2023-04-26 12:51:44
https://www.capitalethiopia.com/2023/04/24/ethiopias-debt-distress-signaled-to-drop-from-its-9-year-highs/
በተያዘው የፈረንጆቹ አመት የኢትዮጵያ የውጭ እዳ ከአመታዊ ጥቅል ምርት/ GDP አንፃር የሚኖረው ድርሻ ከዘጠኝ አመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 20 በመቶ በታች እንደሚሆን በቅርቡ ይፋ የተደረገው የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት/ IMF ሪፖርት ተነበየ፡፡
የገንዘብ ድርጅቱ በሪፖርቱ እንዳስቀመጠው የኢትዮጵያ የውጭ እዳ ከጥቅል ምርት አንጻር የሚኖረው ድርሻ እኤአ በ2023 ወደ 18.2 በመቶ እንደሚወርድ ትንበያውን አስቀምጧል፡፡ ይህም መቶኛ በጥቅምት ወር አውጥት ከነበረው የ22.4 በመቶ ትንበያ ዝቅ ያለ ነው፡፡
በተመሳሳይ በ2024 ከጥቅል ምርት አንጻር የእዳው መጠን ወደ 15.8 በመቶ እንደሚሆን ነው ሪፖርቱ የተነበየው፡፡
እኤአ 2017 ኢትዮጵያ ከፍተኛ የእዳ ስጋት ውስጥ መግቧቷን ተከትሎ ንግድ ተኮር ብድር መውሰድ ማቆሟ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ ባለፉት ሶስት አመታት ግድም ወደ አደሪቱ የሚገባው አዳዲስ ብድር በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን በአንጻሩ ለተወሰዱ ብድሮች የምታደርገው ክፍያ እየጨመረ መጥቷል፡፡
ምንም እንኳ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ያጋጠመ ቢሆንም እና አዳዲስ ብድር እየተለቀቀ ባይሆንም አገሪቱ የእዳ ክፍያዋን ሳታዛንፍ እየከፈለች ትገኛለች፡፡ በዚህም መሰረት ባለፉት ሶስታ አመታት የውጭ እዳ ክምችቱ እየቀነሰ መጥቷል፡፡
286 views09:51