Get Mystery Box with random crypto!

ከዚሁ ከ'አባ' ሃሳብ ሳንወጣ: በቀደመው መልእክቴ መጨረሻ አንድ ነገር ጠቅሻለው:: 'ደስስስስ ልና | Albastros Ministries

ከዚሁ ከ"አባ" ሃሳብ ሳንወጣ: በቀደመው መልእክቴ መጨረሻ አንድ ነገር ጠቅሻለው:: "ደስስስስ ልናሰኘው እንጂ ይሄን ያን አድርግልኝ ለማለት አባ አንበለው" ብዬ ነበር:: " ለምኑ ይሰጣችዋል" የሚለውን ቃል ዘንግቼ አይደለም:: የለመነው ሁሉ አይሰጠንም የሚያስፈልገን እንጂ…

አርብ ከሰአት ሁለተኛዋ ልጃችን (ኤማ) በማሚ ስልክ በተደጋጋሚ ደወለች: እናም ሰአቱ ስልክ ላነሳ የማልችልበት የስራ ሰአት ስለነበር አላነሳሁም:: ከዚያም ስልኩ ላይ ባለ መቅረፀ ድምፅ በመጫን የቴክስት መልእክት ተላከልኝ:: ራሱን ላስፍርላችሁ "Daddy I want to show you something This is Ella and Emma" የጀመርኩትን ስራዬን ስጨርስ ( ከአንድ ሰአት በሁዋላ) መልሼ ደወልኩ::

ኤማ ናት ያነሳችው:: እጅግ በጣም ደስታ እና ፈንጠዝያ በተሞላው ድምፅ " Daddy Daddy can we do vedio??" አለችኝ "አዎ የኔማር" ብዬ ሳልጨርስ: ምስልዋን ማየት ጀመር እሱዋም የኔን::

እኔም ደስታዋን ተካፈልኩ: ደስስስስ አለኝ አብሬአት ጮህኩ:: ምን ሆና ቢሆን ጥሩ ነው:: ለመጀመርያ ግዜ አንድ ጥርስዋ ተነቃንቆ

አይ የልጅ ነገር አላችሁ? ምን መሰላችሁ ታላቅ እህትዋ (ኤላ) ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ: ሰባት ግዜ ጥርስዋ ሲነቃነቅ/ ሲነቀልላት/ ስትደሰት ስትፈነጥዝ: ስር ስርዋ በመሮጥ እየተቁለጨለጨች ነበር የምታያት::

ታድያ ዛሬ እንዲነቃነቅ ወይም እንዲነቀል ጥያቄ ሳታቀርብ በግዜው የእርሱዋም ተራ ደረሰ::

እና ምን ለማለት መሰላችሁ: ነገሮቻችን ውብ የሚሆኑት እንደቃሉ በግዜው ነው:: "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤" መክ3:11 አያችሁ ለሌሎች ልጆች / ለወንድም እህቶቻችን/ ሲደረግላቸው: አብረናቸው ደስታቸውን እንካፈል:: " የኔስ ነገር??" ብለን አናጉረምርም:: በነገራችን ላይ ብዙ ነገራችን የሚዘገየው እስክናድግለት እየጠበቀ ሊሆን ስለሚችል እድገታችን ላይ እናተኩር:: አባት ልጁ ሲያድግለት ደስ ይለዋልና:: እድገቱን በማየት እድሜው የሚፈቅድለትን በግዜው ውብ አድርጎ ይሰራለታል/ ይሰጠዋል/ ::

ኤማ(ትንሽዋ ልጃችን) የታላቅ እህትዋን ጥርስ መነቃነቅ አይታ ብታለቅስ የኔስ ብላ ብትጠይቅ: ግዜውን እንድትጠብቅ ከመንገር ውጪ ደስ እንዲላት ወይንም ከምታለቅስ ብዬ እንደማላነቃንቅላት ሁሉ: እግዚአብሔር አባታችንም ምንም እንኩዋን ሰማይን እና ምድርን የማነቃነቅ ችሎታ ቢኖረውም ነገሮቻችንን ውብ አድርጎ መስራት የሚወደው በግዜው ነው:: በአጭሩ አለግዜው የተነቀለ ጥርስ ላይበቅል ይችላል::ስለዚህ በቅሎ ለሌሎች የሚተርፍን በረከት በግዜው እንዲመጣ እየጠበቅን: ስለሚሰጠን ነገር ሳይሆን ስለአባትነቱ "አባ" እንበለው::

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል ብዙነህ /ዘማሪ

https://www.facebook.com/100045580370341/posts/pfbid02ZKubKhGtxLfGr4o6DU3ia7gyeNk3SJxnww1nmnWTyypCXe7YyjVBgfAJyGH1JbTNl/?d=n