Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል ለእርሻ ምቹ የሆነ 6ሺ ኪ.ሜ ስኩዌር መሬት አላት፤ በተቃራኒው ኢትዮጵያ 379ሺ ኪ.ሜ | አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam

እስራኤል ለእርሻ ምቹ የሆነ 6ሺ ኪ.ሜ ስኩዌር መሬት አላት፤ በተቃራኒው ኢትዮጵያ 379ሺ ኪ.ሜ ስኩዌር መታረስ ሚችል መሬት አላት ። ነገር ግን ..እስራኤል በግብርና ምርት በአመት 9.5 ቢሊዪን ዶላር ታገኛለች ። የግብርና ምርት በእስራኤል ኤክስፖርት ገቢ በማስገኘት ደረጃ ስምንተኛ ደረጃን የያዘ ነው ። አጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 22,145 km2 ነው ።ይህ ማለት የኢትዮጵያን 2% ብቻ ነው ። ከዚህም መሬቷ ላይ ከግማሽ በላይ በረሃ ነው ።

ጂኦግራፊው ለግብርና ምቹ አይደለም ። 20 በመቶ ብቻ ነው ለግብርና የሚመቸው ። ይህም 433 ,000 ሄክታር ያህል ነው ።
በግብርና ስራ ላይ የተሰማራ የሰው ኃይል ብዛቷ 3.7 በመቶው ብቻ ነው ።
አመታዊ የዝናብ መጠን ደግሞ ይገርማል ከ30.5 - 889 ሚሜ ነው ።

በአንፃሩ ኢትዮጵያ ደግሞ በግብርና ምርት በአመት 2.53 ቢሊዩን ዶላር ብቻ ታገኛለች ። የግብርና ምርት በኢትዮጵያ ኤክስፖርት ገቢ በማስገኘት ደረጃ ደግሞ አንደኛ ነው ። አጠቃላይ የቆዳ ስፋታችን 1,104,300 km2 ነው ። እስራኤል የዚህን 2% በመቶ ብቻ ናት ።

ኢትዮጵያ ከ51.3 ሚሊየን ሄክታር በለይ ለእርሻ ምቹ መሬት አላት።ከዚህ ውስጥ 16, 187 ,000 ሄክታር እየታረሰ ነው ።
70 በመቶ ያህሉ የሰው ኃይል ግብርና ላይ ተሰማርቷል ።
አመታዊ የዝናብ መጠናችን ከ1000 - 2200 ሚሊ ሜትር ይደርሳል ።

ያለውን ልዮነት ለመገንዘብ ሰንጠረዡን ይመልከቱ

ታድያ በዚያች ሚጢጢ መሬት በጥቂት የሰው ኃይል በማይመች መሬት በዝቅተኛ ዝናብ መጠን የምታመርተው ምርት እንዴት የራሷን 95 በመቶ ምግብ ሸፍና ወደ ውጭ በመላክ ከኢትዮጵያ በሦስት እጥፍ ገቢ ታገኛለች ? ምናቧቷን ሸጣ ነው ? እውቀት አይደለምን ቴክኖሎጂን አይደለምን ?