Get Mystery Box with random crypto!

Bisratfm101.1

የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat101fm — Bisratfm101.1 B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat101fm — Bisratfm101.1
የሰርጥ አድራሻ: @bisrat101fm
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.16K
የሰርጥ መግለጫ

Bisrat FM 101.1 is a radio station established by Oyaya Multimedia. Journalist Messele Mengistu, is the owner of Oyaya Multimedia and who remained in the hearts of the Ethiopian radio listeners for the past 5 years, has just realized his long time dream a

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-29 10:07:19 ነሐሴ 23፤2014-ህንድ በሙስና ተገንብተዋል የተባሉ 100 ሜትር ከፍታ ያላቸውን መንትያ ህንጻዎችን አፈረሰች

በህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊ ከተማ አቅራቢያ በቀጥታ ስርጭት በተላለፈ አስደናቂ ትዕይንት ለዘጠኝ አመታት ከዘለቀ የህግ ዉዝግብ በኋላ ሁለት የመኖሪያ ህንፃዎችን እንዲፈርሱ ተደርጓል፡፡100 ሜትር ከፍታ ያላቸው "መንትያ ህንጻ" መውደም ህንድ በሙስና ገንቢ እና ባለስልጣኖች ላይ ጠንካራ መሆኗን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ህንጻዎቹ ለዘጠኝ ዓመታት የዘለቀ የህግ ክርክር ውስጥ የነበሩ ሲሆን ነዋሪዎች እንዳልነበሩበት ብሎም በሴኮንዶች ልዩነት ውስጥ ወደ ፍርስራሽነት መቀየሩ ተነግሯል፡፡ከ3,700 ኪሎ ግራም በላይ ፈንጂ በማጥመድ ህንጻዎቹ በ12 ሰከንዶ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል፡፡

ህንፃዎቹ የተገነቡት ሱፐርቴክ ሊሚትድ የሪል እስቴት ድርጅት ሲሆን የግንባታ ደንቦችን በመጣስ ተከሷል ይላል የዳጉ ጆርናል ዘገባ።በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሁም ቤት አልባ ውሾች ከፍንዳታው በፊት ከአጎራባች ፎቆች ጭምር እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

https://bit.ly/3pQ033J

#BisratNews #BisratFM #Ethiopia #India

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
179 views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:00:54 ነሐሴ 23፤2014-ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ትላንት ምሽት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ በሶስት የተለያዩ ርቀቶች ድል በድል ሆነዋል፡፡

አትሌቶቹ ድል የተቀዳጁት በግማሽ ማራቶን፣በማራቶንና በ1500 ሜትር ርቀት ነው፡፡

በአየርላንድ አንትሪም ግማሽ ማራቶን፡-

በወንዶች
1ኛ ጀማል ይመር፣ 59:03

4ኛ ተስፋሁን አካልነው፣ 1:01.43

በሴቶች

1ኛ ያለምዘርፍ የኋላው፣ 1:04.21

2ኛ ፀሐይ ገመቹ፣ 1:05.00

አውስትራሊያ በተደረገ ግማሽ ማራቶን፡-

በሴቶች

1ኛ በቀለች ጉደታ፣ 1:08.05

በወንዶች

2ኛ ኪሮስ አሸናፊ፣ 1:05.51

ሜክሲኮ ላይ በተካሄደ ማራቶን ፡-

በሴቶች

1ኛ አማኔ በሪሶ፣ 2:25.05

3ኛ ሙሉዬ ደቀቦ፣ 2:31.07

ጀርመን ሊቨርኩሰን በተካሄደ የ1500 ሜ ውድድር ውድድር ደግሞ :-

1ኛ ነፃነት ደስታ፣ 4:07.53

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን

https://bit.ly/3RcFdaq

#BisratNews #BisratFM #Ethiopia #Athletics

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
203 views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:28:07 ነሐሴ 22፤2014-አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

የፕሬዜዳንታዊ ምርጫው የድምፅ ቆጠራ ከደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀ ሲሆን በውጤቱም ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት በድጋሚ ተመርጠዋል።

በእጩ ተወዳዳሪነት የቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅ ሲያገኙ አቶ ቶኪቻ ዓለማየሁ 17 ድምፅ አግኝተዋል።

https://bit.ly/3ReLO4m

#BisratNews #BisratFM #Ethiopia #ኢሳያስ_ጅራ

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
277 views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:50:07
ዛሬ ነሐሴ 22፤2014-እግር ኳስን በሬድዮ ተመልከቱ በ-#እንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ #አስተንቪላ (#Aston_Villa) ከ #ዌስትሃም_ዩናይትድ (#West_Ham_United) ቀን 10:00 ሰዓት ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ ከ 9:50 ጀምሮ በቀጥታ ያስተላልፋል።

ከዚህ ጨዋታ በማስከተል #ኖቲንግሃም_ፎረስት (#Nottingham_Forest ) ከ #ቶተንሃም_ሆትስፐር (#Tottenham_Hotspur) ምሽት 12፡30 ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ ከ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ያስተላልፋል።

በመጨረሻም በ-#ፈረንሳይ_ሊግ_አንድ #ፓሪሰን_ዠርሜን #Paris_Saint_Germain) ከ #ሞናኮ (#monaco ) ምሽት 3:45 ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ ከ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ያስተላልፋል።

#AVLWHU #NFFTOT #PL #Live #ኦያያ #BisratFm

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
262 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:23:31
በ-#እንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ ዛሬ የሚደረጉ የጨዋታ መርሃ ግብሮች።

#PL

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
246 views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:41:09
ዛሬ ነሐሴ 21፤2014-በ-#እንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ #ሳውዝሃምፕተን ከ #ማንችስተር_ዩናይትድ በመላው #ዓለም በFacebook ገጻችን በቀጥታ እናስተላልፋለን።

የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ እና ሼር በማድረግ ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን ።

#SOUMUN #ኦያያ_መሴ #መሰለ_መንግስቱ #PL #Live #ኦያያ #BisratFm

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
292 views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:33:28
ዛሬ ነሐሴ 21፤2014-እግር ኳስን በሬድዮ ተመልከቱ በ-#እንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ #ሳውዝሃምፕተን (#Southampton) ከ #ማንችስተር_ዩናይትድ (#Manchester_United) ቀን 8:30 ሰዓት ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ ከ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ያስተላልፋል።

ከዚህ ጨዋታ በማስከተል #ማንችስተር_ሲቲ (#Manchester_City ) ከ #ክሪስታል_ፓላስ (#Crystal_Palace) ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ ከ 10:30 ጀምሮ በቀጥታ ያስተላልፋል።

በማስከተልም #አርሰናል (#Arsenal ) ከ #ፉልሃም (#Fulham) ምሽት 1፡30 ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ ከ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ያስተላልፋል።

በመጨረሻም በ-#ጣልያን_ሴሪ_ኤ #ኤሲ_ሚላን (#AC_Milan) ከ #ቦሎኛ (#Bologna) ምሽት 3:45 ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ ከ 3:30 ጀምሮ በቀጥታ ያስተላልፋል።

#SOUMUN #MCICRY #ARSFUL #PL #Live #ኦያያ #BisratFm

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
261 views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:52:44 ሰኔ 30፣2014-ከስራ እለቃለው ባሉት የእንግሊዝ ጠ/ሚ ምትክ ፓርቲያቸው ሰው እስኪሾም ድረስ ጆንሰን በስልጣን ላይ ይቆያሉ

የቦሪስ ጆንሰን አስተዳደር ቁልፍ ሚኒስትሮችን እና ሌሎች ባለስልጣናት ከስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ በተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ መነሳያቸውን ገልፀዋል። በምትካቸው ፓርቲያቸው ሰው እስኪመረጥ ድረስ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሆነው እንደሚቆይ ተናግረዋል።

ከስራ የመልቀቂያ ማዕበል ማክሰኞ እለት የጀመረ ሲሆን መነሻው የቀድሞ የአርብቶ አደር ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት ክሪስ ፒንቸር የፆታዊ ብልግና ቅሬታዎች ከቀረቡ በኋላ ነው። ጆንሰን ይቅርተ በመጠየቅ በመንግስት ስራ ውስጥ የማይመች መሆኑን ባለማወቅ የተሰራ ስህተት ነው ማለታቸው ይታወሳል።

በዚህ ቅሌት ምክንያት ስራቸውን እንደለቀቁ የሚናገሩት የእንግሊዝ መንግስት ከፍተኛ ሚኒስትሮች ጆንሰን የሀገሪቱ ብሄራዊ ጥቅም ማስተዳደር ላይ ባላቸው አቅም እምነት አጥተናል ብለዋል።የ58 አመቱ ጠ/ሚ ጆንሰን በስልጣን ላይ እያሉ ያለውን ውዝግብ ለመፍታት ወራት ቢፈጅባቸውም ውጤት አላስገኘም።


በኤተን እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተማሩት ጆንሰን የፓርላማ አባል ሆነው የፖለቲካ ህይወት ከመጀመራቸው በፊት በቀኝ ክንፍ መጽሔቶች እና ጋዜጦች ላይ ዘጋቢ እና ጸሐፊ ሆነው ሰርተዋል። በኋላም ላይም የለንደን ከንቲባ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል።

በስምኦን ደረጄ

https://bit.ly/3nN2lzy


#BisratNews #BisratFm

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
67 viewsedited  12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:19:10 ሰኔ 30፣2014-የ2015 በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫዎች ፦
1. ብድር መቀነስ
2. የበጀት ጉድለት መቀነስ
3. ያለንን ሀብት በቁጠባ መጠቀም
4. የዋጋ ንረትን ማረጋጋት ነው

ባለፉት ሁለት ሶስት አመታት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ባይሰራ ኑሮ ከአሁኑ የባሰ ችግር ያጋጥመን ነበር። አሁንም ይህንን ለመቆጣጠር እየስራን ነው። የመጀመርያው ጥብቅ የገንዘብ አስተዳደር መጠቀም ነው። ሁለተኛው ምርታማነትን ማሳደግ ነው። በግብርና የጀመርነውን አስደማሚ ስራ ማስቀጠል ነው። ሌላው ፕሮጀክቶችን በጊዜ ማጠናቀቅ ነው።

5.መልሶ ማቋቋም እና ሰብአዊ እርዳታ ነው
6. የሀገር ደህንነት እና ሰላምን ማስጠበቅ ነው

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

https://bit.ly/3yKC0bR

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
69 views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:52:19 ሰኔ 30፣2014-በሚቀጥለዉ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች በወቅቱ ካልደረሱ ሌሎች ምርጫዎችን መንግስት ይከተላል-ጠ/ሚ አብይ

በ 2015 ዓ.ም የሚሰጠዉ ሀገር አቀፍ ፈተናን ዲጂታል በሆነ መንገድ በኦንላይን ምዘናዉን ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል። ለዚህም 1ሚሊዮን የሚሆኑ ታብሌት ኮምፒውተሮች ወደ ሀገር ይገባሉ ተብሎም ነበር።

በዛሬዉ እለት እየተካሄደ በሚገኘው 6ኛዉ የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለ ጠ/ሚ አብይ ከአባላቱ ከቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች መካከል ታብሌት ኮምፕዩተሮቹን ወደ ሀገር የማስገባቱ ስራ መስተጓጎሉ ነበር።

ጠ/ሚ አብይ ይህን በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ ያለዉን ስርቆት ለማስቀረት ሲባል ፈተናዉን ዲጂታላይዝ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም 1ሚሊዮን ታብሌት ኮምፕዩተሮቹን ከቻይና መንግስት ጋር በመሆን ለማስገባት እየተሰራ እንደነበር አስታዉሰዋል። ሆኖም በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያትም አምራች ድርጅቱ ስራዉን በተያዘለት ግዜ ማጠናቀቅ አለመቻሉን አስታዉቀዋል።

በ 2015 ለመስጠት የታቀደዉ ፈተናዉ ፤ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ ታብሌት ኮምፒውተሮቹ በተያዘላቸዉ ግዜ ከደረሱ ፈተናዉ ይሰጣል ማለታቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል። ሆኖም ታብሌቶቹ በግዜዉ ካልደረሱ መንግሰት ሌሎች ምርጫዎችን እንደሚጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

በበረከት ሞገስ

https://bit.ly/3RjjKh5

#BisratNews #BisratFm #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv
69 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ