Get Mystery Box with random crypto!

Bisratfm101.1

የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat101fm — Bisratfm101.1 B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat101fm — Bisratfm101.1
የሰርጥ አድራሻ: @bisrat101fm
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.16K
የሰርጥ መግለጫ

Bisrat FM 101.1 is a radio station established by Oyaya Multimedia. Journalist Messele Mengistu, is the owner of Oyaya Multimedia and who remained in the hearts of the Ethiopian radio listeners for the past 5 years, has just realized his long time dream a

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-07 14:49:48 የዳንስ ወረርሽኝ





#BisratNews #Oyaya_Multimedia #ኦያያመልቲሚዲያ #BisratFm #BisratTv #ብስራትቴሌቪዥን #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኦያያ

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
58 views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:48:53 የቸልሲ ስር-ነቀል ለውጥ





#BisratNews #Oyaya_Multimedia #ኦያያመልቲሚዲያ #BisratFm #BisratTv #ብስራትቴሌቪዥን #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኦያያ

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
72 views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:37:00 ሰኔ 30፣2014-የንጹሀን ግድያ የሚከሰተዉ በመንግስት ቸልታ ነዉ የሚባለዉ የተሳሳተ ነዉ - ጠ/ሚ አብይ አህመድ

6 ኛዉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተገኙበት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ይገኛል።

ከምክርቤቱ አባላትም ለ ጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ከቀረቡት ጥያቄዎች ዉስጥም የጸጥታ ችግር ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ መከላከል አይገባም ነበር ወይ? የንጹሀንስ ሞት መቼ ያቆማል? በቀጣይስ ችግሩ እንዳይከሰት መንግስት ምንድነዉ እቅዱ? የሚሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ።

ጠ/ሚኒስትር አብይ በመልሳቸዉ የሽብር ቡድኖች የሚፈጽሟቸዉ ጥቃቶች በመንግስት ቸልተኝነት የሚፈጠር ነዉ የሚለዉ የተሳሳተ ነዉ ብለዋል። የሚፈጠሩ የጸጥታ ስጋቶችን ለማረጋጋትም የጸጥታ አካላት ዉድ ህይወታቸዉን እያጡበትም ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ለአብነትም በቅርቡ በወለጋ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ፣ ጋምቤላ ፣ አሙሮ በተከታታይ በተፈጸመሙ ጥቃትቶች በርካታ የጸጥታ ሀይሎች ህወታቸዉን አጥተዉበታል ብለዋል። ደራሼ ላይም የወረዳ አመራሮችን እና የጸጥታ አካላትን ጨምሮ 80 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏልም ማለታቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ጠ/ሚ አብይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች የበርካታ ንጹሀንንም ህይወት መታደግ ችለናልም ብለዋል።

በበረከት ሞገስ

https://bit.ly/3Pb1apu

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
117 views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:23:15
ሰኔ 30፣2014-በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ አዲስ አበባ ሊፈፀሙ የነበሩ ስድስት የሽብር ተግባራት መክሸፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስት አብይ ተናግረዋል።

ይህው የሽብር ቡድን በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ መሰሉን የሽብር ተግባር የመፈፀም እቅድ ቢኖረውም ከሽፏል ሲሉ በተጨማሪነት ተናግረዋል።

በአሁን ሠዓት በየቀኑ ከአሸባሪ ሀይል ጋር እየተፋለመ ይገኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጨምረው ተናግረዋል።

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
95 views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:07:38 ሰኔ 30፣2014-በምክርቤቱ ስበሰባ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል

6ኛዉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተገኙበት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ይገኛል።

ከምክርቤቱ አባላትም ለ ጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪየሰ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ከቀረቡት ጥያቄዎች ዉስጥም~~~

¤ የጸጥታ ችግር ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ መከላከል አይገባም ነበር ወይ? የንጹሀንስ ሞት መቼ ያቆማል? በቀጣይስ እንዳይከሰት መንግስት ምንድነዉ እቅዱ? የሚሉት ይነሳሉ።

¤ በቀጣይ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች ሂደት ተስተጓጉሏል ፤ ለ 2015 ፈተና ለዚህስ መንግስት ምን እያከናወነ ነዉ?

¤ ከትግራይ ክልል ህዝቡ ለሚያሰማዉ ሰቆቃ መንግስት ምን እገዛ እያደረገላቸዉ ነዉ?

ጠ/ሚኒስትሩ በእነዚህ እና ሌሎች በሚቀርቡላቸዉ ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራርያን የሚሰጡ ይሆናል።

https://bit.ly/3ypxbDg

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
82 views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:03:37
ሰኔ 30፣2014-በአማራ ክልል ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ 12 ዜጎች ተገለዋል ተባለ !!

በኢትዮጲያ የተፈፀሙ ዘር ተኮር ጥቃቶችን
ለማውገዝ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች መከላከል የለባቸውም ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ተናግረዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በአማራ ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ሰልፍ በማድረጋቸው ብቻ ለእስር እና እንግልት ተዳርገዋል ሲሉ አባሉ አንስተዋል።

ድርጊቱ ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን እና ያፀደቀቻቸውን አለም አቀፍ ህጎች የሚፃረር በመሆን በአፋጣኝ የእርምት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

እስከ አሁን በተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች 12 ሰዎች ተገለዋል ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ሲሉ አባሉ በፓርላማው አንስተዋል።

ናትናኤል ሀብታሙ

https://bit.ly/3PbYd7Q

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia #አማራ

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
78 viewsedited  07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:00:56
ሰኔ 30፣2014-አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በተደጋጋሚ የሚፈፅመውን የሽብር ድርጊቶች ለማውገዝ ዳተኝነት ያሳያሉ ተብለው በበርካታ ኢትዮጲያውያን ዘንድ ይታማሉ።ከፍ ሲል በተከበረው ምክር ቤት አሸባሪው ተብሎ የተፈረጀውን ኦነግ ሸኔን ታጣቂ ሀይል ኢ መደበኛ ብለው ሲጠቅሱ እና የሽብር ቡድኑ የሚፈፅማቸውን ዘር ተኮር ጅምላ ፍጅት ግጭት በማለት ሲጠቅሱ ይስተዋላሉ የህ/ተ/ም/ቤት አባል አቶ ሙሉቀን አሰፋ ለጠ/ሚ አብይ አህመድ ያቀረቡት ጥያቄ

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
84 views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:21:40 በመፅሀፍ ቅዱስ ከሚገኘው የሶምሶም ታሪክ ጋር የሚመሳል የወንጀል ታሪክ





#BisratNews #Oyaya_Multimedia #ኦያያመልቲሚዲያ #BisratFm #BisratTv #ብስራትቴሌቪዥን #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኦያያ

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
107 views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:41:11 ሰኔ 29፣2014-የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት የፍልስጥኤም ተቀናቃኝ መሪዎችን ከ15 ዓመታት በኃላ እንዲገናኙ አደረጉ

የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቦኔ የፍልስጤም ተቀናቃኝ መሪዎች የሆኑትን ማህሙድ አባስን እና እስማኤል ሃኒያን ተቀብለዋል፡፡የፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት አባስ እና የሃማስ ፖሊት ቢሮና የጋዛ ሰርጥን የሚገዛው ቡድን መሪ የሆኑት ሃኒያን ከ15 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በአልጄሪያ 60ኛው የነጻነት ቀን በዓል ላይ እንዲገኙ በፕሬዝዳንት ቴቦኔ ተጋብዘዋል፡፡አልጄሪያ የፍልስጤም ዋነኛ ደጋፊ ሀገር ነች።በአልጄሪያ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች የተላለፉ ምስሎች እንዳመላከቱት ፕሬዝዳንት ቴቦዩን የፍልስጤም አቻቸው እና ሃኒያ ሲጨብጡ እንዲሁም የሃማስ የልዑካን ቡድን አባላት አባስን አቅፈው ታይተዋል።

ሃኒያ እና አባስ መካከል ንግግር ስለመደረጉ ግን ግልፅ አይደለም።ፕሬዝዳንት አባስ የአልጄሪያን 60ኛ የነጻነት ቀን የሚዘክር የፍልስጤም ማህተም እና በቅርቡ "አልጄሪያ" የሚል ስያሜ የተሰጠውን የራማላ ጎዳና የሚያሳይ ካርታ ለፕሬዝዳንት ቴቦዩን አበርክተዋል።

እ.ኤ.አ. በ2006 በተካሄደው የሕግ አውጭ ምርጫ ሀማስ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ነገር ግን ከአንድ አመት በኋላ በሁለቱ ሰዎች መሪዎች መካከል በተፈጠረ ዉዝግብ ሃማስ በደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት የጋዛ ሰርጥን ተቆጣጥሯል፡፡በውስጣዊ ክፍፍል ምክንያት የፍልስጤም ምርጫ እስካሁን ድረስ አልተካሄደም።

በስምኦን ደረጄ

https://bit.ly/3bNCJ2V

#BisratNews #BisratFm #Algeria

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
189 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:38:46 ሰኔ 29፣2014-በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ወንዝ ዉስጥ ህይወቱ አልፎ ተገኘ

በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታ ህዳሴ ወይም አሮጌው ቄራ በሚባለዉ አካባቢ ትላንት ምሽት 2 ሰዓት ከ27 ደቂቃ ላይ እድሜው 37 የሚገመት ሰው ወንዝ ውስጥ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል፡።

ግለሰቡ ወንዝ ውስጥ ገብቶ በምን ምክንያት ህይወቱ እንዳለፈ ያልታወቀ ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡በሚቀጥለው የሀምሌ ወር ሳምንታት እና ቀናቶች በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በአዲስ አበበ እና ዙሪያዋ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሜትሮሎጀ ኢንስቲትዩት ያወጣውን መረጃ በመጥቀስ ህብረተሰቡ ራሱን ከጎርፍ እና ከበረዶ እንዲጠብቅ እና ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ትላንትና ማምሻውን የጣለው በረዶ ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ እክል መፍጠሩ ተገልጿል፡፡በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ ወይራ ሰፈር በሚባል ቦታ ላይ ትላንት ማምሻውን በጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ የመኖሪያ መንደሮች እና ግቢዎች በበረዶ ግግር ተሸፍነው ሰዎችን እንዳይንቀሳቀሱ አድርጎ እንደነበር ኮሚሽኑ አስታዉቋል፡፡።

የበረዶው ግግር ለሰዎች ሆነ ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ አዳጋች የነበረ ሲሆነረ የኮሚሽኑ የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ለአርባ ደቂቃ ባደረጉት የበረዶ መጥረግ እና በረደውን የመበተን ስራ በሰው ላይ ጉዳት ሳያደርስ ማስወገድ መቻሉን አቶ ነጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በትግስት ላቀዉ

https://bit.ly/3nHjRW1

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia #አዲስ_አበባ

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
122 views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ