Get Mystery Box with random crypto!

BBC አማርኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amaric — BBC አማርኛ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amaric — BBC አማርኛ
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amaric
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.65K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━
WELL COME
ቢቢሲ አማርኛ 🇪🇹
━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━
Verified official channel ®
@BBC_Amaric
https://t.me/joinchat/AAAAAE7S0z4ya9Z6ragluA

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 21:34:28
ሰበርመረጃ!!

የኢትዮጵያ መከላከያ ቆቦን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል።

በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል።

@bbc_amharic1
395 views , 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:38:09
የሸኔ ታጣቂ በአፋር ክልል በከፈተው አዲስ ጥቃት ንጹሐንን እየገደለ መሆኑ ተሰማ!

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ቡድን በአፋር ክልል ቡርቃ ከተማ አዲስ የጥቃት ዘመቻ መጀመሩንና ንጹሐን ሰዎች እየተገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

የአዲስ ማለዳ ምንጮች በገለጹት መሠረት፤ ሸኔ ጥቃቱን የከፈተው ባሳለፍነው ነሐሴ 18/2014 ነው። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ የቡርቃ ከተማ ነዋሪዎች እየተገደሉ ነው ያሉት ምንጮች፤ ‹‹ድሮም ከሕወሓት ጋር ጥብቅ ትስስር አለው። አሁንም ጥቃቱን በተመሳሳይ ጊዜ ከፍተዋል።›› ሲሉ ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://bit.ly/3dP5qNS

@bbc_amharic1
635 views , 12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:37:55
"አሸባሪው ህወሓት ካለፈው ስህተቱ የማይማር እና ጦርነት ብቻ ናፋቂ መሆኑን ከሚፈፅመው ድርጊት መገንዘብ ይቻላል" -የመከላከያ ሚኒስቴር

አሸባሪው ህወሓት ካለፈው ስህተቱ የማይማር እና ጦርነት ብቻ ናፋቂ መሆኑን ከሚፈፅመው ድርጊት መገንዘብ ይቻላል ሲል የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በህዝብ ጉያ ተሸጉጦ ወጣቶችን ወደ ጦርነት እየማገደ ያለው አሸባሪው ህወሓት ከሠላም ይልቅ ጦርነትን እንደሚመርጥ በቅርቡ በከፈተብን ጦርነት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

የፌዴራል መንግስት ለሠላም የዘረጋውን የሠላም አማራጮች አሸባሪው የህወሃት ቡድን ወደ ጎን ትቶ በበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ ተጠቃሁ በማለት ወጣቶችን እየቀሰቀሰ በጦርነት እያስፈጃቸው ይገኛል ሲልም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ፀብ አጫሪነት፣ ቅጥፈት እና የሐሰት ፕሮፖጋንዳ የአሸባሪው ህወሓት ተፈጥሯዊ ባህሪው ነው። ትላንት የተናገረውን ዛሬ የማይደግመው ይህ የሽብር ቡድን በትግራይ የሚኖሩ ዜጎችን በሠላም የመኖር መብታቸውን ነፍጓልም ብሏል።

የሽብር ቡድኑ መንግስት ያደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ለጦርነት ሲዘጋጅ መቆየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ከሠሞኑም አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለተቸገሩ የትግራይ ወገኖቻችንን የምግብ እርዳታ የሚያደርሡበትን ነዳጅ ዘርፎ ለጦርነት መውሠዱ ለትግራይ ህዝብ ያለው ጥላቻና ንቀት ማሳያ ነው ማለቱንም ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@bbc_amharic1
640 views , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:37:55
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ!

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ  በቀን እና በማታ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 ሺሕ 515 ተማሪዎች አስመርቋል።ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺሕ 910፣ በሁለተኛ ዲግሪ 1 ሺሕ 597 እንዲሁም በሶስተኛ ዲግሪ 69 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ተመራቂዎቹ 4ሺሕ 613 ወንድ እና 1ሺሕ 902 ሴት ተማሪዎች ናቸው።

በተጨማሪም ዩኒቨርስቲው በአባትነታቸው የሚያስተምሩ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ የሚወዱ በችግር ግዜ ለወገን ዘብ ለቆሙት አርዓያ ሰብ የሆኑትን ለብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያስቻለችው ሀገር ወዳድዋ ኢትዮጵያዊት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የዛሬ ምሩቃን የኢትዮጵያን ሸክም የሚያቀሉ ለሀገር ሰላም እና ልማት የሚተጉ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።ዩኒቨርሲቲው 60 አመታትን ባስቆጠረው የመማር ማስተማር ሂደት በኢትዮጵያ ካሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት ጥራት በግምባር ቀደምትነት ከሚነሱት ተቋማት እንደሚጠቀስም ገልፀዋል። 

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ፣ የኢንዶኔዚያ አምባሳደር እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  የተገኝተዋል። በ1955 ዓ.ም የተመሰረተው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን አመታት ብቁ ዜጋን በማፍራት ኃላፊነቱን ሲወጣ እንደነበር ተጠቅሷል።

@bbc_amharic1
536 views , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:37:55
በኢትዮጵያ 7 ትሪሊዮን ኪዪቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ!!!

በኢትዮጵያ በኦጋዴን አካባቢ 7 ትሪሊዮን ኪዪቢክ ጫማ (200 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ደገማ) የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ የሚያረጋግጥ ጥናት ይፋ ተደርጓል።

የማዕድን ሚንስቴር ከአሜሪካው ኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሲሼየትስ ኢንክ ኩባንያ (ኤልሲኤአይ) የጥናት ተቋም ጋር በመተባበር ያስጠናውን የነዳጅ ክምችት ጥናት ይፋ አድርጓል።

በዚህ መርሀ ግብር ላይ እንደተጠቀሰው ኢትዮጵያ በኦጋዴን ተፋሰስ 7 ትሪሊየን ጫማ ጥልቀት ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት እንዳላት በጥናቱ ተረጋግጧል ተብሏል። የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ( ኢ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት ጥናቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን የመደራደር አቅም ያሳድገዋል ብለዋል።

“ከዚህ ቀደም የነበሩ ኩባንዎች ምን ያህል ክምችት እንዳለን አይነግሩንም ነበር” ያሉት ሚኒስትሩ አሁን የተጠናው ጥናት ግን ለክምችቱ መጠን ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም የነዳጅ ሀብት መጠናችን በዚህ ጥናት መረጋገጡ በተስፋ ብቻ ሲነገረን የነበረው ነገር ወደ እውነትነት እንዲቀየር ያደርጋልም ሲሉ ሚንስትሩ አክለዋል።

ይህ የነዳጅ ሀብት የአዋጭነት ጥናት ለአራት ወራት የተካሄደ ሲሆን ጥናቱ ኢትዮጵያ በተለምዶ ከሚባለው በትክክል ያላት የተፈጥሮ ነዳጅ መጠን ምን ያህል እንደሆነ የሚያሳይ እንደሆነም በጥናቱ ርክክብ ወቅት ተገልጿል።የጥናቱን ውጤት ይፋ በማድረጉ እና የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተሉያዩ ተቋማት ሚኒስትሮችን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮችም ተገኝተዋል።

(አልአይን)
@bbc_amharic1
475 views , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:37:55
በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመቶ ስለወደቀው አውሮፕላን የአየር ሀይል አዛዥ ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ የሰጡት ተጨማሪ መረጃ!!

ከቀናት በፊት በተከለከለ የበረራ አቅጣጫ ከፍታና ወደ ኢትዮጵያ የአየር ክልል መስመር ጥሶ የገባ አውሮፕላን የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ትእዛዝ ባለመቀበሉ በኢትዮጵያ አየር ሃይል ተመቶ መውደቁ መገለፁ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት:-

አይነቱ:- የቀድሞ ሶቭየት ህብረት ስሪት አንቶኖቭ 26

የመጫን አቅም:- 5 ቶን እና 40 ወታደሮችን ከነትጥቃቸው የሚይዝ

አጠቃላይ ክብደት:- 24 ሺ ኪሎ ግራም

ንብረትነቱ :- "የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት መሆኑ የታመነበት" በሚል ተጠቁሟል።

የተመታበት ሰአት:- ምሽት 3:30 መሆኑን የኢፌድሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌ/ጀ ይልማ መርዳሳ አሳውቀዋል።

@bbc_amharic1
430 views , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:37:55
በመቀለ ከተማ ላይ ተፈፀመ በተባለ የአውሮፕላን ጥቃት 4 ሰዎች መገደላቸውን እና በጥቃቱ ሌሎች 9 ሰዎች መጎዳታቸውን የዓይን እማኞች እና የሆስፒታል ምንጮች መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አየር ኃይል በትግራይ «ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ» ጥቃት መፈፀሙን አስታወቋል።

በሰላማዊ ሰዎች መኖርያ አካባቢ ተፈፅሟል ተብሎ በትግራይ አማፅያን የቀረበበትን ክስም ዉድቅ አድርጓል።

@bbc_amharic1
410 views , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:37:55
ፌደራል ፖሊስ ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ መሰማራቱን ገለጸ!

የፌዴራል ፖሊስ በአዲስ መንፈስ በበለጠ ተነሳችነትና አንድነት ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ መሰማራቱን ገለጸ፡፡

ተቋሙ የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን በ2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የተቋሙ አመራርና አባላት የሀገርን ደህንነትና የዜጎችን ሰላም በጀግንነት በማስጠበቅ ረገድ ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት የሽብር ቡድኖችን የጥፋት መረብ በመበጣጠስ እና ሴራቸውንም በማክሸፍ መስዋዕትነት ጭምር እየከፈሉ ሀገራዊ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ፖሊሳዊ ተልዕኮውን በታላቅ ጀግንነት መወጣታቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ገልፀዋል።

በሽብርተኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት በውይይቱ በአጽንኦት መነሳቱን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡የተቋሙ አመራርና አባላት በ2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረጉ በኋላ ዕቅዱን በማፅደቅ በአዲስ መንፈስ በበለጠ ተነሳችነትና አንድነት ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ መሰማራታቸው ተገልጿል፡፡

@bbc_amharic1
516 views , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:11:40
ሰበር መረጃ!!

መንግሥት የተመረጡ የጁንታው ወታደራዊ ዐቅሞች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ጁንታው ጥቃቱን ቀጥሎበታል። በመኾኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለጁንታው ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ ይወስዳል።

ስለኮነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል።

@bbc_amharic1
754 views , 15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:11:39
ህወሃት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ናፍታ እና ቤንዚን ሊያቀብል የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።

መነሻውን ከሰመራ ያደረገ ኮድ 3 ታርጋ ቁጥር A47679 አይሱዙ ተሽከርካሪ መዳረሻውን ወደ ህወሓት ቡድን በማድረግ 3000 /ሦስት ሺህ/ ሊትር ናፍጣ እና 2000 /ሁለት ሺህ/ ቤንዚል ካልዋን ላይ ሲደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኙት መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት ህወሓት በሀገራችን ላይ ጦርነት ቢከፍትም በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን አፀፋዊ ምላሽ እየተሠጠ ባለበት ወቅት በህገ ወጥ መንገድ ለጠላት ሊደርስ የነበረን ነዳጅ መቆጣጠር ችለናል ብለዋል።

መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ አክለውም በቀጣይም ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን በህገወጥ መንገድ ሊደርስ የሚችል ማንኛውም ነገር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

[FDRE Defense Force]
@bbc_amharic1
677 views , 15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ