Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ጉባኤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawi_gubae — መንፈሳዊ ጉባኤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawi_gubae — መንፈሳዊ ጉባኤ
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawi_gubae
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.49K
የሰርጥ መግለጫ

ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም።
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4 : 7
@Menfesawi_Gubae
ጥያቄ ካላችሁ ከታች ባለው አድራሻ መጠየቅ ትችላላችሁ።
@HenokAsrat3

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 09:00:35
99 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 08:56:41 ቅዱሰ ፓትርያርኩ ሕክምናቸውን አጠናቀው ጷጉሜን ፩ ቀን ፳፻ ፲ወ ፬ ዓ.ም ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው ይመለሳሉ።
**********
ነሐሴ ፳፮ ቀን ፳፻ ፲ወ ፬ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
***
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሐምሌ ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም ወደ ሰሜን አሜሪካ በማቅናት ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሕክምናቸውን በሚገባ በመከታተልና የጤናቸው ሁኔታም በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ጷጉሜን ፩ቀን ፳፻ ፲ ወ፬ ዓ.ም ወደ አገራቸው ኢትዮጵያና ወደ ቅዱስ መንበራቸው እንደሚመለሱ ታውቋል።

የቅዱስነታቸውን ወደ አገር ቤት መመለስን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የአቀባበል ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።የተቋቋመው ኮሚቴ የካህናት፣የሰንበት ትምህርት ቤቶች፣የመርሐ ግብር ዝግጅትና የጸጥታ ኮሚቴዎችን ያቀፈ ሲሆን በሁሉም ዘርፍ አመርቂ ውጤት የታየበት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።

የአቀባበል ኮሚቴው በጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ዋና
ሥራ አስኪያጅ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ሰብሳቢነት የሚመራ
መ/ብ አባ ተክለያሬድ ጎርጎርዮስ የሰንበት ትምህርት ቤቶት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ
1/ መ/ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
2/ መ/ር እንቆባህርይ ተከስተ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
3/ መ/ሕ ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ የቋሚና ጊዚያዊ ፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ
4/ ወ/ሮ ጽጌረዳ አለሙ የበጀትና ሒሳብ መምሪያ ኃላፊ በአባልነት ተመድበው የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት ላይ ይገኛሉ።

የኮሚቴ አባላቱ የካህናትና የሰንበት ተማሪዎች የቅድመ አቀባበል ሥራዎችን በሚገባ በማከናወን ዝግጅታቸውን አጠናቀው የቅዱስነታቸውን መምጣት እየተጠባበቁ የሚገኙ ሲሆን
ከፕሮቶኮልና ከአየር መንገድ የቪአይፒ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሥራውን እንዲመሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው መ/ሕ ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ አስፈላጊውን የፕሮቶኮል አቀባበል ሥርዓቶችን ቀድመው በማጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በሚገባ ተወጥተው የቅዱስ ፓትርያርኩን መምጣት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል ይበል ብለናል ።

የበጀት፣ የመርሐ ግብር ዝግጅትና የጸጥታ ሥራዎችን እንዲሰሩ የተመደቡት ም/ል ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የቅዱስነታቸው ልዮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የበጀትና ሒሳብ መምሪያ ኃላፊዎች አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሁሉ በሚገባ ማጠናቀቃቸውም ታውቋል።
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ዶ /ር አቡነ ጴጥሮስም የኮሚቴውን የሥራ እንቅስቃሴ በሚገባ በመምራትና በማስተባበር ሥራውን በአስደናቂ መልኩ ለውጤት ለማብቃት ሌት ከቀን እየደከሙ ይገኛሉ።
እግዚአብሔር ለብጹዕነትዎ
ረጅም ጊዜን ይሰጥዎ ዘንድ ጸሎታችን ነው ።
የቅዱስነታቸውን ወደ አገራቸው መመለስን በማስመልከትም የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ሕብረት ጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩን የቀለም መቀባት ሥራ የሙያ ሥራ ድጋፍ በማድረግ (ነጻ የጉልበት ሥራ በማከናወን) በቅዱስነታቸው ወደ መንበረ ክብራቸው መመለስ የተሰማቸውን ደስታ የሚገልጽ የበረከት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

የቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል መርሐ ግብር በአየር መንገድ በመገኘት እንዲቀበሉ በተፈቀደላቸው ብፁዓን አባቶች፣በጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣በካህናትና በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከተከናወነ በኃላ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በምልዓተ ሕዝ ብ ይፋዊ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የወጣው መርሐ ግብር ያስረዳል።
በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤም የቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ አገራቸው መመለስን በማስመልከት ውይይት በማድረግና የአቀባበል ሥነሥርዓቱን ዝርዝር የሥራ ሒደት በማስመልከት ተወያይቶ ያሳለፈውን ውሳኔ መነሻ በማድረግ ሥራዎች በሚገባ እየተከናወኑ መሆኑም ታውቋል።
95 views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 08:55:44 #እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_እናንተም_የምትወዱት_ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡

ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡

በአዲስ ዓመት አዲስ ይህወት
100 views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:30:14 "ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡

እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ወደ_ኦሎምፒያስ)
393 views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:17:59 ወዳጄ ሆይ፦
ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛቆሮ.10፥31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
154 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:06:40 #ኹሉንም_ነገር_ለእግዚአብሔር_እንስጠው

ወርቅን የሚያነጥር ሰው አንዲትን የወርቅ ቅንጣት ወደ እሳት ውስጥ ጨምሮ እጅግ ንጹህ እስክትኾን ድረስ ይጠብቃታል፡፡ እግዚአብሔርም ልክ እንደዚሁ ሰዎች እስኪነጹ፣ እስኪለወጡና ባገኛቸው ነገር ጥቅም እስኪያገኙ ድረስ ፈተና ውስጥ እንዲቆዩ ይፈቅዳል፡፡ ይህ ደግሞ ከጥቅምም እጅግ ከፍ ያለ ጥቅም ነው፡፡

ስለዚህ ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም ተስፋ ሊቈርጥ አይገባውም፡፡ ያ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያኽል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኵሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንሔድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቈርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡

ይህን በማስመልከትም ጠቢቡ ሰው እንደዚህ ሲል መክሮናል፡- “ልጄ ሆይ! ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሔድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ፤ ልብህን አቅና፤ ኹልጊዜ ታገሥ፤ አታወላውልም፤ በመከራ ብትጨነቅም አትጠራጠር” /ሲራ.2፥1-2/፡፡ “ኹሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ስጠው፡፡” ለምን? እግዚአብሔር ከዚያ መከራ መቼ እኛን ማውጣት እንዳለበት ያውቃልና፡፡ ስለዚህ ኹሉንም ለእርሱ ልንሰጥ፣ ዘወትር እርሱን ልናመሰግን፣ ኹሉንም ነገር - ጥቅምም ይኹን ቅጣት - በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፤ ይህም ቢኾን ለእኛ ረብሕ የሚኾን ነውና፡፡ አንድ ሐኪም፥ ሐኪም የሚባለው ታካሚውን ገላዉን ሲያጥበውና ሲመግበው እንዲሁም ደስ ወደሚያሰኝ ስፍራ ሲወስደው ብቻ አይደለም፤ በእርሱ (በታማሚው) ሰውነት ላይ የቀዶ ጥገና ምላጭና ቢላ ሲያሳርፍም ጭምር ሐኪም ነው፡፡ አባትም አባት የሚባለው ልጁን ሲንከባከብ ብቻ አይደለም፤ የገዛ ልጁን ከቤት ሲያስወጣው፣ ሲገሥጸው፣ ሲገርፈውም ያው አባት ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔር ከሐኪሞችም በላይ ሰውን ወዳጅ እንደ ኾነ በማወቅ፥ ምን ዓይነት የሕክምና ዓይነት እንደሚሰጠን በጥልቀት አንጠይቅ፤ ወይም ደግሞ ለደረሰብን መከራ እርሱን ተጠያቂ አናድርግ፡፡ ከዚህ ይልቅ እርሱ የወደደውን ነገር - ቅጣትም ይኹን ቅጣት የሌለው ነገር - ብቻ ምንም ይኹን ምን በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፡፡

በየትኛውም መንገድም ቢኾን የእርሱ ፈቃድ እኛ እንድንድንና ከእርሱ ጋር አንድ እንድንኾን ነውና፡፡ የትኛው መንገድ ለእኛ እንደሚጠቅምም እርሱ ያውቋል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የትኛው መንገድ ወደ እርሱ እንደሚመልሰው ያውቃል፡፡ ኹላችንም እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ልንድን እንደምንችል ያውቃል፡፡ በመኾኑም የሚመራን በዚህ እኛ በምንድንበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ወደየትኛውም መንገድ ቢወስደንም - ልክ እንደ መጻጉዑ - እርሱ እንደሚያዘ’ን ተከትለን መሔድ እንጂ ትልቁ ጉዳያችን በለስላሳና በቀላል አልያም ደግሞ በከባድና በሸካራ ጎዳና እንድንሔድ የሚያዘ’ንን ትእዛዝ መኾን የለበትም (ልንሔድበት የሚገባው መንገድ እርሱ ስለሚያውቀው እንዲሁ መታዘዝ እንጂ የመንገዱን ከባድነት ወይም ቀላልነት የእኛ አጀንዳ ሊኾን አይገባውም፡፡)

(#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ መልእክታት - ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው )
478 views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:16:29 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!

የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

መልካም ቀን
602 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:15:30
Video from henok
871 views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 21:32:00 እንዴት ናችሁ ጸሎት እንዴት ነበር ምን አጋጠማችሁ ምንስ ገጠማችሁ የውስጣችሁ ሰላም እንዴት ነበር በጸሎት በረታችሁ በውስጥ መስመር ሀሳባችሁን ግለጹልኝ
እንኳንም አደረሳችሁ
676 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:18:54 ❖ ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡
እንኳን አደረሳችሁ እህት ወንድሞቼ
670 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ