Get Mystery Box with random crypto!

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicsuccession — የጥያቄዎቻችሁ መልስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicsuccession — የጥያቄዎቻችሁ መልስ
የሰርጥ አድራሻ: @apostolicsuccession
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.61K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ኦርቶዶክሳዊ ገጽ ዋና ዓላማ የወጣቱን ጥያቄ መመለስ ነው። ወጣቶች ማንኛውም በሕይወታቸው የገጠማቸውንም ይሁን መንፈሳዊ ጥያቄ በሚረዱት መልክ መልስ ይሰጥበታል
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCPLJimNlqTFBnlbsh_vccgg
ለጥያቄዎችና ለአስተያየቶች
@AbuNak
@Rhripsime

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-11-20 17:41:47 ‹ክርስቶስ ከሶቅራጥስ ጋር በምስስል ሲነጻጸር›

◉የሁለተኛው መቶ ዘመን ክርስቲያን ዐቃቤ እምነትና ፈላስፋ የነበረው ሰማዕቱ ዮስጢኖስ በአንድ ወቅት ይህን ተናግሯል።ከጥንቶቹ ግሪካውያን ፈላስፎች መካከል በአመክንዮ ይኖሩ ከነበሩት አሳቢያን እንዲያውም፣ በሃሳብ በማንሰላሰል፣ በአንዳንድ ሃሳቦቻቸው ክርስቲያን-መሰል አመለካከት(outlook) ፣እምነትና እይታ ያስተጋቡ ነበር። ዮስጢኖስ ፈላስፋ ሶቅራጥስን በስም እየጠቆመ፦
‛ሶቅራጥስ በእውነቱ ስለ ክርስቶስ(logos) በማንሰላሰል ከፊል እውቀት ነበረው’ እስከማለት ደርሶ ነበር።
አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሶቅራጥስ፣አፍላጦን እና አርስጣጣሊስ “ደጋግ አረማውያን” ብለው ይጠሩአቸዋል። ሶቅራጥስን የክርስቶስ ጥላዊ ምሳሌ አድርገው የሚመለከቱም ነበሩ። ከነዚህም አበው መካከል ሰማዕቱ ዮስጢኖስ በsecond apology መጽሐፉ(እዚህ ጽሑፍ ላይ ወደአማርኛ ለመመለስ ተሞክሯል።) እንዲህ ብሏል፦

[ ‹‹እንግዲህ አስተምሕሮቻችን ከሰው ትምህርት ሁሉ የሚበልጡ ኹነው ይታያሉ። ምክንያቱም ስለ እኛ የተገለጠው ክርስቶስ፥ ምሉዕ ምኩነ-ሰባዊ ኋኝ (the whole rational being)፣ ሥጋም ፣አእምሮም ፣ ነፍስም ሆነ። እኔ ሕግ ሰጪዎችም ሆኑ ፈላስፎች በደንብ የተናገርኩትን ያህል፥አንዳች የተወሰነ ክፍለ-ቃል በማግኘትና በማሰላሰል አብራርተዋል። ነገር ግን ምሉዕ ቃል'ን ማለትም ክርስቶስን ስለማያውቁ፣ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ይቃወማሉ።
___
በሰዋዊ ውልደት ከክርስቶስ በፊት የቀደሙት ደግሞ ነገሮችን በአመክንዮ ለማየትና ለማረጋገጥ ሲሞክሩ እንደ እምነት የለሽ ሰዎችና ጣልቃገብ ባተሌዎች ተደርገው ወደ ፍርድ ቀረቡ። እና ከሁሉም በላይ በዚህ አቅጣጫ ቀናተኛ የነበረው ሶቅራጥስ ከራሳችን(ከክርስቶስ) ጋር እጅግ ተመሳሳይ በሆነ ወንጀል ተከሷል። አዳዲስ አማልክትን እያስተዋወቀ ነው ብለው ነበርና፥ መንግሥትም ያወቃቸውን፣እውቅናም የሰጣቸውን አማልክት አድርጎ አይቆጥራቸውም ነበርና። ነገር ግን ሆሜርን እና የቀሩት ክቱል ባለቅኔዎችን ከሀገሩ አስወጣ፣እና ሰዎች ክፉ መናፍስትን እና ገጣሚዎቹ የሚናገሩትን፥ኾነ የሚያደርጉትን ነገር እንዲክዱ አስተማሯቸዋል፤
‛የሁሉንም አባት እና ፈጣሪ ማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ወይም እሱን ካገኘሁት በኋላ እርሱን ለሁሉም መግለጽ አስተማማኝ አይደለምን?’በማለት የማያውቁትንም አምላክ እንዲያውቁ የአመክንዮአዊ ምርመራ(investigation of reason) መንገድን መክሯቸዋል።
_
ነገር ግን እነዚህን ነገሮች የእኛ የሁላችን ክርስቶስ በራሱ ኃይል አድርጓል። ማንም በክርስቶስ እንጂ ስለዚህ ትምህርት እንዲሞት በሶቅራጥስ(በሶቅራጥስም በከፊል(partially) የታወቀ)የሚታመን የለምና፤ (እርሱ ነበርና ፤በሁሉም ሰው ውስጥ ያለው ቃል ነውና የሚመጣውንም ነገር ትንቢት በነቢያቱም ሆነ በራሱ ማንነት ፥ ጥልቅ ፍቅርን በሚያደርግና እነዚህን ነገሮች በሚያስተምርበት ጊዜ ተናግሯል)፤ ፈላስፎችና ሊቃውንት ብቻ ሳይሆኑ፣ እንዲሁም የእደ-ጥበብ ባለሙያዎችና ፈጽሞ ያልተማሩ ሰዎችም ደግሞ፥ ክብርን፣ ፍርሃትን፣እና ሞትንም ሁሉ ይንቃሉ። እርሱ የማይነገር የአብ(ineffable father) ኃይል ነው እንጂ የሰው አእምሮ መገለጫ መንገድ ብቻ አይደለም።.››]¹
__
[1]- [St. Justin Martyr,Second Apology, chapter 10]

@orthodoxdigitallibrary
691 viewsedited  14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 16:26:36 ጾመ ነብያት በያዝነውሳምንት ይገባል ጾሙን በኦርቶዶክሳዊ የጾም ስርዓት ማሳለፍ ይኖርብናል ማለትም በጸሎት በንስሀ በንባብ  ማሳለፍ ይጠበቅብናል።

ለዚህ ጾም ብናነባቸው ብዬ የምጋብዘው መጽሐፍት
ስለ ጌታችን ቅድስት ልደቱ እና ስለ ነገረ-ክርስቶስ የሚናገሩ የአበው መጽሐፍትን
፩ የቅዱስ አትናቴዎስን On the incarnation of the word
፪ የቅዱስ ኤፍሬምን On our lord
፫ የቅዱስ ኤፍሬምን Hymn on the nativity
፬ የቅዱስ አምብሮስን The sacrament of the incarnation of our lord
፭  የቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያን Scholia on incarnation of the only begotten
፮  የቀሲስ ታድሮስን Joyful songs of the glorious nativity let Us praise with the angels by st. jacob of serugh

ሌሎች የአበው ሥራዎች
፯ የቅዱስ ሄሬኔዎስን On the apostolic preaching
፰የቅዱስ ቆጵርያኖስን On the unity of the church (treatise1)
፱ የቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያን On the holyspirit
፲ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙን On God and christ the five theological orations
፲፩ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስን Catechetical discourse
፲፪ የቅዱስ ኤፍሬምን Hymns on the unleavened bread
አምላከ አበው አንብበን ለመጠቀም ያብቃን!
1.0K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ