋግማችሁ አንኳኩ አትሰልቹ ።

.........የአልጋ ቁራኛ የሆናችሁ ፣ በእዳ የተያዛችሁ ፣ ጠላት ያስጨነቃችሁ ፣ ልጅ ያጣችሁ ፣ እርዝቅ የራቃችሁ ፣ ሰላም የናፈቃችሁ ያአለህ በሉ ። አትሰልቹ አንኳኩ ይከፈታል የፍጡር ደጅ ያልሰለቻችሁ የጌታችሁ ደጅ አይሰልቻችሁ ። ማን ደጅ እንደቆማችሁ አስቡ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ አዛኝ የሆነው ጌታችሁ ደጅ ላይ ናችሁ ያአላህ በሉ አንኳኩ ይከፈታል ።

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.9K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 18:09:43 አዕምሮህ ውስጥ ምንድንነው የምትዘራው? መልካም ሀሳብ ወይስ መጥፎ ሀሳብ? አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ ፤ የዘራኸውን ታጭዳለህ! ደጋግመህ ያሰብከው ሀሳብ በህይወትህ ውስጥ በተግባር ይገለጣል።
ከሚያበረታቱህ ሰዎች ጋር ብቻ ዋል ፤ በጎ ነገር ብቻ ስማ ፤ ብቻህን ስትሆን ራስህን አድንቅ ፤ እንደምትችል ለራስህ ንገረው ፤ አየህ ጠንካራ ስብዕና የሚገነባው እንደዚህ ነው።

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.7K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:16:29 የአላህ_ውሳኔ_ሁሌም_ትክክል_ነው...

ታክሲ ስላመለጠህ አትናደድ: መንትያ ህንፃዎቹ ውስጥ የሚሰራው ጆን ከሞት የተረፈው በዛ ቀን ታክሲ ስላላገኘ ነበር!

አላርሙን በትክክል ስላለሞላህ አትናደድ: ወይዘሮ ማርሊ ያን ቀን አላርሟን በትክክል ስላልሞላች ነው የተረፈችው!

የመኪናህ አንዱ ጎማ ስለተኛ አትበሳጭ: ማርክ በዛ ምክንያት ነው በህይወት የተረፈው!

"ኸይር ማለት አላህ የመረጠልህ ውሳኔ ነው!"
ሰይድ አልኢማም ኢብነል ቀይም

ሁሉም ጉዳይህ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነው: ያመለጠህም ሆነ የተቀማህው ነገር የለም።

አልሀምዱሊላህ!!!

@Dinel_islam @Dinel_islam
400 views11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:30:11 «ሶላቱን ጠብቆ የማይሰግድ ሰው የቂያማ ቀን ከነ ፊርዓውን ከነ ሀማን ከነ ቃሩን ከነ ኡበይ ኢብኑ ኸለፍ ጋር ነው የሚቀሰቀሰው»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

«ሰወች ሆይ! ከጠላት ጋር ተገናኝቶ መፋለምን አትመኙ! ይልቁንስ አላህ ሰላምን እንዲሰጣችሁ ለምኑት፣ ነገር ግን አይቀሬ ሁኖ ከጠላት ጋር ከተገናኛችሁ ወደኋላ አትበሉ ታገሱ»።ረሱል (ሰ ዓ ወ)ምንጭ፦ ሶሒሁል ቡኻሪ

«ከሱብሒ በፊት ያለችዋ ሁለት ረክዓ ሱና ሶላት፣ አጠቃላይ ከዱንያ እና በርሱዋ ውስጥ ከሚገኘው ሁሉ ትበልጣለች»።ረሱል (ሰዐወ)

@Dinel_islam @Dinel_islam
569 views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:23:39 አነስ ኢብኑ-ማሊክ (ረ፡ዐ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሰ፡ዐ፡ወ)እንዲህ አሉ፡-ወደ-ሰማይ) ባረግሁ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ፡፡ጂብሪልንም፡-ማናቸው እነዚህ?ስለው፡ እነዚህ(በሐሜት) የሰዎችን ስጋ የሚበሉና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው አለኝ" (አቡ ዳዉድ)፡፡ሐሜት በውዱና በተፈላጊው ዓለም በአኼራ ባለቤቱን ከከሳሪዎች የሚያደርግ በሽታ ነው፡-

ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡(ቁርአን-49:10)

@Dinel_islam @Dinel_islam
839 views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:10:16 °•ለሰዎች የምትመክረውን ቅድሚያ ራስህን/ነፍስያህን ፈትሽበት ሰዎችን መምክር ቀላል ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለሰዎች የምንመክረው እኔ ተግብሬዋለሁኝ ወይ እኔስ የት ነኝ ብሎ ራስን መገምገም ብዙዎቻችን የዘነጋነው ጉዳይ ነው!

።።ብዙ ሰዎች ሰውን ይመክራሉ ለሰዎች እንደሻማ ናቸው ነገር ግን ዘወር ብለህ ስታያቸው ለራሳቸው ምክር የሚያስፈልጋቸው ሆነው ታገኛለህ ይህ ማለት ለሰዎች ብርሃን ሆነው ለራስ ልክ ሻማ መቅለጥ ማለት ነው እናማ ወዳጆቼ እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ ለራሳችን ትኩረት እንስጠው !!

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.0K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:47:11 ➧. #ኢላሂ! ስሜቴ አሸናፊ አቅሌ ተሸናፊ ነፍሴ ነውረኛ ምላሴ ነገረኛ ታዛዥነቴ አናሳ ወንጀሌ ብዙ ሆነው የልቤን ብርሃን ጋርደውታል።

➧. አንተ ደግሞ ደካማነቴን አዋቂ ነውሬን ደባቂ ወንጀሌን መሀሪ መልካምን አሰሪ ነህና እኔን ለኔ አትተወኝ ያረብ ።

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.1K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 08:50:17 አደራ

➣ዛሬ ሰኞና ማክሰኞን መፆም አይቻልም

የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ (ሶስቱ) የተሽሪቅ ቀናቶች የመብላት የመጠጣት እና አላህን የማውሳት ቀናቶች ናቸው። ] (ሙስሊም ፥ 1141).

ሼር ማድረግ አትርሱ ሁሉም ሙስሊሞች ማወቅ ይኑርበት!

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.3K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 08:28:20 ➲"ልብ የአይን ተከታይ ( ተጎታች) ነው ይባላል ፣

....... ያስለመደውን ይለምዳል ።
አይን መጥፎ ነገርን በለመደ ግዜ ቀልብም ይህንኑ መጥፎ የሚለምድና የሚመኝ ይሆናል ። መልካሙም ላይ እንዲሁ ነው ። እናም አይኖቻችንን ከሓራም እንጠብቅ ። መልካም ነገርን እናስለምዳቸው ።

መልካም ቀን

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.4K views05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:05:28 ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ህልም ያያሉ ልጃቸው በሙሉ ፍቃደኝነት "አባቴ! የታዘዝከውን ፈፅም" ሲላቸው የአላህ ወዳጅ ልጃቸውን ለማረድ ተዘጋጁ። ቢላዋውን በእጃቸው ይዘው ወደ አላህ እንዲህ በማለት ተጣሩ፦
"አምላኬ ሆይ! ይህ ብቸኛ ልጄ ነው። የዓይኔ ማረፊያ፣ የልቤ ፍቅር ነው።"
አላህ (ሱ ወ) እንዲህ ሲላቸው ሰሙ፦"ባሪያዬን እንዳጠፋ የተማፀንክባትን ሌሊት ታስታውሳለህ? አንተ ለልጅህ እንደምታዝነው፣ እኔም ለባሪያዬ እጅግ በጣም አዛኝ፣ እጅግ በጣም ሩኅሩኅ መሆኔን አታውቅምን? አንተ ባሪያዬን እንዳጠፋ ተማፀንከኝ። (ስለዚህ) አሁን ልጅህን እንድትሰዋ እፈልጋለሁ!"
"የአላህን ትዕዛዝ እንድፈፅም ምን ያክል አገዝከኝ!" ቀጥለው እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንስተው ዱዓ አደረጉ፦
"ጌታዬ! ባለሁበት ሁኔታ ትዕግስትን አላብሰኝ! እንግዲህ ምንም አልቀረኝም። አርጅቻለሁና እዘንልኝ!"
ኢስማዒልም (ዐ ሰ) አሉ፦ "ጌታዬ! ትዕግስትን እና ፅናትን አላብሰኝ!። አባቴ ሆይ! የጀነት በሮች ተከፍተዋል።"
መላኢካዎች በነገሩ ግራ ተጋብተውና ተደናግሯቸው ሱጁድ በመውረድ አላህን ይማፀናሉ፦ "ጌታችን ሆይ! ነቢይህ ያንተን ፍቃድ ሊሞላ ለመሰዋዕት ተጋድሟል፣…እዘንላቸው።" ይላሉ።
ኢስማዒል ቀጠሉና ለአባታቸው ፍፁም ታዛዥነታቸውን ለመግለፅ፣ ፅናታቸውን ለማሳየት እንዲህ አሉ፦
"አባቴ! ከፍቅር ማሳያዎች አንዱ አለመዘግየት ነው! በላ የታዘዝከውን ቶሎ ፈፅም!"
ኢብራሒም (ዐ ሰ) ኢስማዒልን
(ዐ ሰ) አጋድመው "ውድ ልጄ! እንግዲህ የውመል ቂያማ ላይ እንገናኝ! በትንሳኤው ቀን ዳግም አይሃለሁ!" አሉትና ቢላዋውን አጥብቀው ይዘው ወደ ኢስማዒል (ዐ ሰ) አንገት ሰነዘሩ። በዚያችው ቅፅበት አላህ (ሱ ወ) ጅብሪልን አዘዘው፦
"ፍጠን። ቢላዋውን ገልብጠው!" ጅብሪል ቢላዋው የኢስማዒልን
(ዐ ሰ) አንገት ከመንካቱ ገለበጠው። ኢብራሒም (ዐ ሰ) እንደገና ቢላዋውን አጥብቀው ይዘው ለመሰንዘር ሞከሩ። ግን መቁረጥ አልቻሉም። ቢላዋው እጃቸው ላይ እንዳለ ተገለበጠ።
~ አላህ (ሱ ወ) እንዲህ አለ፦
~ "ኢብራሒም (ዐ ሰ) ራዕዩን ተቀብሏል። ከልብ ማመኑን አረጋግጧል" ቀጠለና በአላህ
(ሱ ወ) ትዕዛዝ መሰረት ጅብሪል ተክቢራ እያደረገ የጀነት በግ ይዞ ከተፍ አለ።
~ «አላሁ አክበር አላሁ አክበር»
ኢብራሒም (ዐ ሰ) ተክቢራውን ሲሰሙ እንዲህ በማለት ተቀበሉት፦
~ «ላኢላሀ ኢልለሏህ ወላሁ አክበር»
~ ኢስማዒልም (ዐ ሰ) እንዲህ በማለት ተክቢራውን ሞሉት፦
~ «አላሁ አክበር ወሊላሒል ሐምድ»
በዚህ መልኩ የተክቢር አትተሽሪቅ ክፍሎች ተሟሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ ዒድ አል አድሓ (የመስዋዕቱ በዓል) በመጣ ቁጥር በዓሉ ከዋለበት ቀን ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ አራተኛው ቀን የዐስር ወቅት ድረስ ተክቢር አትተሽሪቅ ይባላል።
አባት እና ልጅ በደስታ ተሞልተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። እናታችን ሐጀር ኢስማዒልን (ዐ ሰ) እቅፏ ውስጥ አስገባችው። ወደ ደረቷ በኃይል አስጠጋችው።

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.5K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ