Get Mystery Box with random crypto!

ግዮን-ፎረም

የቴሌግራም ቻናል አርማ amarawiyan — ግዮን-ፎረም
የቴሌግራም ቻናል አርማ amarawiyan — ግዮን-ፎረም
የሰርጥ አድራሻ: @amarawiyan
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.37K
የሰርጥ መግለጫ

ግዮን -ፎረም
➠ ወቅታዊ እና ታማኒ መረጃ፣
➠ ትኩስ እና ፈጣን ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች ለእናንተው
ለአስተያየት እና ጥቆማ
@Amarawiyanbot
@Amarawiyanbot
t.me/amarawiyan
Invite link
"አማራ በአማራነቱ ይኮራል"

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-05-12 10:17:06 #Breaking

ህውሓት ጦር መክፈቷ ተሰምቷል ። ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል ።


በዩቲዩብ ቻናላችን የአርበኛ ፋኖ ቻላቸው እንየው በጋይንት : በጭልጋ የፈፀማቸውን ጀብዶች ይዘን ቀርበናል ።



2.2K views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 09:04:29 በፋኖ ላይ መዝመት በአማራ ህልውና ላይ መዝመት ማለት ነው! ሲል የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ መግለጫ ሰጧል፡፡

በፋኖ ላይ መዝመት በአማራ ህልውና ላይ መዝመት ማለት ነው! ሲል የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ መግለጫ የሰጠ ሲሆን መግለጫውም፡- በቅርቡ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ለዘመናት ተከባብሮ በሚኖረው በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ማህበረሰብ የተፈጠረው ግጭት መነሻው የቀብር ድንጋይ ነው ብሎ መቀበል በስተጀርባ ሆነው ሴራውን ላቀነባበሩትና ጠቡን ለቆሰቆሱት ወንጀለኞች ሽፋን መስጠት ነው ብለን እናምናለን። በተለይም ባለፈው አራት ዓመታት ኢትዮጵያ ሰላም በተነሳችበት፣ ሚሊዮኖች በተፈናቀሉበት፣ በመቶ ሺዎች ሕይወታቸውን ባጡበት፤ አማራው በቤኒሻንጉል-ጉሙዝና በኦሮሚ ያ ክልሎች በየጊዜው በማንነቱ በሚታረድበት፣ በአማራና በአፋር ክልል ከተማዎች በተደመሰሱበትና ከሁሉም በላይ ዶ/ር አብይ አህድ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታትና ድራሹን ለማጥፋት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት በጎንደር ላይ የተፈጠረውን ከቀብር ድንጋይ ጋር ማያያዝ ነገሩን ማቅለል ይመስለናል። የሀገር ሽማግሌውን ሸህ ከማል ለጋስን ለመቅበር በተሰበሰበው የሙስሊም ወግኖቻችን ላይ ቦንብ የወረወረው ግለሰብ ወይም ስብስብ ወንጀሉን የፈፀወው የኦርቶዶክስ ቤተ-ከርስቲያን ተቆርቋሪ ስለሆነ ነው ብሎ መደምደም ከላይ የተጠቀሰውን የሃገራችንን ሁኔታ አለማገናዘብና ሴራውን ላቀነባበሩት ማምለጫ መንግድ መክፈት ይመስለናል።

እውነቱን ተገንዝቦ የችግሩን መንሥኤ ፊትፊት አለመጋፈጥ ማህበረሰቡን ለተከታታይ ጥቃት ማጋለጥ ነው ብለንም እናምናለን። በዚህ አጋጣሚ በሀገር አፍራሾች ደባ ምክንያት ለሞቱት ሙስሊምና ክርስቲያን ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፤ የሁለቱም የእምነት ተከታዮች የፈረሱትን መስጊዶች በጋራ እንዲሰሯቸውና ጠላትን እንዲያሳፍሩም እናሳስባለን። ሀገር የማፍረስ ፕሮጀክት ያነገበ ጠ/ሚንስትር በሚመራት ሀገር ጎንደር በተፈፀመው አሳዛኝ ተግባር የሌሎቹ እጅ መኖሩ ሊደንቀን አይገባም።
ነገሮች የተቀነባበሩ ስለሆነ ሁኔታውን የበለጠ ማጦዝ አሰፍስፎ ይጠብቅ የነበረው የአህመዲን ጀበል ፅንፈኛ የሰለፊ ቡድን በወራቤ በርከት ያሉ ቤተክርስቲያናትን ሲያቃጥል ጊዜ አልፈጀበትም።

እሳቱን ለማጥፋት የወጡ ሰዎችንም በመደብደብ የአካል ጕዳት አድርሷል። ይህ ቡድን ለአማራ ክልል እንግዳ አይደለም። አጣዬ በተደጋጋሚ ስትወረርና ስትወድም እንዲሁም ወራሪው ሕወሃት ደብረሲና ሲደርስ በማህበራዊ ሚድያ በደሰታ ሲፈነድቅ ነበር። ኦሮሚያ ክልል ሙስሊም አማራዎች በማንነታቸው በየጊዜው ሲታረዱ አንድም ቀን ድምፁን አሰምቶ ኢያውቅም። ስለሆነም ይህ ቡድን ከጎንደር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በደሴ በሚገኙት ጀሌዎቹ አማካይነት በምኑም ላይ በሌበት ፋኖን አሸባሪ ነው፣ ፋኖ አክራሪ ክርስቲያን ነው የሚል ዘመቻ መክፈቱ ሊደንቀን አይገባም።

ለመሆኑ ፋኖን አክራሪ ክርስቲያን የሚለው በሰሜን ወሎ ፀረ-ወያኔ ትግሉን የሚመሩትን እነ ፋኖ ጄነራል ሃሰን ከረሞን ሙሊሞች አይደሉም እያለን ይሆን?
በጄነራል አሳምነው ፅጌ ስም የተሰየመውን እና ሁሉንም ያካተተውን የፋኖ ብርጌድ አዛዥ በሆኑት በእነ መሬ ዎዳጆ የሚመራውን ጦር ለማን አሳልፎ ሊሰጥ አስቦ ይሆን? የሕወሃትን ምሽግ ሲሰብሩ የተሰውትን እነፋኖ ሙሐምድ ደጉንና ሰይድ ገረየስን እና ሌሎችንም በእምነታቸው የማይደራደሩ ሙስሊሞች እንደሆኑ ሊክደን ይሆን? ሃቁ ግን ከአብይ አህመድ ጀምሮ ጀዋር መሃድ ከእሥር ከተፈታ ወዲህ የጠ/ሚንስትሩ ደጋፊ የሆነው ይህ ፅንፈኛ ቡድንና እንደ ኦፌኮ የመሰሉ ድርጅቶች የከነከናቸውና እንቅልፍ የነሳቸው ነገር ቢኖር ፋኖ የአማራው የጋራ እሴትና ሁሉን አቃፊ መሆኑ ነው። በፋኖ ውስጥ የነሱ ውድቀት ፍንትው ብሎም ስለሚታያቸው ነው። አብይ አህመድ ከአማራ ሕዝብ አብራክ የወጣውንና ለአማራ ሕዝብ ህልውና ብሎም ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠል የቆመውን ፋኖን እንደ ዋና ጠላት አድርጎ ከቆጠረው ዋል አደር ብሏል።

ጠ/ሚንስትሩ በሕወሃት ወረራ ጊዜ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለውን ፋኖን ስንቅና ትጥቅ እንዳይደርሰውና በባዶ ሆዱና እግሩ እንዲዋጋ ያደረገውና ዛሬም የሚያሳድደው አገር የማፍረስ አጀንዳውን የሚገዳደርበት ብቸኛ ኃይል ስለሆነ ነው።
ዛሬ ሕወሃት የፋኖን ያህል ለአብይ አህመድ አጀንዳ አይደለም፤ ማስረጃውም ብርሃኑ ጁላን ሲሸልስ ድረስ ልኮ ከሕወሃቱ ጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር ፋኖን በጋራ ስለማጥፋት ተደራድሯል።
ስለዚህ ፋኖን ለመምታት መንደርደሪያ እንዲሆን የጎንደሩ ግጭት መቀነባበር ነበረበት።

ዋና ተዋንያኖቹም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ባሕርዳርና ጎንደር የሚርመሰመሱት በተመስገን ጥሩነህ የሚመሩት የአብይ አህመድ ደህንነቶችና ሁኔታውን ያመቻቸላቸው ምን ጊዜም የወገኑ ጠላት የሆነው ብአዴን መሆናቸውን ሕዝቡ ሊያውቅ ይገባል እንላለን።
ተጠያቂዎቹም ወንጀለኞቹም እነሱ ናቸው። ይህ መግለጫ እየወጣ ባለበት ሰዓት ደቡብ ወሎ ገራዶ የሚገኘውን የፋኖ ካምፕ አስከብቦታል።

በሰሜን ወሎ ከሕወሃት ኃይል ጋር ለተፋጠጠው የፋኖ ኃይል ደጀን የነበረውን የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን አንስተውታል። ሴራውም ቀጥሏል።
ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሀይ:_
ከሀገርህ ያለህ ክብርና ፍቅር ከስነልቦናህ የማይፋቅ ስለሆነ ለማንም ጥያቄ እንዲያነሳበት አትፍቀድለት።
ስለሆነም ዛሬ ያንተ ዋና አጀንዳ ህልውናህን ማስጠበቅ ብቻና ብቻ ነው። ዙሪያህን ሊያጠፉህ በሚፈልጉ ጠላቶች ተከበሃል። በተለይም ሕወሃትና የኦሮሞ ብልጽግና እየተናበቡ የሚያሳዩህ መከራ መቼም አያባራም። ጄኔራል ተፈራ ማሞን ከሥልጣኑ ካነሱት በኋላ የክልልህን ልዩ ኃይል እየበተኑብህ ነው።

በህልውናህ ላይ የተቃጣብህን አደጋ ፈጽሞ ማጋነን አይቻልም። ስለሆነም ከልጅህ ከፋኖ ጎን ከመቼውም በበለጠ እንድትቆም ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን።
ዕድሜያቸውና አቅማቸው የሚፈቅድላቸውን ልጆችን ፋኖን አንዲቀላቀሉ አድርግ።

አንተም ራስህ ፋኖ ነህና በመንደርህ፣ በቀበሌህና በወንዝህ በጎበዝ አለቃ ተደራጅ። ነገር ግን ሁሉም አማራ አሁኑኑ በአንድነት ተደራጅቶ ህልውናውን ካላስጠበቀ በስተቀር “አማራ" የሚባል ሕዝብ እኮ እዚህ አካባቢ ይኖር ነበር የሚባልበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

በቅርቡ የሚታየው የአማራን ልዩ ኃይል፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖን ተሸላሚና ያልተሸለመ በሚል ጨዋታ የአማራውን የህልውና መከታ የሆኑትን የአማራ ኃይሎችን በመከፋፈል የሚደረግ የብአዴን ብልጽግና ሌላ ዙር ሴራን በመገንዘብ ማክሸፍ ይገባል።
ለፋኖ፣ ለአማራን ልዩ ኃይል እና ለአማራ ሚሊሻና ሽልማታቸው የአማራን ህልውና በማስከበርና ሀገራቸውን በመታደግ የገቡበትን ታሪካዊ ትግል በድል መወጣት ነው።

አማራን በመላው ሀገሪቱ የአሰቃቂ ወንጀሎች ሰለባ ተደርጎ እረፍት አልባ ህይወት እንዲመራ ቀንና ሌሊት የሚሰራው የአብይ አህመድ የብልጽግና አገዛዝ ከአማራ አብራክ ለወጡ ኃይሎች ወዳጅ ወይም ሸላሚ ለመሆን መቅረብ ትልቅ ቧልትና አይን አውጣነት መሆኑን ያለፉት አራት የነውጥና የመንግስታዊ ውሸት አመታት ምስከሮች ናቸው ብሏል የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በመግለጫው።

ኢመማ

https://t.me/amarawiyan
2.1K viewsedited  06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 08:46:46 ሁሉም አማራ መሰልጠን መታጠቅ ፋኖን መቀላቀል አለበት ። አለቀ!

በክንዳችን ነፃነታችን እናረጋግጣለን !
1.8K views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 08:42:42 የትግራይ ህዝብ “ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል” እንዲዘጋጅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥሪ አቀረቡ !!

ትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ከማዕከላዊው መንግስት ጋር ችግሮችን በዲፕሎማሲ ለመፍታት ሲደረግ የነበረው ጥረት “ባለመሳካቱና የሰላም መንገድ በመዘጋቱ የትግራይን ሕዝብ ነፃነት ለማረጋገጥ” የክልሉ ህዝብ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረቡ።

ደብረፅዮን በመቀሌ ሌሎች የሕወሓት አመራሮች ደግሞ በተለያዩ የትግራይ ዞኖች ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበት የከፋ ስቃይ እንዲቀለበስና የትግራይ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

“ሁሉም የፖለቲካ ችግር በሰላምና በዲፕሎማሲ እንደማይፈታ ብናውቅም አሁን የገባንበት ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድመን እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተናል” ብለዋል ደብረፅዮን በመቀሌ ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ።

በአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸማጋይነት ጊዚያዊ ስምምነት ተደርጎ ወደ ክልሉ እህል መድሀኒትና ሌሎች ድጋፎች እንዲገቡ ጥረት ብናደርግም እስከ አሁን ድረስ የተገኘው ድጋፍ ችግሩን ለማቃለል በቂ አይደለም ብለዋል።

መላክ ያለበትን መልዕክት ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ባለን የመገናኛ መንገድ አድርሰናል ያሉት ደብረፅዮን የሚመለከታቸው ያሏቸውን አካላት አልዘረዘሩም።

መንግስት የተኩስ አቁም በሚል ሽፋን የመሳሪያና የሰራዊት ማሰባሰብ ስራ ላይ ነው ሲሉ የከሰሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የትግራይ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚረጋገጠው የኀይል የበላይነትን በመያዝ ብቻ መሆኑን ለተሰብሳቢዎች አስረድተዋል።

ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር(ሞንጀሪኖ)፣ አለም ገብረሐዋድና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ነዋሪዎችን ያወያዩ ሲሆን ሕዝቡ ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ባመቻችም ሕወሓት ራሱ ዕርዳታ በማስተጓጎልና ተጎራባች ክልሎችን በመውረር እንቅፋት መፍጠሩን ይናገራል። የትግራይ አማፅያን በቅርቡ ይዘውት ከነበረው የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንት የምዕራብ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊትን በቦታው ተገኝተው ያበረታቱ ሲሆን ወታደራዊ ብቃቱን የሚያሳይ ትርዒትም ተመልክተዋል።

Wazema
https://t.me/amarawiyan
https://t.me/amarawiyan
1.9K viewsedited  05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:14:57
ፋኖነት ሕይወቱ ነው!

ከምርጫ 97 ማግስት ገና በልጅነቱ ነው የአርበኝነት ትግሉን የተቀላቀለው! በአማራ ተጋድሎ ምልክት የነበረው የጎቤ ጦር አካል ነበር። ያውም ቀኝ እጁ!
በአርበኝነት ትግሉ ደጀኔ ማሩን ሊያፍኑ የመጡ አንድ መኪና የአፋኝ ቡድን አባላት መንገድ ላይ ተመትተው አላማቸው የከሸፈው አጋዬ በሚመራው ጦር ነበር።

ከተመቱት መካከል የቆሰሉትን ታዲያ ከሕዝብ መኪና ጠይቀውም ወደ ጎንደር ሆስፒታል ልከዋቸዋል። መንግስት የተባለው "ሽፍታ" ብሎ አስከሬን በሚጎትትበት ወቅት ፋኖዎቹ እነ አጋዬ ሊገድላቸው የመጣን ቁስለኛ አሳክመዋል።

በ2008 ዓ/ም በነበረው ንቅናቄ ወደ አማራ ክልል መጥተው ንፁሃንን ሊያፍኑ የትህነግ የትህነግ የአርማጭሆን በርሃ ሳያልፉ መምገድ ላይ የቀሩት በእነ አጋዬ ጦር ነበር። እነ አጋዬ ጫካ ሆነውም የከተማውን ሕዝብ ጠብቀዋል።

አጋዬ አድማሱ ለእስር ተዳርጎ ማዕከላዊና ሌሎች እስር ቤቶችንም አይቷል። ሲመለስ ወደ ግብርና ስራው ገብቷል። ጠላት ሲመጣ ደግሞ የግብርና ስራውን ትቶ በርካታ ጀብዱዎችን ሰርቷል። ዛሬ የአማራ ክልል በሕልውና ትግሉ ላደረገው አስተዋፅኦ ሸልሞታል። ሲያንሰው ነው! አጋዬ የሕልውና ትግሉ ፋኖ ብቻ አይደለም። ፋኖነት ያደገበት ነው። ፋኖነት የኖረበት ሕይወቱ ነው!

Getachew shiferaw

https://t.me/amarawiyan
https://t.me/amarawiyan
1.9K viewsedited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:06:41
የመተከል አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በጃዊ ከተማ ጥቃት እየደረሰብኝ ነው ሲል ገልጿል።

የመተከል አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ደመላሽ አንድነው ለንሥር ብሮድካስት እንደገለፁት በወረዳው አስተዳደር በኩል የመተከል አስተዳደር ኮሚቴ እና የቦርድ አባል የሆኑትን የማሰር እና ስም የማጠልሸት ተግባር የተጀመረ ቢሆንም ይህን እኩይ ተግባር በመቋቋም መተከልን ወደ አማራ ጎጃም ግዛት ለማስመለስ የሚያስችል ተግባራትን እየፈፀሙ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ሆኖም ይላሉ ሰብሳቢው የአዊ ዞን አስተዳደር ከቤኒሻጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት በሚቀበሉት የአማራነት አፍራሽ ተልዕኮ ምክንያት የመተከል አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴን በጠላትነት ፈርጀው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብለዋል።

በትናትነው ዕለትም የማንነት ኮሚቴ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ እንዳለው አዲስን ከስራ ገበታቸው ላይ እያሉ ፓሊስ እና ሚሊሻ በመላክ ያሰራቸው ሲሆን ሌሎችንም ኮሚቴዎች በተመሳሳይ ለማሰር ማደኛ አውጥተው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በኮሚቴዎች ላይ የሚደርሰው እስርና አደን መተከልን ወደ ጎጃም ነባር ግዛትነት ለመመለስ የሚደረገውን ትግል እንቅፋት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን መላው የአማራ ህዝብ ሊረዳ ይገባል ብለዋል።

አክለውም የአማራ ህዝብ የመተከል ዕርስትን እንደ ወልቃይት፣ ራያ እና ደራ ተመለክቶ ትግሉን ከጎናችን ሆኖ
እንዲመራ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ንስር ብሮድካስት

https://t.me/amarawiyan
https://t.me/amarawiyan
1.8K viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:03:23
"#ዝምተኛው_ደምሳሽ"

ሀብት ነበረው : ነገር ግን ከሕዝብ ነፃነት አልበለጠበትም : ጀግንነቱን የራያ ተራሮች ይመሰክራሉ። የሚመራው ጦር በራያ ተራሮች ከ12 ቀን በላይ ከጠላት ጋር ተዋግተዋል።

በየጁ ተራሮች ተመሳሳይ ተጋድሎ ፈፅመዋል። በሃብሩ መርሳ ሸንተረር ሸለቆዎች ጀግንነቱን ለታሪክ አስመዝግቧል።

በጊራና እና በወርጌሳ የተራራ ሰንሰለት ከጢነኞቹ ጋር ጠላትን ሲያስጨንቅ ከርሟል። ከጠላት ስናይፐር እስከ ሞርታር ድረስ የማረከው ፋኖ መሪ ነው። ዛሬ አንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል።

ፋኖ ምሬ ወዳጆ

አራጋው ሲሳይ

https://t.me/amarawiyan
https://t.me/amarawiyan
1.8K viewsedited  19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ