2022-07-09 07:41:15
ይቅር በሉ
ጥላቻ፣ መራርነት፣ ቂምና በቀል አየሩን በሞላበት በዚህ ጊዜ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የሆንን ሁሉ፣ እርሱ ስለ ይቅርታ ያስተማረንን ልናስታውስ ያስፈልጋል። በወንጌላት ውስጥ ጌታችን ስለ ይቅርታ ያስተማራቸው ሰባት ጥቅሶች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦ በጸሎት መንፈስ ራሳችንን እየመረመርን እናንብባቸው።
አንደኛ ፣
“ስለዚህ መባህን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በምታቀርብበት ጊዜ ወንድምህ የተቀየመብህ ነገር መኖሩ ትዝ ቢልህ፣ መባህን በዚያው በመሠዊያው ፊት ተወው፤ በመጀመሪያ ሄደህ ከወንድምህ ጋር ተስማማ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን ለእግዚአብሔር አቅርብ። ማቴ 5:23፣ 24
ሁለተኛ፣
“እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ … እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣
በደላችንን ይቅር በለን።” ማቴ 6:12
ሶስተኛ፣
“እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን የሰዎችን ኀጢአት ይቅር የማትሉ ከሆነ፣ አባታችሁም ኀጢአታችሁን ይቅር አይልላችሁም።” ማቴ 6:14፣ 15
አራተኛ፣
“ስለዚህ መንግሥተ ሰማይ፣ በአገልጋዮቹ እጅ የነበረውን ሂሳብ ለመተሳሰብ የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች። ሂሳቡን ማጣራት እንደ ጀመረም ዐሥር ሺህ ታላንት ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ አቀረቡለት። አገልጋዩም ያለበትን ዕዳ መክፈል ስላቃተው እርሱ ራሱ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹና ንብረቱ ሁሉ ተሽጠው ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።
“በዚህ ጊዜ አገልጋዩ እግሩ ላይ ወድቆ፣ ‘ታገሰኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ ሲል ለመነው። ጌታውም አዘነለትና ማረው፤ ዕዳውንም ትቶለት አሰናበተው።
“ያ አገልጋይ ከጌታው ፊት እንደ ወጣ አንድ መቶ ዲናር የእርሱ ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ባልንጀራውን አግኝቶ እንቅ አድርጎ በመያዝ፣ ‘ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ!’ አለው።
“ባልንጀራው አገልጋይም ከፊቱ ወድቆ፣ ‘ታገሠኝ እከፍልሃለሁ’ ብሎ ለመነው።
“ነገር ግን ሊታገሠው ፈቃደኛ ስላልነበረ፣ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ ወህኒ ቤት አስገባው። 31የሆነውን ነገር ያዩ ሌሎች አገልጋዮችም በጣም አዘኑ፤ ሄደውም ሁኔታውን በሙሉ ለጌታቸው ነገሩት።
“በዚህ ጊዜ ጌታው አገልጋዩን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ ‘አንተ ክፉ አገልጋይ፤ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ አንተም ባልንጀራህን ልትምረው አይገባህም ነበርን?’ በቍጣም ያለበትን ዕዳ ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ ለአሳሪዎች አሳልፎ ሰጠው።
“ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ወንድሞቻችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ፣ የሰማዩ አባቴም እንደዚሁ ያደርግባችኋል።” ማቴ 18፡ 25- 35
አምስተኛ፣
“እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፣ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። ይቅር ባትሉ ግን የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።” ማር 11:25፣ 26
ስድስተኛ፣
“አትፍረዱ፤ አይፈረድባችሁም፤ አትኰንኑ፤ አትኰነኑም። ይቅር በሉ፤ ይቅር ትባላላችሁ።” ሉቃ 6:37
ሰባተኛ፣
“ወንድምህ ቢበድል ገሥጸው፤ ቢጸጸት ይቅር በለው። በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ፣ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር በለው።” ሉቃ 17፡ 1,4
አባት ሆይ፣ ይቅር ባይ ልብ ስጠን።
262 views04:41