Get Mystery Box with random crypto!

የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የሰርጥ አድራሻ: @adnan567mh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.89K
የሰርጥ መግለጫ

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን✔
JOIN 👇
@Adnan567mh
🌐💚💛❤️

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 18:57:22 አይገርምም!!

የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው።

ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው።

የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው።

«ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው።

ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው።ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው።

ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል።

እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው።

በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱ የበሉት ሌሎች ሰዎች፤ ሰንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው።

ይህ ሁሉ እውነታ እያለ "ነኝ "እና "አልኝ" በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም። እስቲ ያወሰሰብናትን ሕይወትን
ቀለል እናድርጋትና ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር!!
https://t.me/Adnan567mh
82 views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 18:57:22 إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسْتَقَٰمُوا۟ تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا۟ وَلَا تَحْزَنُوا۟ وَأَبْشِرُوا۟ بِٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ
እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ጀነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡

ሱረቱል ፉሲለት 30}
https://t.me/Adnan567mh
87 views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:24:42 فليست هذه الدنيا بشيء ... تسؤوك حقبة وتسر وقتا

وغايتها إذا فكرت فيها ... كفيئك أو كحلمك إن حلمتا

سجنت بها وأنت لها محب... فكيف تحب ما فيه سجنتا



ምንም አየደለችም የዱንያዋ ህይወት
ዘመን አስደስታህ ታዝናለህ ሌላ ወቅት

ድካዋ'ኮ የሧ ስታስተነትናት
ወይ እንዳንተ ጥላ ወይ እንደ ህልምህ ናት

ታሥረሃል በውስጧ የሷ ወዳጅ ሆነህ
የታሰርክበትን እንዴት ትወዳለህ?!


ከታኢየቱል ኢልቢሪ የተወሰደ
https://t.me/Adnan567mh
216 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:33:26 እውነተኛውን ሞት ከመሞትህ በፊት አትሙት!!
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈

የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦

«የዚያ አላህን የሚያወሳውና የማያወሳው ምሳሌ ልክ እንደሟችና እንደህያው ነው።»

ወንድሜ አላህ ከማውሳት በመዘናጋት ከመሞትህ በፊት አትሙት። በቆምክበትም፣ ቁጭ ባልክበትም፣ ተጋድመህም፣ እየተጓዝክም፣ እየሰራህም፣ በእረፍትህም ሰአት፣ ብቻህንም ሁነህ፣ ከሰው ጋርም ሁነህ

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

308 views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:23:04 ጥሩ ምክሮች!ለብልሆች! አንብበው ሚለወጡበት
ሱረቱል ከህፍን አርብ አርብ የቀራ ከደጃል ተንኮል
ይጠበቃል
ሱረቱል ሙልክን ሁሌ ማታ ማታ የቀራ ከቀብር ፈተና
ይጠበቃል
ሱረቱል ዋቂዐን ሁሌ ማታ ማታ የቀራ ከድህነት
ይጠበቃል
ሱረቱል ኢኽላስን ሶስት ጊዜ የቀራ ቁርዐንን
እንዳከተመ
ይቆጠራል
ሀያተል ኩርሲን እና ሱረቱል ኢኽላስ፣ፈለቅ እንዲሁም
ሱረቱል ናስን ማታ ማታ ወይም ጠዋት ላይ የቀራ
ከሸይጣን
ተንኮል እንጠበቃለን
የኢሻን ሠላትና የሱብሂን ሠላት በጀምዐ የሠገደ
ለሊቱን
በሙሉ እየሠገደ እንዳደረ ይቆጠራል
የሱብሂን ሠላት ሰግዶ ጎህ እስኪቀድ ድረስ አዝካሮችን
እያለ የተቀመጠ ሀጅ እንዳደረገ ይቆጠርለታል
የረመዳንን ፆምና የሸዋልን 6ቱን ቀን የፆመ አመቱን
በሙሉ እንደፆመ ይቆጠራል ኢንሻእአላህ ሁላችንም
አንብበን የምንጠቀምበት ሠዎች ያድርገን!
https://t.me/Adnan567mh
443 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 21:38:29 #የጠቢባን_ንግግር *ክፍል አንድ*

*هناك شخص تحترمه لأنه محترم، وهناك شخص تحترمه لأنك محترم.
ስለተከበረ የምታከብረው እና ስለተከበርክ የምታከብረው ሰው አለ።

*ليس من العدل أن تطلب من الآخرين ما لست مستعدا لفعله.
ለማድረግ ዝግጁ ያልሆንክበትን ነገር ከሌሎች መጠየቅ ፍትሐዊነት አይደለም።

*بعض الناس يبحثون عن مكان جميل
والبعض الآخر يجعل المكان جميل
አንዳንድ ሰዎች የሚያምር ቦታ ይፈልጋሉ፣ ሌሎች ደግሞ ያሉበትን ቦታ ውብ ያደርጋሉ።

*وأنت في طريقك للبحث عن حياة فلا تنسى أن تعيش
በመንገድህ ላይ ህይወትን ስትፈልግ መኖርን አትርሳ።

*الكثير متزوج .. لكن القليل لديه "شريك" حياة.
ብዙዎች ያገቡ ናቸው፤ የህይወት አጋር ያላቸው ግን ጥቂቶች ናቸው።

*من باب الأدب استمع للبشر جيداً، أما من باب الإحتياط فلا تصدق كل مايقولون .
እንደ ስነ-ምግባር ሰዎችን በጥሞና አዳምጥ፤ ለቅድመ ጥንቃቄ ግን የሚናገሩትን ሁሉ አትመን።

*وتعظم في عين الصغير صغارها وتصغر في عين العظيم العظائم.
በትንሽ ዓይን ትንሽ ነገር ትልቅ ይሆናል፤ በትልቅ ዓይን ትልቅ ነገር ትንሽ ይሆናል።
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

372 views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:23:22 #ባሪያዬ እኔን መገናኘት ከወደደ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿قالَ اللَّهُ: إذا أحَبَّ عَبْدِي لِقائِي أحْبَبْتُ لِقاءَهُ، وإذا كَرِهَ لِقائِي كَرِهْتُ لِقاءَهُ.﴾

“አላህ እንዲህ አለ፦ ባሪያዬ እኔን መገናኘት ከወደደ እኔም እሱን ማግኘትን እወዳለሁ። እኔን መገናኘት ከጠላ ደግሞ እኔም እሱን ማግኘትን እጠላለሁ።”

ቡኻሪ ዘግበውታል: 7504

https://t.me/Adnan567mh
345 views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 10:04:03 የዐዋቂ ምክር ለባለትዳር ጥንዶች…

بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

نصيحة عالم للزوجين

قال الإمام العلامة ابن باز رحمه الله تعالى :

الواجب على الرجل أن #لايستعجل في #الطلاق ؛ وأن #يعاشر_بالمعروف وأن يحذر ظلم المرأة وبخسها حقوقها ..

ታላቁ ኢማም ኢብን ባዝ (ከፍ ያለው አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ አሉ ፦

በአንድ ወንድ ላይ ግዴታ የሚሆነው
ባለቤቱን በመፍታት ላይ አለመቾከሉ ነው።

እንዲሁም በመልካም ሁኔታ ሊኗኗራት
ነው።

ሴቲቱንም ከመደል ሊጠነቀቅ ነው።

(ያላትን) ሐቅም ላያሳንስባት ነው !

والواجب على #الزوجة_التواضع وعدم إغضاب الزوج وعدم إيذائه، وعليها أن تتواضع وأن تستعمل اللطف والرفق والكلام الطيب مع الزوج حتى لا تثير حفيظته فيطلق .

በርሷም (በባለቤቱ) ላይ ግዴታ የሚሆንባት ለባለቤቷ መተናነስ ነው ።

እንዲሁም ባለቤቷን አለማስቆጣትና
አለማስቸገርም ነው።

በርሷ ላይ ያለባት ለሱ መተናነስ ስትኗኗረው በእዝነትና ለስለስ ባለ ሁኔታ ላይ መሆን ነው።

እንዲፈታት በመጠባበቅ ላይ እስከ
ማትመርጥ ድረስ ከባለቤቷ ጋር መልካም
ንግግርን መነጋገር ነው ያለባት !

وعلى الجميع الصبر والاحتساب في جميع الأحوال ..

كما قال سبحانه وتعالى :

« إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ » ( الزمر : ١٠)

فلا بد من الصبر على بعض العوج .. ولا بد للمرأة أن تصبر أيضاً على ما قد يقع من الزوج من بعض الخلل أو بعض التقصير وما أشبه ذلك .

مجموع الفتاوى/٤٧١٣ .

ባጠቃላይ ሁላቸውም ላይ ያለባቸው በሁሉም ሁኔታቸው ላይ ታጋሽ መሆንና
(ከአላህ) ጋር ሒሳባቸውን መተሳሰብ
ነው።

ልክ አላህ እንዳለው ፦

(( " (እነዚያ) ታጋሾች (አላህ ዘንድ)
ያላቸው ምንዳ ከትስስብ ውጪ
ነው። " ))
【አል–ዙመር (10)】

(ለወንድ ልጅ) ከፊሉ ጥመት አለው በተባለው (የሴት ልጅ አፈጣጠር ላይ …) ትዕግስት ማድረጉ ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው !!!

እንዲሁም በሴቲቱ ላይም በድጋሚ ከባለቤቷ በሚገጥማት አንዳንድ ክፍተቶች ፥ ጉድለቶችና የመሳሰሉ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ታጋሽ መሆኗ ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው !!!

(አል–ፈታዋ / 4713)

[ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ
ቢን ባዝ]
https://t.me/Adnan567mh
389 views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:58:55 #ተውሒድ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

 ﴿أتانِي جِبْرِيلُ عليه السَّلامُ، فَقالَ: مَن ماتَ مِن أُمَّتِكَ لا يُشْرِكُ باللَّهِ شيئًا دَخَلَ الجَنَّةَ،﴾

“ጅብሪል (عليه السلام) መጣና እንዲህ አለኝ፦ ከህዝቦችህ በአላህ ላይ ምንም ሳያጋራ የሞተ ጀነት ገባ።”

ቡኻሪ ዘግበውታል: 2388

ጆይን፡‐https://t.me/Adnan567mh
525 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 11:31:47 7ቱ_ቁርአን_ውስጥ_የተጠቀሱ_ከንቱ_ምኞቶች

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ تُرَٰبًۢا﴾
" ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ "
[ሱረቱ ነበእ 40]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى قَدَّمْتُ لِحَيَاتِى﴾
" ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራን) ባስቀደምኩ ኖሮ "
[ሱረቱል ፈጅር 24]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى لَمْ أُوتَ كِتَٰبِيَهْ﴾
" ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ "
[ሱረቱል ሃቀህ 25]

⇦ ﴿يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًۭا﴾
" ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ "
[ሱረቱል ፉርቃን 28]

‏⇦ ﴿يَٰلَيْتَنَآ أَطَعْنَا ٱللَّهَ وَأَطَعْنَا ٱلرَّسُولَا۠﴾
" ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ "
[ሱረቱል አህዛብ 66]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى ٱتَّخَذْتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلًۭا﴾
" ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ "
[ሱረቱል ፉርቃን 27]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًۭا﴾
" ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ "
[ሱረቱ ኒሳእ 73]

☞ ሁሉም የሟቾች ምኞት ናቸው
ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው
ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው
ጥሩን ነገር መስራት ነው ...

☞ ቀብር ገብተህ/ሽ አንተም.አንቺም ይህን
ከምትመኝ/ኚ ነፍስህ/ሽ አካልህ/ሽ ውስጥ
እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም/ሚ።

አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ
ጠብቀን ያረብ!
ሼር ጆይን ተቀላቀሉ
https://t.me/Adnan567mh
597 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ