Get Mystery Box with random crypto!

'አሸባሪው ህወሓት ካለፈው ስህተቱ የማይማር እና ጦርነት ብቻ ናፋቂ መሆኑን ከሚፈፅመው ድርጊት መገ | BBC አማርኛ

"አሸባሪው ህወሓት ካለፈው ስህተቱ የማይማር እና ጦርነት ብቻ ናፋቂ መሆኑን ከሚፈፅመው ድርጊት መገንዘብ ይቻላል" -የመከላከያ ሚኒስቴር

አሸባሪው ህወሓት ካለፈው ስህተቱ የማይማር እና ጦርነት ብቻ ናፋቂ መሆኑን ከሚፈፅመው ድርጊት መገንዘብ ይቻላል ሲል የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በህዝብ ጉያ ተሸጉጦ ወጣቶችን ወደ ጦርነት እየማገደ ያለው አሸባሪው ህወሓት ከሠላም ይልቅ ጦርነትን እንደሚመርጥ በቅርቡ በከፈተብን ጦርነት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

የፌዴራል መንግስት ለሠላም የዘረጋውን የሠላም አማራጮች አሸባሪው የህወሃት ቡድን ወደ ጎን ትቶ በበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ ተጠቃሁ በማለት ወጣቶችን እየቀሰቀሰ በጦርነት እያስፈጃቸው ይገኛል ሲልም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ፀብ አጫሪነት፣ ቅጥፈት እና የሐሰት ፕሮፖጋንዳ የአሸባሪው ህወሓት ተፈጥሯዊ ባህሪው ነው። ትላንት የተናገረውን ዛሬ የማይደግመው ይህ የሽብር ቡድን በትግራይ የሚኖሩ ዜጎችን በሠላም የመኖር መብታቸውን ነፍጓልም ብሏል።

የሽብር ቡድኑ መንግስት ያደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ለጦርነት ሲዘጋጅ መቆየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ከሠሞኑም አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለተቸገሩ የትግራይ ወገኖቻችንን የምግብ እርዳታ የሚያደርሡበትን ነዳጅ ዘርፎ ለጦርነት መውሠዱ ለትግራይ ህዝብ ያለው ጥላቻና ንቀት ማሳያ ነው ማለቱንም ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@bbc_amharic1