Get Mystery Box with random crypto!

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicsuccession — የጥያቄዎቻችሁ መልስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicsuccession — የጥያቄዎቻችሁ መልስ
የሰርጥ አድራሻ: @apostolicsuccession
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.61K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ኦርቶዶክሳዊ ገጽ ዋና ዓላማ የወጣቱን ጥያቄ መመለስ ነው። ወጣቶች ማንኛውም በሕይወታቸው የገጠማቸውንም ይሁን መንፈሳዊ ጥያቄ በሚረዱት መልክ መልስ ይሰጥበታል
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCPLJimNlqTFBnlbsh_vccgg
ለጥያቄዎችና ለአስተያየቶች
@AbuNak
@Rhripsime

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-07-07 22:22:20 https://t.me/akoteat
4.9K views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:42:59
ተሳተፉ
8.2K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 10:48:45 ሰላም አቡ። ይህን መልእክት እያነበብክ ከኾነ ሰላምታዬን ለወንድም አክሊልም አድርስልኝ። እግዚአብሔር በሚያውቀው በጣም ነው የምወዳችሁ፣ የምኮራባችሁ የምማርባችሁ እንዲሁም መንፈሳዊ ቅናት የምቀናባችሁ። እያወደስኳችሁ አይደለም ምንም ብታደርጉ መወደስ የለባችሉም ምክንያቱም በእናንተ አድሮ የሚሰራ መድኃኔዓለም እንጂ እናንተ አይደላችሁም የእውቀት ምንጭም ባለቤትም እሱ ነው እና ከራሳችሁ የኾነ ምንም የላችሁም ይህንን እናንተም ታውቃላችሁ እና ያው ማወደሴ አይደለም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ኃጢአት ከጣለው ውዳሴ ከንቱ የጣለው ይበዛል ስለሚል። ወደ ጉዳዬ ስገባ የኔ ማንነት መሰረቱ (foundation) ይሄ ቻናል ነው የጥያቄዎቻችሁ መልስ የሚለው። ይህን የምልህ ነፍሴን ስላተረፈልኝ ነው። ታሪኩ እንዴት መሰለህ እኔ ዪኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ እና እኛ ክላስ ውስጥ አንዲት ልጅ ተሐድሶ ሆነች ሲሉኝ ውስጤ ስለተቃጠለ ማውራት አለብኝ ብዬ ሄድኩ ከዛ አወራን የሚገርምህ በሕይወቴ መጽሐፍ ቅዱስ የሚባል ገልጨ አላውቅም ነበር አሁንም ቢኾን ጨርሼ አንብቤ እንኳን አላውቅም። እና እልሃለው በሞራል ሂጄ ገበሬ አስደንግጥ የኾነ ጥቅስ እየነገረች አወናበደችኝ እና እሷ ያለችው ነገር ውስጤ ቀረ ምክንያቱም ከዛ በፊት ምንም አይነት የቤተ ክርስቲያን እውቀት አልነበረኝም ለስሙ የእድሜዬን ብዙውን ክፍል ሰ/ትቤት ነው ያሳለፍኩት። እና ከዛ በኋላ ትምህርቴን እንኳ መማር አልቻልኩም ነበር ክላስ ቁጭ ብዬ እሷ ያለችኝ ኑፋቄ ብቻ ነው ውስጤ ሚመላለስ እጅግ በጣም ተረበሽኩ ደግነቱ ባይባልም ኮሮና መጥቶ ወደ ቤት ተመለስን ግን ጭንቀቱ ውስጤ መረበሹ አላቆመም አንዳንዴ ውስጤ ትክክል ናት እያለ ያስጨንቀኛል በጣምምምምምምም፤ እኔ ደሞ ምንም እውቀት የለኝም ለማበድ ምንም አልቀረኝም ቀንም ሌትም እንቅልፍ አልነበረኝም የሚገርምህ በቃ መናፍቅ ልኾን ነው ብዬ ነበር ግን ውስጤ ላይ በ40 ቀኔ የተቀልብኩት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲጠብቀኝም ይሰማኛል። ከዛ እንዴት እንደኾነ አላውቅም እዚ ቻናል ውስጥ ገባው ከመጀመሪያው ጀምሬ ኹሉንም አየውት በጣም ነበር ለማመን የከበደኝ ምክንያቱም የጥያቄዎቼ እያንዳንዱ መልሶች ቁጭ ቁጭ ብለዋል ከዛ ማዳማጥ ጀመርኩ ቮይሶቹን ፤ጽሑፎችን ደሞ አነባለው ከዛ ጥያቄዬ ቀስ በቀስ እየተመለሰ እየጠነከርኩ መጣው ሌላው የሕይወቴ መሰረት ደሞ የለቀቃችሁት መጽሐፍ ነበር "መድሎተ ጽድቅ" እንዴት መዶሻ የኾነ መጽሐፍ መሰለህ ቅጽ 1 የናንተን ሶፍት ኮፒ አነበብኩ ቅጽ 2 ቆጥቤ ገዛው እንደውም ማዘር ቀውጣው ነበር ቲሸርት አገዛም ብላ መድሎተ ጽድቅን ካነበብኩ በኋላ ይበልጥ ጠንከር አልኩ አሁንም ግን ቻናሉን መከታተል ጀመርኩ በተለይ ነገረ ድኅነት አስሩ ክፍሎች ፣ የሮሜ ማብራሪያዎች ፣ የእብራውያንም ኹሉንም ደጋግሜ አደመጥኩ የሚገርምህ መጽሐፍ ማንበብ የጀመርኩ ከናንተ የተነሳ ነው ከመጽሐፉ በላይ ግን የቀረጸኝ እመቤቴን ቻናሉ ነው። ይህን ኹሉ ሳወራ አዋቂ ሁኜ አይደለም እግዚአብሔር በሚያወቀው የደንቆሮዎች አለቃ ነኝ አቡነ እንኳን ማለት የቻልኩት በቅርቡ ነው። እና ከዚህ ኹሉ በኋላ እንደገና ልጅቷ ጋር አወራን ከዛ ልሰማት ነው እንዴ የመጽሐፍ ቻናላችሁ ላይ ገብቼ ኹሉንም መጽሐፍ ስላወረድኩ ከዛ እያየው አስጨነኳት ከዛ ሚገርመው ነገረ ድኅነትንም ልኬላት መድሎተ ጽድቅንም ስለ ድኅነት የሚናገረውን አንብባ ይደድ አሳምኖኛል አለች ከዛ ግቢ የሚበጠብጥ ማዕተብ ያደረገ ተኩላ ነበር እሱ ጋርም አገናኘችን ጌታ ይመስገን ምንም አልደነገጥኩ አልተረበሽኩ ዘላብዶ ሄደ አንድ ያለኝን ነገር ግን አልረሳውም "እኔ ጴንጤ የሆንኩት ሃይማኖተ አበውን አንብቤ ነው" ነበር ያለኝ እና በጣም ነበር የሳኩት ሃይማኖተ አበውን ባላነበውም የተለያዩ ትምህርቶች እና መጻሕፍት ላይ ሲጠቀስ አይቻለው ውስጡ ያለው ትምህርት። እና ከዚህ ኹሉ በኋላ አሁን ላይ ውስጤ ምንም አይነት የምንፍቅና ጥያቄ ምናምን የለም ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው። አሁን ላይ የሚያሳስበኝ የስም ክርስቲያን መኾኔ ምግባር የለለኝ መኾኔ ነው ለዚህም ወልደ ዮሐንስ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ ለምግባር ለትሩፋት እንዲያበቃኝ። አሁንም ቻናላችሁን እከታተላለው ከተላያዩ ወንድሞች ጋር የምታደርጉትንም ውይይት አያለው ዩ ቲዩብ ላይ እየገባው አሁንም ከናንተ እየተማርኩ ነው። የሚገርምህ አቡ ባይገባኝም (ለቦታው ባልመጥንም) ሰ/ትቤታችን ውስጥ ለኅጻናትና አዳጊ ክፍል ተከታታይ ኮርሶችን አሰጥ ነበር እንዲሁም አዋቂዎች ላይም ኮርስ የመስጠት እድል ተሰጥቶኛል ለትምህርት ወደ ግቢ ስለመጣው ሳይኾን ቀረ እንጂ አሁን ላይ ክብር ለመድኃኔዓለም ይሁን እመቤቴ ጥላዋን በላዬ ጥላብኝ በቸርነቱ አለው። እና አሁን ላለሁበት(ለመጽናቴ) ነገር ትልቁንና የመጀመሪያውን ደረጃ ተወጥቶ ያዳነኝ ቻናላችሁ ነው እናንተንም በውስጥ እጠይቅ ነበር እና ዋጋ ከፋይ መድኃኔዓለም ዋጋ ይክፈልልኝ። እኔ አላሞግሳችሁም ምክንያቱም አንደኛ ሁሉ ሥራ የመድኃኔዓለም እናንተ መሳሪያ ናችሁ ኹለተኛ ምንም ብታደርጉ እንዳደረጋችሁ አይቆጠርም ቅዱስ ጳውሎስ ዓለምን ዞሮ እግሩ እስኪላጥ አስተምሮ ገና እንዳላይዝኩት እቆጥራለው ነው ያለ በዚህ ሒሳብ እናንተ ገና 0 ላይ ናችሁ ምንም አልሰራችሁም እና ሥሩ ጠንክሩ በርቱልን።

" እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ። የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።"
(የሉቃስ ወንጌል 17:10)

ታናሽ ወንድማችሁ ወልደ ዮሐንስ ከ.....ኢትዮጵያ
7.2K views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 22:04:45 ያለፈው ዘመን ይበቃናል

ለግል ተማሪዎች የእመቤታችን ዘካሪዎች ዛሬ 21/10/2014 የተሰጠ

አቡ
@ApostolicSuccession
5.5K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 09:30:13

10.4K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 16:56:29

9.1K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 16:56:29

7.6K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 16:34:54

7.3K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 12:30:18
12.7K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 10:13:56
10.8K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ