Get Mystery Box with random crypto!

'ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ' ሱብሀነላህ! እንዴት በምን ሒሳብ አንድ አባ ወራ ባል | 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌

"ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን "

ሱብሀነላህ! እንዴት በምን ሒሳብ አንድ አባ ወራ ባል የትዳር አጋሩ የሆነች ሴት ላይ ያውም የአምስት ወር ፅንስ በሆዷ የተሸከመችን ያውም ሙስሊም የሆነ ሰው እንዲህ ዓይነት ጭካኔ ይፈፅማል !?

ዑማው ግን ወዴት እያመራ ይሆን ግን? የተባለው የተነገረው ቂያማ ደረሰ ይሆን ወላሒ ያስፈራል።ያ ጀማዓ! ለመዘገብም ይሰቃል።

ዜናውን ያገኘሁት ከአረብ ኒውስ ነው።ሀና ሙሐመድ ቁድር
የምትባል የሊባኖስ ትሪፖሊ ነዋሪ የሆነች የ21 ዓመት ወጣትና ባለ ትዳር ነች ልጅ ይከሰታል የአምስት ወር ፅንስ ሆነ ባል አባወራም አቅሜ አይችልም ማስወጣት አለብሽ በፍፁም!አለ።

ሚስትም በፍፁም ሞቼ ነው ቆሜ አለች አተካራ ተነሳ ባል ሚስተር ኤ ኤ የመጨረሻውን ጭካኔ ፈፀመባት ቤት ውስጥ ባለ የጋዝ ሲሊንደር እሳት ለቀቀባት ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

በቃጠሎው ሙሉ ለሙሉ ሰውነቷ ተቃጥሎ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ላይ ነች ያቺ ምስኪን መቶ ፐርሰንት ነዳለች። የተኛችበት አል ሰላም ሆስፒታል ዶክተር ሰውነቷ መቶ ፐርሰንት መቃጠሉን አረጋግጠው የሚቻለውን ህክምና ሁሉ እየሞከሩ መሆኑን ለአረብ ኒውስ የገለፁ ሲሆን በህይወትና በሞት መሐል ነች ሲሉ አክለዋል።

የቤተሰቡ አባል የሆነው አብዱራህማን ሐዳድ በጣም በአስጊ ሁኔታ ላይ መሆኗን ገልፆ የሆስፒታሉ ቢል ራሱ ካሁኑ ወደ ሺህ ዶላሮች እንደደረሰና በየቀኑ የ $ 400 ዶላር ወጪ አለው። የሀና ዓይነት ምስኪን ደግሞ የሚችለው እንዳልሆነ ገልጿል።

በዛ ላይ ደግሞ አሉ ዶክተሩ የሀና የአምስት ወር ፅንስ ሆዷ ውስጥ ሞቷል ያን በኦፕሬሽን ለማውጣት የምናደርገው ጥረትም ለሀና ህይወት ሌላው አደጋ ነው ሲሉ የአል ሰላም ሆስፒታል ዶክተር ተናግረዋል።

ሀና ወደ 15 የደም ቅያሪ platelets transfusions እንደሚያስፈልጋትና ለያንዳንዱ $ 100 ዶላር ይፈልጋል ሲል ሐዳድ ጠቅሶ ሐና ደግሞ ከድህነት በታች የሚኖር ቤተሰብ ነው ያላትና ይከብዳል ሲል ይናገራል።

ዶክተር ጋብሬል አል ሳቢ እስካሁን በየቀኑ ሰርጀሪ እየተደረገላት
እንደሆነና የሰውነቷ አብዛኛው ክፍል በመቃጠሉ በ life support ነው ያለችው ብለዋል።

አላህ ሺፋውን ያምጣላት ግን ለምን!?

"ልጆቻችሁን ድኽነትን በመፍራት አትግደሉ፣እናንተንም እነሱንም የምረዝቀው እኔ ነኝ፤" እያለን አላህ ምን ያህል ዑማው በዓለማዊነት መዘፈቁን ከሚያሳዩ ክስተቶች አንዱ ማሳያ ይህ ነው።
" የሴቶቻችሁን ነገር አደራ!"ነበር ያሉት ሐቢቡና (ሰ ዐ ወ) በመጨረሻው ሐጅ ላይ

ባለቤቷ ሚስተር A A በልዩ ጥበቃ በእስር ላይ ይገኛል።
ሀና ድና እናይ እንሰማ ይሆን!? ወላሁ አዕለም! እሱ ምን ይሳነዋል!?#

@Dinel_islam @Dinel_islam