Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 7 ትሪሊዮን ኪዪቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ!!! በኢትዮጵያ በኦጋዴ | BBC አማርኛ

በኢትዮጵያ 7 ትሪሊዮን ኪዪቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ!!!

በኢትዮጵያ በኦጋዴን አካባቢ 7 ትሪሊዮን ኪዪቢክ ጫማ (200 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ደገማ) የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ የሚያረጋግጥ ጥናት ይፋ ተደርጓል።

የማዕድን ሚንስቴር ከአሜሪካው ኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሲሼየትስ ኢንክ ኩባንያ (ኤልሲኤአይ) የጥናት ተቋም ጋር በመተባበር ያስጠናውን የነዳጅ ክምችት ጥናት ይፋ አድርጓል።

በዚህ መርሀ ግብር ላይ እንደተጠቀሰው ኢትዮጵያ በኦጋዴን ተፋሰስ 7 ትሪሊየን ጫማ ጥልቀት ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት እንዳላት በጥናቱ ተረጋግጧል ተብሏል። የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ( ኢ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት ጥናቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን የመደራደር አቅም ያሳድገዋል ብለዋል።

“ከዚህ ቀደም የነበሩ ኩባንዎች ምን ያህል ክምችት እንዳለን አይነግሩንም ነበር” ያሉት ሚኒስትሩ አሁን የተጠናው ጥናት ግን ለክምችቱ መጠን ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም የነዳጅ ሀብት መጠናችን በዚህ ጥናት መረጋገጡ በተስፋ ብቻ ሲነገረን የነበረው ነገር ወደ እውነትነት እንዲቀየር ያደርጋልም ሲሉ ሚንስትሩ አክለዋል።

ይህ የነዳጅ ሀብት የአዋጭነት ጥናት ለአራት ወራት የተካሄደ ሲሆን ጥናቱ ኢትዮጵያ በተለምዶ ከሚባለው በትክክል ያላት የተፈጥሮ ነዳጅ መጠን ምን ያህል እንደሆነ የሚያሳይ እንደሆነም በጥናቱ ርክክብ ወቅት ተገልጿል።የጥናቱን ውጤት ይፋ በማድረጉ እና የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተሉያዩ ተቋማት ሚኒስትሮችን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮችም ተገኝተዋል።

(አልአይን)
@bbc_amharic1