Get Mystery Box with random crypto!

አሁናዊ የዋጋ መናር ችግርን ለመከላከል ምን መደረግ አለበት ? (ክቡር ገና - ለኢፕድ ከሰጡት ቃ | አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam

አሁናዊ የዋጋ መናር ችግርን ለመከላከል ምን መደረግ አለበት ?

(ክቡር ገና - ለኢፕድ ከሰጡት ቃል)

- አስመጪዎቹ ማን እንደሆኑ ይታወቃሉ ፤ ስለዚህ መጋዘናቸው ውስጥ ምርቱ አለ ወይስ የለም ? የት አደረሱት የሚለውን መንግስት መከታተል አለበት። ኅብረተሰቡም ዋነኛ ተባባሪ በመሆን ሥራውን ሊተባበር ይገባል።

- ህብረተሰቡ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሕገወጥነት ሲከሰት ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ይገባዋል።

- መንግሥትም ከመጠን በላይ ያከማቹትን መለየት አለበት ከዚህ ባለፈ ተፈላጊ ምርቶች የሚባሉትን በመለየት በብዛት ወደገበያው እንዲቀርቡ ማድረግ ይኖርበታል። ይህም ፋብሪካዎች ምርታቸውን እንዲጨምሩ ማድረግ።

- ከውጭ የሚመጣውንና በጣም አስፈላጊ ነው የሚባል ምርትን መንግሥት እራሱ አስገብቶ እንዲከፋፈል በማድረግ ችግሩን መቀነስ ይቻላል።

- መንግሥት በእራሱ ድርጅቶች በኩል ዋና ዋና ምርቶችን በማስመጣት የዋጋ መናርን ለማቀዛቀዝ ይችላል።

- መንግሥት ሁሉን ነገር ክፍት አድርጎ ጫናውን ሊቋቋመው ስለማይችል ሁኔታው እስኪረጋጋ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በዋና ዋና ምርቶች ላይ ከዚህ ዋጋ በላይ መሸጥ አይቻልም የሚል እቀባን ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባታል።

- ምርት ያቆሙና የቀነሱ ፋብሪካዎችን በመደገፍ በብዛት እንዲያመርቱ ማድረግ የምርት እጥረትን ሆነ የዋጋ መናርን ይከላከላል። ይህ ምርት የደበቁ አውጥተው እንዲሸጡ እና በገበያ ውድድር ውስጥ እንዲገቡ ያስገድዳቸዋል።

- መንግሥት በሚያምናቸው ነጋዴዎች አማካኝነት በተለየ ሁኔታ ምርቶች ወደአገር ውስጥ የሚገቡበትን መንገድ ማመቻቸት ይችላል። በዚህ ወቅት ምርት ደብቀው እና አሽገው ያስቀመጡ ግለሰቦችም እንዳይከስሩ በማሰብ ወደገበያ የሚያወጡበት አጋጣሚ ይፈጠራል።