ልጆቼ በተለያየ ስም ይጠሩኛል:: ዳዲ: አባቴ:አባት... "አባ" ብለው ሲጠሩኝ ግን: በቃ ምን ልበላችሁ ልቤ ይንሰፈሰፋል: ደስታዬ እጥፍ ይሆናል:: እኔ ሰው ሆኜ ይሄ ስሜት ከተሰማኝ እግዚአብሔር እማ እንዴት አብልጦ ደስስስ አይለው?
“ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።” ገላ4:6
ከዚህ ቃል የምረዳው: ሰጪው ራሱ እግዚአብሔር: እርሱን እራሱን የምጠራበት የልጁን/ የእየሱስን/ መንፈስ በልቤ ውስጥ ላከ:: አይገርማችሁም? እኔ ልጆቼ "ዳዲ ዳዲ" ሲሉኝ ባይከፋኝም አይጥመኝም እናማ አልፎ አልፎ "አባ" በሉኝ እላቸዋለው:: የሆነ በቃላት የማይገለፅ: የተለየ ስሜት /connection/ ይሰማኛል::
ደግሜ ልበላችሁ እኔ በልቤ ይሄ ከተሰማኝ... መለኮት የሆነውማ...
እስቲ ለሶሻል ሚድያ ያልሆነ: የእውነት አባትነቱ ገብቶን እና ተረድተን የልጁን መንፈስ በልቡ እንደፈሰሰለት ሰው በግላችን አባ አባ እንበለው:: ታድያ ይህን ያን አርግልኝ ለማለት ሳይሆን ደስስስስ እንዲለው:: ገላትያ 4:6