Get Mystery Box with random crypto!

Albastros Ministries

የቴሌግራም ቻናል አርማ albastrosministries — Albastros Ministries A
የቴሌግራም ቻናል አርማ albastrosministries — Albastros Ministries
የሰርጥ አድራሻ: @albastrosministries
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.83K
የሰርጥ መግለጫ

"መልህቄ" የተሰኘው አልበሜን ዳውንሎድ በማድረግ ይባረኩበት:: ሊንኩን ለሌሎችም ያካፍሉ::

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-26 19:47:16 Albastros Ministries pinned «የተወደዳችሁ:- በዚህ ዝማሬ አብራችሁን ጌታን እንድታመሰግኑ: ሌሎችም እግዚአብሔርን ለማመስገናቸው ምክንያት እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር እጠይቃችዋለው::

»
16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 17:32:18 የተወደዳችሁ:- በዚህ ዝማሬ አብራችሁን ጌታን እንድታመሰግኑ: ሌሎችም እግዚአብሔርን ለማመስገናቸው ምክንያት እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር እጠይቃችዋለው::



4.5K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 22:23:24
መልካም ገና
808 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 17:44:19
2023 እንደ ግለሰብ እንደ ቤተሰብ እንደ ቤተክርስቲያን እንዲሁም እንደ ሃገር እንደገና የምንሰራበት አመት ይሁን!Happy Newyear #YearofRestoration
2.6K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 20:40:10
መልካም አዲስ አመት
የሰላም አመት ይሁንልን
5.2K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:27:23
በእናቴ ማህፀን ውስጥ ሳለው አጥንቶቼ ሳይዋደዱ
ደፋ ቀና ስል አድጌ እግሮቼም ቆመው ሲሄዱ
ሳልፈጠር የተፈጠሩን ቀኖቼን ያየህ
መልካም እየሆንክ እስከዛሬ እኔን እረዳህ

በእግዚአብሔር መልካምነት የረሰረሱ 40 አመታትን ጨርሼ እነሆ ዛሬ በመልካምነቱ 41 ጀመርኩ ክብሩ ይስፋ
5.7K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 17:25:59 ከዚሁ ከ"አባ" ሃሳብ ሳንወጣ: በቀደመው መልእክቴ መጨረሻ አንድ ነገር ጠቅሻለው:: "ደስስስስ ልናሰኘው እንጂ ይሄን ያን አድርግልኝ ለማለት አባ አንበለው" ብዬ ነበር:: " ለምኑ ይሰጣችዋል" የሚለውን ቃል ዘንግቼ አይደለም:: የለመነው ሁሉ አይሰጠንም የሚያስፈልገን እንጂ…

አርብ ከሰአት ሁለተኛዋ ልጃችን (ኤማ) በማሚ ስልክ በተደጋጋሚ ደወለች: እናም ሰአቱ ስልክ ላነሳ የማልችልበት የስራ ሰአት ስለነበር አላነሳሁም:: ከዚያም ስልኩ ላይ ባለ መቅረፀ ድምፅ በመጫን የቴክስት መልእክት ተላከልኝ:: ራሱን ላስፍርላችሁ "Daddy I want to show you something This is Ella and Emma" የጀመርኩትን ስራዬን ስጨርስ ( ከአንድ ሰአት በሁዋላ) መልሼ ደወልኩ::

ኤማ ናት ያነሳችው:: እጅግ በጣም ደስታ እና ፈንጠዝያ በተሞላው ድምፅ " Daddy Daddy can we do vedio??" አለችኝ "አዎ የኔማር" ብዬ ሳልጨርስ: ምስልዋን ማየት ጀመር እሱዋም የኔን::

እኔም ደስታዋን ተካፈልኩ: ደስስስስ አለኝ አብሬአት ጮህኩ:: ምን ሆና ቢሆን ጥሩ ነው:: ለመጀመርያ ግዜ አንድ ጥርስዋ ተነቃንቆ

አይ የልጅ ነገር አላችሁ? ምን መሰላችሁ ታላቅ እህትዋ (ኤላ) ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ: ሰባት ግዜ ጥርስዋ ሲነቃነቅ/ ሲነቀልላት/ ስትደሰት ስትፈነጥዝ: ስር ስርዋ በመሮጥ እየተቁለጨለጨች ነበር የምታያት::

ታድያ ዛሬ እንዲነቃነቅ ወይም እንዲነቀል ጥያቄ ሳታቀርብ በግዜው የእርሱዋም ተራ ደረሰ::

እና ምን ለማለት መሰላችሁ: ነገሮቻችን ውብ የሚሆኑት እንደቃሉ በግዜው ነው:: "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤" መክ3:11 አያችሁ ለሌሎች ልጆች / ለወንድም እህቶቻችን/ ሲደረግላቸው: አብረናቸው ደስታቸውን እንካፈል:: " የኔስ ነገር??" ብለን አናጉረምርም:: በነገራችን ላይ ብዙ ነገራችን የሚዘገየው እስክናድግለት እየጠበቀ ሊሆን ስለሚችል እድገታችን ላይ እናተኩር:: አባት ልጁ ሲያድግለት ደስ ይለዋልና:: እድገቱን በማየት እድሜው የሚፈቅድለትን በግዜው ውብ አድርጎ ይሰራለታል/ ይሰጠዋል/ ::

ኤማ(ትንሽዋ ልጃችን) የታላቅ እህትዋን ጥርስ መነቃነቅ አይታ ብታለቅስ የኔስ ብላ ብትጠይቅ: ግዜውን እንድትጠብቅ ከመንገር ውጪ ደስ እንዲላት ወይንም ከምታለቅስ ብዬ እንደማላነቃንቅላት ሁሉ: እግዚአብሔር አባታችንም ምንም እንኩዋን ሰማይን እና ምድርን የማነቃነቅ ችሎታ ቢኖረውም ነገሮቻችንን ውብ አድርጎ መስራት የሚወደው በግዜው ነው:: በአጭሩ አለግዜው የተነቀለ ጥርስ ላይበቅል ይችላል::ስለዚህ በቅሎ ለሌሎች የሚተርፍን በረከት በግዜው እንዲመጣ እየጠበቅን: ስለሚሰጠን ነገር ሳይሆን ስለአባትነቱ "አባ" እንበለው::

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል ብዙነህ /ዘማሪ

https://www.facebook.com/100045580370341/posts/pfbid02ZKubKhGtxLfGr4o6DU3ia7gyeNk3SJxnww1nmnWTyypCXe7YyjVBgfAJyGH1JbTNl/?d=n
10.9K viewsedited  14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 16:27:40 Channel photo updated
13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 16:23:28
ልጆቼ በተለያየ ስም ይጠሩኛል:: ዳዲ: አባቴ:አባት... "አባ" ብለው ሲጠሩኝ ግን: በቃ ምን ልበላችሁ ልቤ ይንሰፈሰፋል: ደስታዬ እጥፍ ይሆናል:: እኔ ሰው ሆኜ ይሄ ስሜት ከተሰማኝ እግዚአብሔር እማ እንዴት አብልጦ ደስስስ አይለው?

“ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።” ገላ4:6

ከዚህ ቃል የምረዳው: ሰጪው ራሱ እግዚአብሔር: እርሱን እራሱን የምጠራበት የልጁን/ የእየሱስን/ መንፈስ በልቤ ውስጥ ላከ:: አይገርማችሁም? እኔ ልጆቼ "ዳዲ ዳዲ" ሲሉኝ ባይከፋኝም አይጥመኝም እናማ አልፎ አልፎ "አባ" በሉኝ እላቸዋለው:: የሆነ በቃላት የማይገለፅ: የተለየ ስሜት /connection/ ይሰማኛል::

ደግሜ ልበላችሁ እኔ በልቤ ይሄ ከተሰማኝ... መለኮት የሆነውማ...

እስቲ ለሶሻል ሚድያ ያልሆነ: የእውነት አባትነቱ ገብቶን እና ተረድተን የልጁን መንፈስ በልቡ እንደፈሰሰለት ሰው በግላችን አባ አባ እንበለው:: ታድያ ይህን ያን አርግልኝ ለማለት ሳይሆን ደስስስስ እንዲለው:: ገላትያ 4:6
9.8K viewsedited  13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 10:41:53
10.6K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ