Get Mystery Box with random crypto!

የህይወት ቃል / Word of life

የቴሌግራም ቻናል አርማ dailywordoflife — የህይወት ቃል / Word of life
የቴሌግራም ቻናል አርማ dailywordoflife — የህይወት ቃል / Word of life
የሰርጥ አድራሻ: @dailywordoflife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቴሌግራም ቻናል በየእለቱ ህይወት ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል አጠር ያለ መልእክት የሚቀርብበት ነው። ይህንን ቻናል በመቀላቀልና አብረን ይህንን የህይወት ቃል እንድንመረምር እናድማችኋለን። ጥያቄ ወይም አስተያየት ቢኖራችሁ በዚህ አድራሻ ጻፉልን። @melakalex ወይም 254724416340

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-05 07:16:19 ምዕራፍ 13 - በጌታ መደሰት
ክፍል ስምንት
ምናልባት በስራ ቦታችሁ ችግር ገጥሟችሁ ይሆናል ወይም የወደፊት ተስፋችሁ እየጨላለመባችሁ ሊሆን ይችላል ፤ የውድቀት ስጋት አድሮባችሁ ሊሆንም ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ጣሉና ጉዳያችሁን እንዴት እንደምትፈቱና ጥበብም እንድታገኙ በመፀለይ ውድቀት እና አደጋን ተከላከሉ፡፡ መልካም ውጤት ለማምጣት ልታደርጉ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ ኢየሱስ ሊያግዛችሁ ቃል ቢገባም የራሳችሁ ጥረትም ሊታከልበት ይገባል፡፡ በሰማዩ አባታችሁ በመታመን የምትችሉትን ሁሉ ካደረጋችሁ በኋላ ከዚያ በኋላ የሚመጣውን ውጤት ሁሉ በደስታ ተቀበሉት፡፡
እግዚአብሔር ልጆቹ በችግር ብዛት እንዲጎሳቆሉ አይፈቅድም፡፡ ጌታችን ፈፅሞ አላታለለንም፡፡ እርሱ ለእኛ «መንገዳችሁ ምንም አደጋ ስለሌለበት አትፍሩ» አላለንም:: እርሱ ፈተናና ችግሮች እንዳሉ ያውቃልና በግልፅ ተናግሯል፡፡ እርሱ እኛን ኃጢአትና ጥፋት ካለበት ዓለም ለማውጣት ሳይሆን ዓላማው፤ ወደዘለዓለማዊና ብርቱ መጠጊያችን ወደሆነው ለመምራት ነው:: ስለደቀመዛሙርቱ የፀለየው የእርሱ ፀሎት “ከዓለም እንድታወጣቸው አልልም፤ በዓለም ውስጥ ከዓለም ክፋት እንድትጠብቃቸው እንጂ» (ዮሐ. 17:15) ብሎ ነበር፡፡ «በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ:: ነገር ግን ዓለምን አሸንፌአለሁና በመከራ ደስ ይበላችሁ» ዮሐ 16:33)፡፡ በተራራው ስብከቱ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ በእግዚአብሔር ስለመታመን አስደናቂ ትምህርቶችን አስተምሯል፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ማፅናኛ እንዲሆኑ በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ለእግዚአብሔር ልጆች የተሰጡ ሲሆኑ፣ በዘመናችንም ሕያው ሆነው ይሰራሉ፡፡ አዳኛችን ተከታዮቹን ወደ ሰማይ ወፎች በመጠቆም ውዳሴያቸውን በዝማሬ እንደሚያቀርቡ እና ስለነገ ሮች በ መጨነቅ እንደማይዋጡ ሲያሳያቸው «አይዘሩም አያጭዱም» ይሁን እንጂ ትልቁ አባት የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣቸዋል ብሏል፡፡ አዳኛችን «ከእነዚህ በብዙ አትበልጡምን?» (ማቴ. 6:26) በማለትም ጠይቋል፡፡ ይህ ታላቅ እግዚአብሔር እጁን ለፍጥረቱ ሁሉ በመዘርጋት ለሰውና ለእንስሳ ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣል፡፡ እርሱ ለሰማይ ወፎች እንኳን ሳይቀር ይጠነቀቃል፡፡ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ይሰጣቸዋል፡፡በርግጥ ምንቃራቸውን በመያዝና አፋቸውን በማስከፈት ምግባቸውን አፋቸው ውስጥ አይጥልላቸውም:: የበተነላቸውን ጥራጥሬ ራሳቸው መለቃቀም አለባቸው:: ለትንሿ ጎጆአቸው ግንባታ የሚሆናቸውን ዕቃም ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ጫጩቶቻቸውን መመገብም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለስራ ሲሰማሩ “የሰማይ አባታችሁ ስለሚመግባቸው» ይዘምራሉ፡፡ እናም «እናንተ ከእነርሱ በብዙ አትበልጡም?» እናንተ ግን አስተዋዮችና መንፈሳዊ አምላኪዎች ስትሆኑ ከሰማይ ወፎች የበለጠ ዋጋ የላችሁምን? እኛ በእርሱ ከታመንን፤ የማንነታችን ፈጣሪ፣ የሕይወታችን ጠባቂ እና በመለኮታዊ አምሳሉ የፈጠረን አምላክ የሚያስፈልገንን እንዴት አብልጦ አይሰጠንም?
ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ 118.3
አባት ሆይ፣ መንገዳችን አልጋ ባልጋ እንዳልሆነ ይቁንም በምናልፍበት ሁሉ አንተ ከእኛ ጋር ሆነህ እንደምታሻግረን ቃል ስለገባህልን እናመሰግንሃለን። አሜን።
312 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:16:13
255 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ