Get Mystery Box with random crypto!

🍂 ዲነል ኢስላም 🕌

የቴሌግራም ቻናል አርማ dinel_islam — 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌
የቴሌግራም ቻናል አርማ dinel_islam — 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌
የሰርጥ አድራሻ: @dinel_islam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.43K
የሰርጥ መግለጫ

♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)ﷻ (ﷺ)
« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...»
ቁርኣን[ 3:104 ]
መወያያ ግሩፓችን ☞ @Dinel_islam_Group
✔ ሀሳብ አስተያየት ካሎት
👉 @DinelIslam1Bot 📩

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:22:00 ጉዳይህን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋና
ፈገግ በል‥ አንድ ነገር ከመጣልህ
ያ ነገር ላንተ ነው ማለት ነው ።

⇘ ካልመጣ ደግሞ ያ ነገር ላንተ አይሆንምማለት ነው ። ከ7 ሰማያት በላይ ያለውአምላክ ጥበበኛና ቸር መሆኑን አትዘንጋ ሁሌም በአላህ ተማመን!

ድንቅ ምሽት

@Dinel_islam @Dinel_islam
447 views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:04:19 የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

....[ እውቀትን ዑለማዎች ላይ ለመኩራራት፣ቂሎችን መሃይሞችን ለመሞገት፣ መቀመጫ ቦታ ለመምረጥ አትማሩ። ይህን ያደረገ ሰው እሳት! እሳት! (ትጠብቀዋለች)
ኢብን ማጀህ እና ኢብን ሒባን ዘግበውታል።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ:- [ መልካም ስራዎች ከመጥፎ አወዳደቅ(አሟሟት)፤ ከጥፋት እና አደጋ ይጠብቃሉ። በዱንያ(ቅርቢቱ ዓለም) የመልካም ስራ ባለቤቶች በመጨረሻይቱም ዓለም የመልካም ስራ ምንዳ ባለቤቶች ናቸው።] ሓኪም ዘግበውታል።

@Dinel_islam @Dinel_islam
715 views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:09:15 ለራስህ ስትል መልካም ሁን!!!

ለሰው መልካም መሆን ካልቻልክ ክፋትን አትመኝለት ::
ሰውን መርዳት ካልቻል ባገኘው ነገር አትመቀኘው ይልቁን በረካ እንዲያደርግለት ዱዐ አድርግለት ::
ለሰው ጥሩ መሆን ካልቻልክ መጥፎ ግን አትሁን መጥፎነትህ ቀን ቆጥሮ ይክስሀል ::
እርግጠኛ ሁን ዛሬ የጎዳህ ነገ እሱንም የሚጎዳው ሰው አያጣም :: ዛሬ ያስለቀሰህ ሰው ነገ የሚያስለቅሰው ሰው አያጣም ::
ምድር ትዞራለች አንተ የሚጠበቅብህ በሰብር መኖር ብቻ ነው።
ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደውና የዋህነት አይጎዳም::
አንዳንድ ሰዎች የዋህ ስንሆንላቸው እንደሞኝ ያዩናል ነገር ግን ያ የዋህ ሰው ካንተ በላይ ብልጥ መሆኑን እወቅ ::
ሰው ካስቀየመክ ሰው ካስከፍ ይቅርታ አድርግለት በአንተ ይቅርታ ማለት እሱም ይማርበታል በስራውም ነገር ያፍራል::
ለራስህ ስትል መልካም ሁን መልካምነት አያስከፍልም ::
ዛሬ ያጣነው ነገ እናገኘዋለን ዛሬ ያገኘነው ነገ እናጣዋለን ዱንያ እንዲህ ናት !

@Dinel_islam @Dinel_islam
987 views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:04:15 ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ في ظِلِّهِ، يَومَ لا ظِلَّ إلّا ظِلُّهُ: الإمامُ العادِلُ، وشابٌّ نَشَأَ في عِبادَةِ رَبِّهِ، ورَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ في المَساجِدِ، ورَجُلانِ تَحابّا في اللَّهِ اجْتَمعا عليه وتَفَرَّقا عليه، ورَجُلٌ طَلَبَتْهُ امْرَأَةٌ ذاتُ مَنْصِبٍ وجَمالٍ، فَقالَ: إنِّي أخافُ اللَّهَ، ورَجُلٌ تَصَدَّقَ، أخْفى حتّى لا تَعْلَمَ شِمالُهُ ما تُنْفِقُ يَمِينُهُ، ورَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خالِيًا فَفاضَتْ عَيْناهُ.﴾

“ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት በቂያማ ቀን በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። እነሱም፦ ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ ላይ ያደገ ወጣት፣ ልቡ ከመስጂዶች ጋር የተንጠለጠለን ሰው፣ ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ፣ የልቅናና የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት (ለዝሙት) ጠርታው ‘እኔ አላህን እፈራለሁ’ ያለ ሰው፣
ምፅዋትን ‘ሰደቃ’ የሚሰጥ ሆኖ ቀኝ እጁ የሚመፀውተውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ የሚደብቅ ሰው፣ አላህን በማስታወስ አይኑ የሚያነባ ሰው ናቸው።”
ቡኻሪ (1423) ሙስሊም (1031) ዘግበውታል!

@Dinel_islam @Dinel_islam
586 views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:52:58
ዝሙት በየሜዳው ሲሰበክና ሰዉ ትዳርን እያጣጣለ በዝሙት ሲዘምን እያየን ዝም
እንበል! ታዛቢዎትም እንሁን! ዝሙትን ለመከላከል ሁላችንም የምንችለውን ሳይሆን የሚጠበቅበን እናድርግ!

.....አንዱ ትውልድ ዛፍን ሲተክል ሌላው እንደሚጠለልበት ሁሉእንዱ ትውልድ ኃጢአትን ሲዘራ የኃጢአቱ መዘዝ በቀጣዩ ትውልድ ላይ በረጅሙ ጥላውን ያጠልበታል፡፡ በውጤቱም ያኛው የዚኛው ተከታይ ይሆናል፡፡ በፍርዱም ዕለት እርስ በርስ ይረጋገማሉ፡፡ አንዱ አስከታይ ሌላኛው ተከታይ ሆነው ሁለቱም በእጥፍ
ይቀጣሉ፡፡ ይህንኑ ማረጋገጥ ከፈለጉ ሱረቱል አዕራፍ ከ38-39 ያሉትን አናቅጽ ያንብቡ፡፡(Surah Al-A’raf (الأعراف), verses: 38)

قَالَ ٱدْخُلُوا۟ فِىٓ أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُم مِّنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ فِى ٱلنَّارِ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا حَتَّىٰٓ إِذَا ٱدَّارَكُوا۟ فِيهَا جَمِيعًا قَالَتْ أُخْرَىٰهُمْ لِأُولَىٰهُمْ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ أَضَلُّونَا فَـَٔاتِهِمْ عَذَابًا ضِعْفًا مِّنَ ٱلنَّارِ قَالَ لِكُلٍّ ضِعْفٌ وَلَٰكِن لَّا تَعْلَمُونَ

«ከጋኔንም ከሰውም ከእናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር ኾናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ» ይላቸዋል፡፡ አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር (ያሳሳተቻትን) ብጤዋን ትረግማለች፡፡ መላውም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙም ጊዜ የኋለኛይቱ ለመጀመሪያይቱ (ተከታዮች ለአስከታዮች) «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን፡፡ ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው» ትላለች፡፡ (አላህም)፡- ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም ይላቸዋል፡፡

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.0K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:59:16 ኢላሂ! ስሜቴ አሸናፊ አቅሌ ተሸናፊ ነፍሴ ነውረኛ ምላሴ ነገረኛ ታዛዥነቴ አናሳ ወንጀሌ ብዙ ሆነው የልቤን ብርሃን ጋርደውታል።

አንተ ደግሞ ደካማነቴን አዋቂ ነውሬን ደባቂ ወንጀሌን መሀሪ መልካምን አሰሪ ነህና እኔን ለኔ አትተወኝ ያረብ ።


@Dinel_islam @Dinel_islam
1.1K views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:11:33 ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት መጥታ እንዲህ አለቻቸው፡

«ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት

«አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ። ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ።

በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ። ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በርሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ
«አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን።

አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።

ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት።

<< አሏህ ለኛ የተሻለውን እንጂ አያደርግም!!>>

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.9K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:38:51 ዛሬ ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ !

የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ]
. (ሙስሊም ዘግቦታል).

اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.

ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዳወሳችው፡- ‹‹ሰዎች (የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት) ይሰሩ ነበር፡፡ ወደ መስጊድ ሲሄዱም በስራ ላይ በነበሩበት ሁኔታ (ላባቸው እየተንቆረቆረና ገላቸውን ሳይታጠቡ) ነበር፡፡ በመሆኑም በዕለተ ጁሙዓ ገላቸውን እንዲታጠቡ ተጠየቁ፡፡››(ቡኻሪ ዘግበውታል)

ሰሉ አለ ረሱል ....

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.4K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 07:32:50 ይታሰብበት

ሶላትን ለመገላገል ያህል ብሎ መስገድ ይብቃ !!

..ሶላት ከትልልቅ ስራዎቻችን ውስጥ አንዱና ታላቁ መሆኑ ግልፅ ነው ።

...ታዲያ ይህንን ታላቅ ስራ ብዙዎች ለመገላገል ያህል በሚያሳዝን ሁኔታ አሯሩጠው ይሰግዱታል ።

የማይረቡ የዱንያ ጉዳዮች ላይ ሰአታትን እያጠፋን እዚህ ክቡር ስራ ላይ 10 ደቂቃ መቆየት አለመቻላችን አሳፋሪ ነው ።

አጅሩንና ለዛውን አብዝተን እናገኘው ዘንድ ተረጋግተን እንስገድ ። በአግባቡ በተሰገደ ግዜም ከወንጀሎች የሚጠብቀን ይሆናል!

ሼር አትርሱ!

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.5K views04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:03:57 በህይወትህ ከምንም በፊት ቅድሚያ የሰጠኸው ለ-ዲንህ ከሆነ ...

....ሌላው ነገር ሁሉ ቦታውን እና ጊዜውን ጠብቆ ታገኘዋለህ!!!

@Dinel_islam @Dinel_islam
1.4K viewsedited  15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ