Get Mystery Box with random crypto!

የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የሰርጥ አድራሻ: @adnan567mh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.89K
የሰርጥ መግለጫ

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን✔
JOIN 👇
@Adnan567mh
🌐💚💛❤️

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-05-23 17:30:29 ቢድዓ [ፍልስፍና]
➩➪➩➪➩➪➧
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

ቢድዓ [ፍልስፍና]
➪➩➪➩➪➩➪

የኛ ሀይማኖት እስልምና የተሟላ እና ጭማሬ የማይፈልግ ሙሉዕነቱ የተረጋገጠ ነው።

الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ

ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡
[ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 3]

በአላህ ምስክርነት ዲናችን የተሟላ ነው። ስለዚህ ቢድዓ አያስፈልግም፤ ለምን ከተባለ ሃይማኖታችን ሙሉ ነውና!!!

ለመሆኑ ቢድዓ ምንድን ነው?
➷➘➷➘➷➘➷➷➘➷
ቢድዓ ማለት ቁርአናዊ እና ሐዲሳዊ ማስረጃዎች እንደዚሁም እንደኢጅማዕ ያሉ ትክክለኛ ማስረጃዎች የማይደግፉት እና ለዲን ተብሎ ወይም ወደ አላህ ያቃርበኛል ተብሎ የሚሰራ ተግባር ነው። ዱንያዊ ፈጠራዎች እዚህ ውስጥ አይገቡም።

➲ በዲን ውስጥ አዲስ ነገርን ማምጣት የተከለከለ ለመሆኑ፤ እንደዚሁም አላህ እና መልእክተኛው - ﷺ - ያዘዙንን ተግባር ሳንጨምር ሳንቀንስ መስራት እንዳለብን ከሚጠቁሙ ቁርአናዊና ሀዲሳዊ ማስረጃዎችን ከብዙ በጥቂቱ እንመልከት፦

وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
[ሱረቱ አል-ሐሽር - 7]

➽ ጌታችን አላህ በዚህ አንቀፅ መልዕክተኛው ﷺ ያመጡትን በቻልነው እንዲንተገብር፤ የከለከሉትንም ከመፈፀም እንዲንቆጠብ ያስገነዝበናል። ቢድዓ ደግሞ መልዕክተኛው ﷺ የከለከሉት ነው።

فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَن تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡
[ሱረት አል-ኑር፣ - 63]

➼ የመልዕክተኛውን ﷺ ትዕዛዝ መጣስ መከራ እና አሳማሚ ቅጣት ያከናንባል። ቢድዓ ደግሞ መልዕክተኛውን ትዕዛዝ መጣስ ነውና እንጠንቀቅ!!!

የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"إياكم ومحدثات الأمور فإن كل محدثة بدعة، وكل بدعة ضلالة، وكل ضلالة في النار"
“እናንተንም አዳዲስ ፈጠራዎችንም አስጠነቅቃችኃለሁ፤ ማንኛውም አዲስ ፈሊጥ ፈጠራ ነው፡፡ አዲስ ፈሊጥ ደግሞ ጥመት ነው፤ ማንኛውም ጥመት ደግሞ የእሳት ነው፡፡”
ኢማሙ አህመድና ሌሎችም ዘግበውታል

በሌላ ሀዲስ ደግሞ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈውልናል፦

[من عمل عملا ليس عليه ﺃمرﻧﺎ فهو ﺭﺩ]
["የኛን ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ተመላሽ ነው"]
(ሙስሊም : 1718)

ልብ እንበል ረሱል ﷺ በቢድዓ ላይ አላዘዙንም። ስለዚህ ባላዘዙበት ስራ መሰማራት ስራችንን ተመላሽ ያደርገዋል።

➲ ዒርባድ ኢብኑ ሳሪያህ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ባስተላለፈው ሐዲስ ላይም ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ፦ [አዳዲስ ፈጠራዎችን አደራችሁን ተጠንቀቁ፤ ፈጠራ ሁሉ ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው።]
(አቡዳውድና ቲርሚዚይ)

➩ ቢድዓን አስመልክቶ ከሰለፎች ንግግር የተወሰነ ለመመልከት ያክል፦
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር - ረዲየሏሁ ዐንሁማ - እንዲህ ይላሉ፦
"ቢድዓ ሁሉ ፈጠራ ናት፤ ምንም እንኳን ሰዎች መልካም ነች ብለው ቢያዩዋትም።"
አልላለካኢይ "ሸርሑስ-ሱንና" 1/92) ላይ ዘግበውታል።

ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
"ተከተሉ፤ አዲስን ነገር (ቢድዓን) አትፍጠሩ፤ በእርግጥም ተብቃቅታችኋል፤ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው"
አድ-ዳሪሚ 211 ላይ ዘግበውታል።

ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - በሌላ ቦታ እንዲህ ይላሉ፦
"በሱንና ላይ ማሳጠር(መብቃቃት) በቢድዓ ላይ ጥረት(ትግል) ከማድረግ ይበልጣል፤ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው።"
አልላለካኢይ "ሸርሑስ-ሱንና" 114 ላይ ዘግበውታል።

ኢማሙ ማሊክ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦
"በእስልምና ውስጥ መልካም አድርጎ የሚያያትን አዲስን ፈጠራ (ቢድዓ) የፈጠረ ሰው፤ በእርግጥም ሙሐመድ - ﷺ - መልእክቱን አላደረሰም በማለት ሞግቷል፤ ምክንያቱም አሏሁ - ተዓላ - [| .. ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡...|] ስለሚል ነው። የዛን ጊዜ ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን ሊሆን አይችልም።
"(ኢብኑሐዝም "አሕካም" 2/231 ላይ ኢማም አሽ-ሻጢቢ 1/49)
ላይ ዘግበውታል።

በአጠቃላይ ከቢድዓ አይነቶች በሙሉ መራቅ ይጠበቅብናል። አላህ ከቢድዓ ርቀው በሱንና ጠንክረው እሱን ከሚገናኙ ደጋግ ባሮቹ ያድርገን
https://t.me/Adnan567mh
673 views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 10:54:04 አንተ ሶላትን የተውከው ወንድሜ ሆይ!!
<===============>

#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!!

ሶላትን ትተህ ከእስልምና ምን ቀረህ? ሶላት የኢስላም ምሰሶ፤ የኢማን መገለጫ -ካባ- መሆኑን አታውቅምን!?

#አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ!

አንተ ስትቀር ሁሉም ፍጥረታት ለጌታቸው
ሰጋጆች ናቸው።

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፡-
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَسْجُدُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ وَالنُّجُومُ وَالْجِبَالُ وَالشَّجَرُ وَالدَّوَابُّ وَكَثِيرٌ مِّنَ النَّاسِ ۖ وَكَثِيرٌ حَقَّ عَلَيْهِ الْعَذَابُ ۗ وَمَن يُهِنِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِن مُّكْرِمٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ ۩
አላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም፣ ለርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን ብዙውም በርሱ ላይ ቅጣት ተረጋገጠበት፡፡ አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን ይሠራልና፡፡
(ሱረቱ አል-ሐጅ - 18)

አንተም የማትሰግድ ከሆነ ከነዚያ
ቅጣት ከተወሰነባቸው አንዱ ትሆናለህ።

#አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ!

#ሶላትን_መተው_ክህደትና (#በአላህ_ላይ) #ማጋራት_መሆኑን_አታውቅምን!?

ነቢዩ ﷺ አንዲህ ብለዋል፡-
«ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺮﺟﻞ ﻭﺑﻴﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻭﺍﻟﻜﻔﺮ ﺗﺮﻙ ﺍﻟﺼﻼﺓ»
‏[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ]
«በሰውየውና በሽርክ ወይም በክህደት መካከል (ያለው) ሶላትን መተዉ ነው።”

« ﺍﻟﻌﻬﺪ ﺍﻟﺬﻱ ﺑﻴﻨﻨﺎ ﻭﺑﻴﻨﻬﻢ ﺍﻟﺼﻼﺓ : ﻓﻤﻦ ﺗﺮﻛﻬﺎ ﻓﻘﺪ ﻛﻔﺮ ‏»
‏[ﺃﺧﺮﺟﻪ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ].
“በኛና በነሱ (በካህዲያን) መሀል ያለው ቃል-ኪዳን (ድንበር) ሶላትን መተው ነው። (ሶላትን) የተወ በእርግጥ ካደ።”

#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!

ሶላትን መተው እንዲሁም (ከሶላት) መዘናጋት ሙናፊቅነት መሆኑን አታውቅም!?
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا
መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ (ይቀጣቸዋል)፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ሰዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም፡፡
(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 142)

ነቢዩም ﷺ በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
«ﺃﺛﻘﻞ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻤﻨﺎﻓﻘﻴﻦ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺸﺎﺀ ﻭﺻﻼﺓ ﺍﻟﻔﺠﺮ، ﻭﻟﻮ ﻳﻌﻠﻤﻮﻥ ﻣﺎ ﻓﻴﻬﻤﺎ ﻷﺗﻮﻫﻤﺎ ﻭﻟﻮ ﺣﺒﻮًﺍ‏» ‏
[ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ ].
“በሙናፊቆች ላይ እጅግ የሚከብደው ሶላት ኢሻዕ እና ሱብሂ ነው። (ሁለቱን በመስገድ) የሚገኘውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን (ወደ መስጊድ) ይመጡ ነበር።”

#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!

እስኪ አስተንትን ሙናፊቆች ለይዩልኝ (ሪያዕ) ቢሆንም እንኳ ይሰግዳሉ፤ አንተ ግን በፍጹም አትሰግድም!!

#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!

ሶላትን መተው ዝንጉነት እና የልብ መድረቅ መሆኑን አታውቅምን!?

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
« ﻟﻴﻨﺘﻬﻴﻦ ﺃﻗﻮﺍﻡ ﻋﻦ ﻭﺩﻋﻬﻢ ﺍﻟﺠﻤﻌﺎﺕ، ﺃﻭ ﻟﻴﺨﺘﻤﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﻗﻠﻮﺑﻬﻢ، ﺛﻢ ﻟﻴﻜﻮﻧﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﻐﺎﻓﻠﻴﻦ»
‏[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ].

“ህዝቦች የጁምዓ ሶላትን ከመተው ይከልከሉ! ወይም አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽግባቸዋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።”

#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!

ሶላትን መተው ስራን ሁሉ እንደሚያበላሽ አልሰማህምን!? የሚከተለውን የነቢዩን
ንግግር ተመልከት።
« ﻣﻦ ﺗﺮﻙ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ ﺣﺒﻂ ﻋﻤﻠﻪ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ].
“የአስርን ሶላት የተወ ስራው በርግጥ ተበላሸበት።”

#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!

ሶላትን መተው ከከሀዲያንና ወንጀለኞች ጋር ለእሳት ቅጣት እንደሚዳርግ አታውቅምን!?

የጀነት ሰዎች የጀሀነም ሰዎችን (ጀሀነም የገቡበትን ምክንያት) ሲጠይቋቸው የሚሰጧቸውን ምላሽ ሲናገር አላህ
እንዲህ ይላል፡-
كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ

ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡
إِلَّا أَصْحَابَ الْيَمِينِ

የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡
فِي جَنَّاتٍ يَتَسَاءَلُونَ

(እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡
عَنِ الْمُجْرِمِينَ

ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡
مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ
(ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»
قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ
(እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡
ሰላትን ወቅቷን ጠብቆ አለመስገድ ሰቀር ለሚባለው የጀሀነም ሸለቆ ውስጥ ለመግባት ሰበብ ይሆናል።

እንዲሁም በሌላ ምዕራፍ አላህ እንዲህ ይላል፦

۞ فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا
ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡
(ሱርቱ መርየም፣ - 59)

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
« ﺍﻟﺬﻱ ﺗﻔﻮﺗﻪ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ، ﻓﻜﺄﻧﻤﺎ ﻭﺗﺮ ﺃﻫﻠﻪ ﻭﻣﺎﻟﻪ‏» ‏
[ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ]
“የአስር ሶላት ያመለጠው ቤተሰቦቹንና ንብረቱን እንደ አጣ (እንደ ተነጠቀ) ነው።”

የአምስቱንም ወቅት ሶላት መተውህስ ምን ያስከትል ይሆን!?

#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!

ሶላትን መተው መረበሽን፣ አለመረጋጋትን፣ ጭንቀትን፤ የኑሮ ጥበትን (እንደሚያመጣ) አታውቅምን!?

አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِي فَإِنَّ لَهُ مَعِيشَةً ضَنكًا وَنَحْشُرُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَعْمَىٰ
«ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡
قَالَ رَبِّ لِمَ حَشَرْتَنِي أَعْمَىٰ وَقَدْ كُنتُ بَصِيرًا
«ጌታዬ ሆይ! ለምን ዕውር አድርገህ አስነሳኸኝ በእርግጥ የማይ የነበርኩ ስኾን» ይላል፡፡

قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتْكَ آيَاتُنَا فَنَسِيتَهَا ۖ وَكَذَٰلِكَ الْيَوْمَ تُنسَىٰ
(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ «ታምራታችን መጣችልህ፡፡ ተውካትም፡፡ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ» ይለዋል፡፡


#ዋ_ንዴትህ! #ዋ_ፀፀትህ!
#አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!

እንዴት ጊዜ ያልፋል፤ እድሜህ (ያለ አግባብ) ይገባደዳል፤ ልብህ
ከጌታህ ተጋርዶ ሳለ!? እንዴትስ በቅርቢቱ አለም (ዱንያ) ከሚገኙት ነገሮች ሁሉ ይበልጥ ጣፋጭ እና ማራኪ የሆነውን
ነገር ሳትቀምስ ዱንያን ትሰናበታታለህ!?

ይህም አላህን በማምለክ፣ በማውሳት፣ በማመስገን እና ለርሱም በመስገድ የሚገኝ ሲሆን።
https://t.me/Adnan567mh
992 views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ