Get Mystery Box with random crypto!

ሰኔ 30፣2014-በአማራ ክልል ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ 12 ዜጎች ተገለዋል ተባለ !! በኢትዮጲያ | Bisratfm101.1

ሰኔ 30፣2014-በአማራ ክልል ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ 12 ዜጎች ተገለዋል ተባለ !!

በኢትዮጲያ የተፈፀሙ ዘር ተኮር ጥቃቶችን
ለማውገዝ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች መከላከል የለባቸውም ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ተናግረዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በአማራ ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ሰልፍ በማድረጋቸው ብቻ ለእስር እና እንግልት ተዳርገዋል ሲሉ አባሉ አንስተዋል።

ድርጊቱ ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን እና ያፀደቀቻቸውን አለም አቀፍ ህጎች የሚፃረር በመሆን በአፋጣኝ የእርምት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

እስከ አሁን በተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች 12 ሰዎች ተገለዋል ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ሲሉ አባሉ በፓርላማው አንስተዋል።

ናትናኤል ሀብታሙ

https://bit.ly/3PbYd7Q

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia #አማራ

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv