Get Mystery Box with random crypto!

አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam

የቴሌግራም ቻናል አርማ arayanews — አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam
የቴሌግራም ቻናል አርማ arayanews — አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam
የሰርጥ አድራሻ: @arayanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.86K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች🇪🇹

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-21 18:22:57
እስራኤል ለእርሻ ምቹ የሆነ 6ሺ ኪ.ሜ ስኩዌር መሬት አላት፤ በተቃራኒው ኢትዮጵያ 379ሺ ኪ.ሜ ስኩዌር መታረስ ሚችል መሬት አላት ። ነገር ግን ..እስራኤል በግብርና ምርት በአመት 9.5 ቢሊዪን ዶላር ታገኛለች ። የግብርና ምርት በእስራኤል ኤክስፖርት ገቢ በማስገኘት ደረጃ ስምንተኛ ደረጃን የያዘ ነው ። አጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 22,145 km2 ነው ።ይህ ማለት የኢትዮጵያን 2% ብቻ ነው ። ከዚህም መሬቷ ላይ ከግማሽ በላይ በረሃ ነው ።

ጂኦግራፊው ለግብርና ምቹ አይደለም ። 20 በመቶ ብቻ ነው ለግብርና የሚመቸው ። ይህም 433 ,000 ሄክታር ያህል ነው ።
በግብርና ስራ ላይ የተሰማራ የሰው ኃይል ብዛቷ 3.7 በመቶው ብቻ ነው ።
አመታዊ የዝናብ መጠን ደግሞ ይገርማል ከ30.5 - 889 ሚሜ ነው ።

በአንፃሩ ኢትዮጵያ ደግሞ በግብርና ምርት በአመት 2.53 ቢሊዩን ዶላር ብቻ ታገኛለች ። የግብርና ምርት በኢትዮጵያ ኤክስፖርት ገቢ በማስገኘት ደረጃ ደግሞ አንደኛ ነው ። አጠቃላይ የቆዳ ስፋታችን 1,104,300 km2 ነው ። እስራኤል የዚህን 2% በመቶ ብቻ ናት ።

ኢትዮጵያ ከ51.3 ሚሊየን ሄክታር በለይ ለእርሻ ምቹ መሬት አላት።ከዚህ ውስጥ 16, 187 ,000 ሄክታር እየታረሰ ነው ።
70 በመቶ ያህሉ የሰው ኃይል ግብርና ላይ ተሰማርቷል ።
አመታዊ የዝናብ መጠናችን ከ1000 - 2200 ሚሊ ሜትር ይደርሳል ።

ያለውን ልዮነት ለመገንዘብ ሰንጠረዡን ይመልከቱ

ታድያ በዚያች ሚጢጢ መሬት በጥቂት የሰው ኃይል በማይመች መሬት በዝቅተኛ ዝናብ መጠን የምታመርተው ምርት እንዴት የራሷን 95 በመቶ ምግብ ሸፍና ወደ ውጭ በመላክ ከኢትዮጵያ በሦስት እጥፍ ገቢ ታገኛለች ? ምናቧቷን ሸጣ ነው ? እውቀት አይደለምን ቴክኖሎጂን አይደለምን ?
23.5K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-20 21:58:02
አሁናዊ የዋጋ መናር ችግርን ለመከላከል ምን መደረግ አለበት ?

(ክቡር ገና - ለኢፕድ ከሰጡት ቃል)

- አስመጪዎቹ ማን እንደሆኑ ይታወቃሉ ፤ ስለዚህ መጋዘናቸው ውስጥ ምርቱ አለ ወይስ የለም ? የት አደረሱት የሚለውን መንግስት መከታተል አለበት። ኅብረተሰቡም ዋነኛ ተባባሪ በመሆን ሥራውን ሊተባበር ይገባል።

- ህብረተሰቡ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሕገወጥነት ሲከሰት ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ይገባዋል።

- መንግሥትም ከመጠን በላይ ያከማቹትን መለየት አለበት ከዚህ ባለፈ ተፈላጊ ምርቶች የሚባሉትን በመለየት በብዛት ወደገበያው እንዲቀርቡ ማድረግ ይኖርበታል። ይህም ፋብሪካዎች ምርታቸውን እንዲጨምሩ ማድረግ።

- ከውጭ የሚመጣውንና በጣም አስፈላጊ ነው የሚባል ምርትን መንግሥት እራሱ አስገብቶ እንዲከፋፈል በማድረግ ችግሩን መቀነስ ይቻላል።

- መንግሥት በእራሱ ድርጅቶች በኩል ዋና ዋና ምርቶችን በማስመጣት የዋጋ መናርን ለማቀዛቀዝ ይችላል።

- መንግሥት ሁሉን ነገር ክፍት አድርጎ ጫናውን ሊቋቋመው ስለማይችል ሁኔታው እስኪረጋጋ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በዋና ዋና ምርቶች ላይ ከዚህ ዋጋ በላይ መሸጥ አይቻልም የሚል እቀባን ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባታል።

- ምርት ያቆሙና የቀነሱ ፋብሪካዎችን በመደገፍ በብዛት እንዲያመርቱ ማድረግ የምርት እጥረትን ሆነ የዋጋ መናርን ይከላከላል። ይህ ምርት የደበቁ አውጥተው እንዲሸጡ እና በገበያ ውድድር ውስጥ እንዲገቡ ያስገድዳቸዋል።

- መንግሥት በሚያምናቸው ነጋዴዎች አማካኝነት በተለየ ሁኔታ ምርቶች ወደአገር ውስጥ የሚገቡበትን መንገድ ማመቻቸት ይችላል። በዚህ ወቅት ምርት ደብቀው እና አሽገው ያስቀመጡ ግለሰቦችም እንዳይከስሩ በማሰብ ወደገበያ የሚያወጡበት አጋጣሚ ይፈጠራል።
28.8K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-17 19:44:05
አሸባሪው ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ የፈፀማቸውን የበቀል እርምጃዎች ቴሌግራፍ በዜናው በዝርዝር ሰርቷቸዋል። ቪዲዮው ከቴሌግራፍ ዜና ተቀንጭቦ የተሰራ ነው።

1) የእርሻ ቦታዎችን አጥቅቷል። አበላሽቷል። ገበሬዎች እንዳያርሱ አድርጓል።

2) ቤት ለቤት እየዞረ ንፁሃንን ገድሏል

3) የገበሬውን ቤት አቃጥሏል

4) ዘርፏል

5) ሰፈሮችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

6) እስከ 700 ሺህ የሚደርስ ሕዝብን አፈናቅሏል።

ይህን ሁሉ እያደረገ ያለው ገና ወረራ ላይ እያለ ነው። ቢቀናው ምን ሊያደርግ እንደሚችል ውድመቱን መገመት ያዳግታል።
21.4K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-17 19:25:53
ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፣አቶ ጌታቸው አሰፋ፣አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 41 ተከሳሾችን ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ጋር በመተባበር ለህግ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ አስተላለፈ።

በሽብር ወንጀል ክስ ከተመሰረተባቸው 62 ተከሳሾች ውስጥ 21ዱ ፍርድ ቤት ቀርበው የተከሰሱበት ክስ በንባብ ቀርቦላቸዋል።

ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት ውስጥ ለ19ኙ ተከሳሾች ክሱ ከዚህ ቀደም በፅሁፍ በእጃቸው እንዲደርሳቸው መደረጉ የተገለጸ ሲሆን ÷ ለሁለቱ ተከሳሾች ደግሞ ዛሬ ክሱ ደርሷቸዋል።
18.4K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ