2023-04-26 12:52:56
https://www.capitalethiopia.com/2023/04/24/capital-newspaper-samanu-pair-for-social-impact/
25ኛ አመቱን እያከበረ የሚገኘው ካፒታል ጋዜጣ የፋሲካ እና ኢድ በአላትን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ለሚሺ የተለያዩ የፍጆታ እቃዎችን አበረከተ፡፡
ካፒታል ጋዜጣ ከሳማኑ ኤፍኤምጂሲ ጋር በመተባበር የሰጠው ድጋፍ በአየር አምባ አፀደ ህፃናት እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች የተበረከተ ነው፡፡
የ25ኛ አመት ክብረ በአሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እየዘከረ የሚገኘው ጋዜጣው በቀደሙት አመታት የማህበራዊ ሃላፊነቱን በተለያየ መልኩ ሲወጣ የቆየ ነው፡፡
ባሳለፍነው ሀሙስ ሚያዝያ 12 የተሰጠው ድጋፍ የኑሮ ውድነት የፈጠረው ጫና ከግምት በማስገባት ይበለጥ ተጋላጭ ለሆኑ የአየር አምባ የት/ቤት ማህበረሰብ አባላት የቀረበ ነው፡፡
በዚህም መሰረታዊ የሆኑ እንደ ዘይት፣ ሳሙና፣ ዱቄት፣ ፓስታ እንዲሁም ደብተር የፍጆታ እቃዎች ተበርክተዋል፡፡
329 views09:52