Get Mystery Box with random crypto!

የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የሰርጥ አድራሻ: @adnan567mh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.89K
የሰርጥ መግለጫ

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን✔
JOIN 👇
@Adnan567mh
🌐💚💛❤️

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-21 09:25:50 ጥሩ ነገር መስራት ለሰው
በጎ ወዳጅ መሆን!!!
==================>
يقول رب العزة.
وأحسنوا إن الله يحب المحسنين
በጎ አድርጉ በጎ አድራጊዎችን አሏህ ይወዳቸዋልና።
ويقول هل جزاء الإحسان إلا الإحسان
የበጎ ነገር ምንዳ በጎ እንጂ ይሆናልን?

ኢብኑል ቀይም አሏህ ይዘንለት አንዲህ ይላል፦
ﻓﻠﻴﺲ ﻟﻠﻘﻠﺐ ﺃﻧﻔﻊ ﻣﻦ ﻣﻌﺎﻣﻠﺔ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺑﺎﻟﻠﻄﻒ ﻭﺣﺐ ﺍﻟﺨﻴﺮ ﻟﻬﻢ ﻓﺈﻥ ﻣﻌﺎﻣﻠﺔ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺑﺬﻟﻚ؛ ﺇﻣﺎ ﺃﺟﻨﺒﻲ ﻓﺘﻜﺘﺴﺐ ﻣﻮﺩّﺗﻪ، ﻭﺇﻣﺎ ﺻﺎﺣﺐ ﻓﺘﺴﺘﺪﻳﻢ ﺻﺤﺒﺘﻪ، ﻭﺇﻣﺎ ﻋﺪﻭٌّ ﻓﺘُﻄﻔﺊ ﺑﻠﻄﻔﻚ ﺟﻤﺮﺗﻪ، ﻭﻣﻦ ﺣﻤﻞ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻤﺤﺎﻣﻞ ﺍﻟﻄﻴﺒﺔ ﻭﺃﺣﺴﻦ ﺍﻟﻈﻦّ ﺑﻬﻢ ﺳﻠﻤﺖ ﻧﻴﺘﻪ ﻭﺍﻧﺸﺮﺡ ﺻﺪﺭﻩ ﻭﻋﻮﻓﻲ ﻗﻠﺒﻪ ﺣﺘﻰ ﻳﺤﻔﻈﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﻦ ﻛﻞ ﺳّﻮﺀ ﻭﻣﻜﺮﻭﻩ
ﺃﻧﻈﺮ : ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴﻢ، ﻣﺪﺍﺭﺝ ﺍﻟﺴﺎلكين
【ሰዎችን ለዘብ በማለት አና በመለሳለስ ለነሱ ጥሩን ነገር በመውደድ ከመኗኖር በላይ ለልብ ጠቃሚ ነገር የለም ሰዎችን በዚህ ሁኔታ መገባየት ወይም በዳ የሆነ ሰው ነውና ውዴታውን ያመጣል ወይም ጓደኛ ነው ጓደኝነቱን የዘወትራል ወይም ጠላት ነው በመላዘብህ ምክንያት ልቡ ላይ ያለውን ፊም ታጠፈልህ ሰዎችን በጡሩ አመለካከት የሰፈረ በነሱ ላይ ግምቱን ያስተካከለ ኒያው ሰላም ይሆናል ልቡ ኣፊያ ይሆናል ከመጥፎ እና ከሚጠላ ነገር ሁሉ አሏህ እስከ ሚጠብቀው ድረስ!】
ምንጭ መዳሪጁሣሊኪን

ለሰው ልጆች መልካም መዋል፣ በመልካም ስራ መጥቀም፣ ችግራቸውን ማቃለል፣ ሀዘናቸውንና ሀሳባቸውን መጋራት፣ በሽርክ እና በኩፍር የተዘጉ ልቦችን በቢድዓ ፅልመት የታወሩ አይኖችን፣ ሰዎችን ከሀቅ አይንን ጨፍኖ በመከተል የታመሙ አካሎችን፣ ሰዎች በጥቅሉ ከሉበት ድርቅና እና አፀፋ፣ ወደ ኢስላም ብርሀን እንዲያቀኑ በር ይከፍታል።

➼ የፍትህ፣ የመልካምነትና የእዝነት መንገድ የሆነውን የአላህን ሸሪዓ (የረሱልን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ሱና) ሰዎች በቀላሉ እንድቀበሉ ይረዳል።

ለሰዎች መልካም መዋልን አስመልክቶ ነብዩ እንድህ ይላሉ፦

ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ (صلى الله عليه وسلم) :- ‏" ﺃَﺣَﺐُّ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪِ ﺃَﻧْﻔَﻌُﻬُﻢْ ﻟِﻠﻨَّﺎﺱِ، ﻳَﻜْﺸِﻒُ ﻋَﻨْﻪُ ﻛُﺮْﺑَﺔً، ﺃَﻭْ ﻳَﻘْﻀِﻲ ﻋَﻨْﻪُ ﺩَﻳْﻨًﺎ، ﺃَﻭْ ﻳَﻄْﺮُﺩُ ﻋَﻨْﻪُ ﺟُﻮﻋًﺎ‏)
ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﻄﺒﺮﺍﻧﻲ، ﻭﺣﺴﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ‏

አብደላህ ኢብኑ ዑመር ረዲያላሁ ዐንሁ እንድህ ሲል ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘግቧዋል።

"አላህ ሱብሃነሁ ወታዓላ ዘንድ በጣም ተወዳጁ ሰዉ ለሰዎች ጠቃሚ ( መልካም የሚውል)፣ ችግር የሚቀርፍ፣ እዳን የሚከፍል ወይም ረሀብን የሚያስወግድ ሰው ነው ብለዋል።"

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم :-
"ﺃَﺣَﺐُّ ﺍﻟْﻌﺒﺎﺩِ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪِ , ﺃَﻧْﻔَﻌُﻬُﻢْ ﻟِﻌِﻴَﺎﻟِﻪِ"
ﺃﺧﺮﺟﻪ ﺃﺑﻮ ﻳﻌﻠﻰ ، ﻭﺣﺴﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ .

"አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ በላጩ ለቤተሰቡ ጠቃሚው ነው"

➨ አላህ በእርግጥ መልካም መስራትን አዟል። ስኬታማነትንም ከመልካም ስራ ጋር አቆራኝቶታል።

{وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩} [ الحج :77]
አላህ እንዲህ ሲል ከልፆታል
"በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና፡፡"

ﻭﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻣﻮﺳﻰ ﺍﻷﺷﻌﺮﻱ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ - ﻗﺎﻝ : "ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ صلى الله عليه وسلم :- ‏( ﺃَﻃْﻌِﻤُﻮﺍ ﺍﻟﺠَﺎﺋِﻊَ، ﻭَﻋُﻮﺩُﻭﺍ ﺍﻟﻤَﺮِﻳﺾَ، ﻭَﻓُﻜُّﻮﺍ ﺍﻟﻌَﺎﻧِﻲَ"
‏ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ‏.

አቡሙሳ ረዲየላሁ ዐንሁ እንድህ ሲሉ ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዘግበዋል።

"የተራበን አብሉ፣ የታመመን ጠይቁ፣ እስረኛንም ፍቱ!"

➲ ከነዚህ ሀድሶች የምንረዳው ቁምነገር ለሰው ልጆች መልካም መዋል ( ኢህሳን ኢላ ኸልቂላህ) እየተረሳ የመጣው የእስልምና ስርኣት ነው።

ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴﻢ: ‏ ﻣﻦ ﺭَﻓَﻖَ ﺑﻌﺒﺎﺩِ ﺍﻟﻠﻪ ﺭَﻓَﻖَ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻪ، ﻭﻣﻦ ﺭﺣﻤﻬﻢ ﺭﺣﻤﻪ، ﻭﻣﻦ ﺃﺣﺴﻦ ﺇﻟﻴﻬﻢ ﺃﺣﺴﻦ ﺇﻟﻴﻪ، ﻭﻣﻦ ﺟﺎﺩ ﻋﻠﻴﻬﻢ ﺟﺎﺩ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ، ﻭﻣﻦ ﻧﻔﻌﻬﻢ ﻧﻔﻌﻪ، ﻭﻣﻦ ﺳﺘﺮﻫﻢ ﺳﺘﺮﻩ، ﻭﻣﻦ ﻣﻨﻌﻬﻢ ﺧﻴﺮﻩ ﻣﻨﻌﻪ ﺧﻴﺮﻩ، ﻭﻣﻦ ﻋﺎﻣﻞ ﺧﻠﻘﻪ ﺑﺼﻔﺔٍ ﻋﺎﻣﻠﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﺘﻠﻚ ﺍﻟﺼِّﻔﺔ ﺑﻌﻴﻨﻬﺎ ﻓﻲ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﻭﺍﻵﺧﺮﺓ، ﻓﺎﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻟﻌﺒﺪﻩ ﺣﺴﺐ ﻣﺎ ﻳﻜﻮﻥ ﺍﻟﻌﺒﺪ ﻟﺨَﻠﻘِﻪ
ﺍﻟﻮﺍﺑﻞ ﺍﻟﺼﻴﺐ ﻻﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴﻢ
አብኑል ቀይም አላህ ይዘንለት እና እንዲህ ይላል "በአላህ ቦሮች ላይ የራራ አላህ ይራራለታል በነሱ ያዘነ አሏህ ያዝንለታል፣ ለነሱ በጎ የደረገ በጎ የደርግለታል፣ ለነሱ ከለገሰ አላህ በሱ ላይ ይይለግሳል፣ የጠቀማቸው ይጠቀመዋል፣ የደበቃቸው ይደብቀዋል፣ የራሳቸውን ኸይር የከለከላቸው ኸይሩን ይከለክለዋል፣ ቤተኛውም አይነት በሀሪ በሮችን ከተኗኖራቸው (ከተገበያቸው) በዛች አይነት አላህ ይገባየዋል በዱንያም እና በአኼራ አላህ ለባሮቹ ይሆናል በሪያው ለአላህ ኽልቅ በሚሆንበት አይነት።
ምንጭ አል ዋቢሉሠይብ ለኢብኑል ቀይም

በእኛ ቦታ የሌሎች እምነት ተከታዮች የተቸገሩትን እንርዳ በሚል ሰበብ በሰፊው የተሰማሩበት የእለት ተለት ተግባራቸው አድርገውታል። በእርዳታም ምክንያት ብዙ ወገኖቻችንን ከእምነታቸው እያስወጧቸው ነው።

➩ ከፊሎቹ እንደ እኽዋን አልሙስሊሚን ያሉት አላህ ይጠብቀንና ለተቸገሩ፣ ለተራቡ፣ ለታረዙ፣ ቤት ለሌላቸው፣ ትዳር ለሌላቸው እንድረስ በሚል ስም የሙስሊሞችን ገንዘብ በያ ቦታው እያሟጠጡ ለቢሮዋቸው፣ ለቤታቸው ለኪሳቸው፣ እና ትክክለኛውን ደእዋ ለማስመታት የቢዝነስ ማሰባሰቢያ መንገድ አድርገውታል።

➪ ይህ ችግር እንዳይታይ እና ሰዎቹ እንዳይነቁ ለማድረግ የሆነች ቦታ ላይ የማብላት፣ የመስፈጠር፣ አደረግን ለማለት ቪዲዮ በማሰየት ይደበቃሉ።
ይህ ተግባር ከሌብነት በስም እንጂ በምንም ያነሰ አይደለም።

➽ ይህንን ችግር እንዲያስተካክሉ አላህን እዲፈሩ በተባሉ ግዜ ልክ የራሳቸውን ገንዘብ ከኪሳቸው አውጥተው እንደሚሰጡ አይነት ሆነው የሰዎችን ስም ለማጥፋት እነኚህ ለራሰቸው ስቁቁን ሆነው ሲያበቁ ሰዎችን ከኸይር ተግባር የርቃሉ ይላሉ። እውነታው ግን እንዲህ አይደለም እህሳን ፍላጎታችን የታዘዝነበት ግዴታችን ነው።
➲ ይህንን ትልቅ የተወደደውን ተግባር ዲራሹን በሚያጠፋ መስመር ሲሰማሩበት አይቶ ዝም ማለት አማናን መብላት ስለሆነ ብቻ ነው። ለጥሩ ተግባር እና በጎ ለማድረግ ብቁነትን አላህ ይወፍቀን።
https://t.me/Adnan567mh
561 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 09:25:50 ☞ #የሴት ፈተና ኢስላምክን እንዲህ ሊያስጥልክ
ይችላልና ተጠንቀቅ **
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ ﺍﻋﻈﻢ ﺍﻷﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺘﻲ ﺗﻨﻘﺺ ﺍﻳﻤﺎﻥ ﺍﻟﺮﺟﻞ
በሚስር(ግብፅ) ከተማ ውስጥ መስጂድን በአዛን
በሰላት አጥብቆ የሚይዝ አንድ ሰው (ሙዓዚን) ነበር። በርሱም ላይ ጥሩ መታዘዝ እና የኢባዳህ ብርሃኖች ይታዩበት ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ መናራህ
ወጣ፡ ታዲያ አዛን ላይ ሆኖ ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ አንዲትን እንስት ይመለከታል ከመቅፅበት
በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቃል ፡

በፍጥነትም እርሷ ወዳለችበት ቤት ይሄድና ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች
#እርሱም፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው
የምፈልገው
#እርሷም ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"
ብላ ጠየቀችው
#እርሱም፡- ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን
መሰባሰቢያ ይዘሺዋል አላት
#እርሷም፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ
ልልህ አልችም አለቸው
#እርሱም፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት
#እርሷም ፡- አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ
(ክርስቲያን) ነኝ አባቴ ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም አለችው"
#እርሱም፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት፡
#እርሷም ፡-እንደዛ ያደረግክ እነደሆን (ክርስቲያን ከሆንክ) እኔም ፍቃደኛ ነኝ (አገባሀለሁ)
ከዚያም ይሄ ሰው እርሷን ለማግባት ሲል ነሳራ
(ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት ተቀመጠ
ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ
ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወደቆ ወዲያኑ # ህይወቱ_አለፈች ፡:
እርሷንም ሳያገኝ እስልምናውን አጥቶ በኩፍር
ላይ ሞተ ። (አል፡ዳኡ ወ’ደዋአ ሊኢብኑ አል፡ቀይም ገፅ 167)

ሰዓይድ ኢብኑ ሙሰየብ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ይል ነበር፡ <<አላህ ሱብሀነ ወተዓላ አንድንም ነብይ አላከም፡ሸይጣን በሴት ፈተና ሲያጠፋቸው ከነርሱ ላይ ተስፋ ባይቆርጥ እንጂ>>
(መውሱዓቱ ኢብኑ አቢ ዱንያ ቅጽ 4 ገፅ 540)
አል-ሀሰን ኢብኑ ሳሊህ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ሲል ይናገራል፡ <<ሸይጣን ለሴት ልጅ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ፡አንቺ የኔ ግማሽ ጎኔ ነሽ፡እኔ በአንቺ
የምወረውርብሽ ቀስቴ ነሽ ደግሞም ባንቺ
ከወረወርኩ አልስተም፡እንቺ የሚስጥሬ ቦታ ነሽ፡አንቺ የኔ የጉዳዬ መልክተኛ ነሽ>>
(መውሱዓቱ ኢቡኑ አቢ ዱንያ ቅፅ 4 ገፅ 539)

ለወንድ ልጅ ከባዱ ፈተና የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ ፈተና በኋላዬ አልተውኩም
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)


------------------
https://t.me/Adnan567mh
657 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 12:20:43 #አንድ_አፍታ

ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ

#share #share #share #share
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
#ልጄ_ሆይ ፧ በዝምታየ ተፀፅቼ አላውቅም ፡፡
•••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ከጠጣህበት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አታስገባ፡፡
•••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ምላስክን ‘አላህ ሆይ ‘ ማለትን አለማምድ ለአላህ ጠያቂን የማይመልስበት ሰዓታት• አሉትና፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ፧ ከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች ፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ከመገረም ጋር አትሳቅ; ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ሁለት ነገሮችን አታውሳ ፧ ሰዎች ወዳንተ ያደረጉትን በደልና ፣ ለሰዎች ያደረከውን መልካም ነገር፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ በጣም ጣፋጭ አትሁን ከንቀት እንዳትበላ መራራ አትሁን እንዳትተፋ ፡፡
•••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ አትመገብ ; ከምትመገበው ለውሻ ብጥለው የተሻለ ነው ፡፡
••••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ የአላህን ፈራቻ ንግድ አድርገህ ያዘው ; ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ ይመጣልሀል፡
https://t.me/Adnan567mh
599 views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 15:55:19 የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሙአዝ እንዲህ ብለውታልል።

ሙአዝ ሆይ! በአላህ ይሁንብኝ እወድሀለሁ። ሙአዝ ሆይ! አንድ ነገር አደራ ልበልህ ከእያንዳንዱ ሰላት በኋላ
"اللهم أَعني على ذڪرك، وشڪرك، وحسن عبادتك
" አሏሁመ አዒኒ ዓላ ዚክሪክ ወሹክሪክ ወሁስኒ ዒባደቲክ"
"አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አንተን በመልካም በማምለክ ላይ አግዘኝ" ማለትን እንዳትተው።
(صحيح الجامع للألباني ٧٩٦٩)
ሸዳድ ብኑ ዓውስ (አሏህ ስራውን ይውደድለትና) ነብዩ (ሶሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሗቸው ይላል "
وفي حديث شدَّاد بن أوس رضي الله عنه: سمعت رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم يقول: ((إذا كنز الناس الذهب والفضة، فاكنزوا هؤلاء الكلمات: اللهمَّ إني أسألك الثبات في الأمر، والعزيمة على الرشد، وأسألك شكر نِعمتك، وأسألك حسن عبادتك، وأسألك قلبًا سليمًا، وأسألك لسانًا صادقًا، وأسألك من خير ما تعلم، وأعوذ بك من شرِّ ما تعلم، وأستغفرك لما تعلم، إنك أنت علام الغيوب))
"ሰዎች ወርቅና ብር ሲያከማቹ እናንተ እነዚህን ንግግሮች አከማቹ:-
አሏህ ወይ!
በነገሮች ላይ ፅናትን፣ቅኑ መንገድ ላይ ቁርጠኝነትን እጠይቅሃለሁ፣
ፀጋህን ማመስገንን እጠይቅሃለሁ፣አንተን በመልካም ማምለክን እጠይቅሃለሁ፣
ንፁህ የሆነች ቀልብን እጠይቅሃለሁ፣እውነተኛ ምላስን እጠይቅሃለሁ፣
አንተ ከምታቀው መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፣አንተ ከምታቀው ሸር ነገር ባንተ እጠበቃለሁ፣
ለምታቀው ነገር ምህረትክን እጠይቅሃለሁ፣ አንተ ኸይብን እጅግ በጣም አዋቂ ነህ"።
ኢማሙ አህመድ(4/123) እና ሌሎች ዘግበውታል
https://t.me/Adnan567mh
696 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 11:48:41 ዚክር ኢማንን ያጠነክራል።

ሸህ አብዱረህማን አሰአድይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

ዚክር ቀልብ ውስጥ የኢማን ዛፍ ይተክላል። ይንከባከበዋል። ያፋፋዋልም። አንድ ባሪያ አላህን ማውሳት በጨመረ ቁጥር ኢማኑ ይበልጥ እየጠነከረ ይሄዳል።

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

827 views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 09:03:44 ከ̎ነ̎ብ̎ዩ̎ ﷺ̎ የተነገሩ ለሰው ልጅ መድሃኒት የሆኑ 30
ንግግሮች
===============================================================

1 " [ፀሐይ በመግቢዋ እስከምትወጣ ድረስ ወደ አላህ የተመለሰ (የተፀፀተ) አላህ ይቀበላዋል ]
.
2 " [እውቀትን ፈልጎ መንገድን የገባ ሰው፤ አላህ ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድ ያገራለታል]
.
3" [ከመልካም ነገር ምንንም አትናቅ፤ ወንድምህን
በፈገግታ ፊት መገናኘት እንኳን ቢሆን]
.
4" [ ከኔ አንድንም አንቀፅ ብትሆን አድርሱ]
.
5" [ ወደ መልካም የተጣራ የተከተሉት ሰዎች ምንዳ ሳይቀነስ የነሱንም ምንዳ ለሱ ይሆንለታል ፤ ወደ ጥመት የተጣራ የተከተሉት ሰዎች ወንጅል ሳይቀነስ የነሱን ወንጀልም በሱ ላይ ይሆናል]
.
6" [ ከእናንተ መካከል መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይር፣ ያልቻለ በምላሱ ፣ ያልቻለ በልቡ , ይህም የእምነት ደካማው ደረጃ ነው]
.
7" [ ከእናንተ በላጫችሁ ቁርአን የተማረና ያስተማረ ነው]
.
8" [ ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው እስካላመናችሁ ጀነት አትገቡም፣ እስካልተዋደዳችሁ ድረስ አታምኑም ።
ብትሰሩት የምትዋደዱበት የሆነን ነገር ላመላክታችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አብዙ ]
.
9" [ ከተቸገረ ሰው ላይ ችግሩን ያቀለለ አላህ በዱንያም በአኼራም ያቀለለታል ]
.
10" [ ሲሸጥ ፣ ሲገዛ ሆነ ሲፈርድ ይቅር ያለ አላህ
ይዘንለት]
.
11" አንድ ባሪያ አንድን ባሪያ በዱንያ ላይ ገመናውን አይደብቅለትም አላህ በአኼራ የደበቀለት ቢሆን እጂ]
.
12" [ ዝምድና ከዓርሽ ተንጠልጥላ፥ የቀጠለኝ አላህ ይቀጥለው የቆረጠኝ አላህ ይቁረጠው ;ትላለች]
.
13 " [ በእውነት ላይ አደራ ፤ እውነት ወደ መልካም
ይመራል መልካምም ወደ ጀነት ይመራል ]
.
14" [ እኔና የቲሞችን የሚንከባከብ በጀነት ውስጥ
እንደዚህ ነን ፥ -መካከለኛዋን እና ጠቋሚ ጣታቸውን አጣምረው እያመላከቱ]
.
15 "[ እሱ የሚወሳበትን የአላህን ቤት ያስገነባ ሰው አላህ ለሱ በጀነት ውስጥ ቤትን ይገነባለታል]
.
16 "[ ህዝቦቼን አስቸግራለሁ ብየ ባልሰጋ ኖሮ፥ ከሁሉም ሰላት (በፊት) በሲዋክ ባዘዝኳቸው ነበር]
.
17 "[ ሁለት ብርዳማ ሳላቶችን የሰገደ ጀነት ገባ ;
(የፈጅር እና ዓስር ሰላት)]
.
18 "[ አንድ ሰው ወንጀል ሰርቶ;ከዚያም ታጥቦ ሰላት ሰግዶ ምህረትን አይጠይቅም ምህረት የተደረገለት ቢሆን እንጂ]
.
19 " [ አንድ ባሪያ ለአላህ ብሎ አንድ ቀን አይፆምም አላህ ሰባ አመታትን ከጀሃነም ያራቀው ቢሆን እንጂ]
.
20" [ ምፅዋት ስህተትን ታጠፋለች ውሃ እሳትን
እንደምታጠፋው]
.
21" [ ከዑምራ እስከ ዑምራ በመካከላቸው ያለውን
ያስምራል; 'ትክክለኛ' ሐጅም ምንዳው ጀነት ነው]
.
22 " [በሁለት እግሮቹና በሁለት ፂሞቹ (ከንፈሮቹ) መካከል ያሉትን ዋስትና የሚሰጠኝ ጀነትን ዋስትና እስጠዋለው]
.
23 " [ አንድ ሰው የተጠማን ውሻ አይቶ ከመጣማቱ የተነሳ አፈር ሲልስ ተመልክቶ በጫማው ውሃ በመቅዳት አጠጣው አላህም ስራውን ወደደለት ጀነትም አስገባው]
.
24 " [ ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሰላቷን ከሰገደች ፣
ረመዳንን ከፆመች ብለቷን ከጠበቀችና ባሏን ከታዘዘች በፈለገችበት የጀነት በር ግቢ ትባላለች]
.
25 " ከልቡ 'ላ ኢላሃ ኢለላህ ' (ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ) ያለ ጀነት ገባ]
.
26 " [በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር ፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር ፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር አልያም ዝም ይበል ]
.
27 "[ ከሰዎች ሁሉ በላጩ ይበልጥ ለሰዎች ጠቃሚው ነው]
.
28 " [ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆነህ አላህን ፍራ፥
ከመጥፎ ስራ በኃላም መልካምን አስከትል ታብሳታለች ፤ ሰዎችንም በመልካም ስነምግባር ተኗኗር]

29" [ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሳይሆን በቁጣ ጊዜ ነፍሱን የሚቆጣጠር ነው ]
.
30 " [ በኔ ላይ አንድን ሰላት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስርን ያወርዳል ]
https://t.me/Adnan567mh
1.2K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 09:27:37 ❥::::::::የዛሬዉ ስራህ::::::::::❥

የዛሬው ስራህና ድካምህ (ለአኺራ)
ነገ ከፊት ለፊትህ የሚሮጠው ብርሃንህ
ክብርህ ፣ ላንተ ቅርብና ያንተ ብቻ ነው
በሰራህ ልክም ብርሃኑ ይጨምራል ።

(يَوْمَ تَرَى الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ يَسْعَىٰ نُورُهُمْ بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِمْ)
"
ምእመናንንና ምእምናትን በስተፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ምንዳ አልላቸው) ፡፡"
[አልሀ-ዲድ 12]

:::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

898 views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 15:59:28 → የዚና ወንጀል በቀብር ውስጥ ያለው ቅጣት ←



«ከሞት በኋላ የሚያጋጥማችሁን ነገር ብታውቁ ኖሮ ምግብም መጠጥም ባላሰኛት የምትጠለሉበት ቤትም ባላስፈለጋችሁ ወደሜዳ ወጥታችሁ ደረታችሁን እየመታችሁ ስለራሳችሁ ባለቀሳችሁ ነበር፡፡ ተቆርጣ የምትበቅል ተከል ብሆን እወድ ነበር።»(ታላቁ ሰሓባ አቡ ደርዳእ /ረድየላሁ አንሁ)

የነዚያ ከዚና ወንጀል ተውበትን ሳያደርጉ የሚሞቱ ግለሰቦች ቅጣት ከመቃብራቸው ውስጥ ይጀምራል፡፡ በረጅም ሐዲሥ ውስጥ እንደተዘገበው አንድ ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ሕልም ማየታቸውን ተናገሩ፡፡ ከርሳቸውም ጋር ሁለት ሰዎች(ጂብሪልና ማሊክ በሰው ሱረት ሆነው)ነበሩ፡፡ ሁለቱ ሰዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ኃጢአተኞች በሞትና በፍርዱ ዕለት መካከል ባለው ሕይወት ውስጥ ሲቀጡ እንደነበረ ያሳዩዋቸው ጀመር፡፡ ይህንኑ ሲገልጹ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡-

«....በመሬት ውስጥ ያለ ጉድጓድ ዘንድ እስከምንደርስ ድረስም(እንዲሁ እያሳዩኝ)ወደፊት መጓዛችንን ቀጠልንበት፡፡ (ጉድጓዱ) የመጋገሪያ ጉድጓድ ይመስላል፡፡ ከላይ በኩል ጠባብና ከሥሩ ከታች በኩል ደግሞ ሰፊ የሆነ ነው፡፡ ጉርምርምታና ድምፆችም ከርሱ ውስጥ ይወጡ ነበር፡፡ ወደ ውስጡ ተመለከትን። እርቃነ ሥጋቸውን የሆኑ ወንዶችና ሴቶችንም አየናቸው፡፡ ከጉድጓዱ ሥር(ከታች በጣሙን የነደደ እሳት ነበር፡፡ እርሱ ድንገት በነደደ ቁጥርም ወንዶቹና ሴቶቹ ይጮኻሉ፡፡ ወደላይም ከፍ ይላሉ ከሞላ ጎደል ከጉድጓዱ ውስጥ ለመውደቅ እስከሚቀርቡ ድረስ፡፡ እሳቱ እያነሰ በሄደ ቁጥርም ወደ ዳሩ ይመለሳሉ፡፡ እኔም እነዚህ እነማን ናቸው? ስል ጠየኳቸው፡፡ እነርሱም … እነዚያን ራቁታቸውን በጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ወንዶችና ሴቶችን በተለመከተ እነርሱ በዚና ላይ የወደቁ ወንዶችና ሴቶች ናቸው በማለት መለሱልኝ፡፡ …» (ሰሒሕ ቡኻሪ)

በዚሁ በተመሳሳዩ ዘገባ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ ) እንዲህ ማለታቸው ተገልጿል፦(… እነዚያን በአስፈሪ ሁኔታ የተዋጡትን ሰዎች እስከማይ ድረስ ወደፊት መጓዛችንን ቀጠልንበት፡፡ እጅግ በካይ የሆነ ክርፋት አለባቸው፡፡ ክርፋታቸው የሠገራ ቧንቧን ይመስላል፡፡ እኔም እነዚህ እነማን ናቸው? ስል ጠየኳቸው፡፡ እነርሱም እነዚያ የወንድና የሴት ዝሙተኞች ናቸው በማለት መለሱልኝ፡፡» (ኢብን ኹዘይማና ኢብን ሂብባን የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሰሒሕ ነው ብለውታል)

በቀብር ላይ ስላለው ቅጣቶች በተመለከተ እዚህጋ ጨርሻለሁ ኢንሻ አላህ በአኼራ ውስጥ ስላለው ቅጣት ይቀጥላል።


☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

793 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 12:46:34 ምኞቴ አያሳካም ብለህ

ተስፋ አትቁረጥ ከሰከንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነገሮችን መቀየር የሚችል ጌታ አለህና,,,,

ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ ኹን ይለዋል,

ወዲያው ይሆናልም ያሲን፥82
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

854 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 09:24:48 ``✧"አንድ ጊዜ የረገጥነውን ወራጅ ውሃ ዳግም እንደማንረግጠው እናውቃለን። የጊዜም ህግ እንዲሁ ነው። ወደፊት እንጂ ወደኋላ መመለስም ሆነ መቆም አያውቅም። ጊዜ ሁሉን ነገር ያለማቋረጥ ይዞ እየከነፈ ይገኛል። የቆሙ የሚመስሉ ነገሮች በሙሉ በጉዞ ላይ ናቸው ሆኖም ጊዜ በጣም በፍጥነት የሚያስኬዳቸው በመሆኑ እንቅስቃሲያቸውን በስሜታችን ለመጨበጥ እንቸገራለን ጥላችን በሴኮንዶች ነጉደዋል ህፃናት በደቂቃዎች ጨምረዋል። ቡቃያዎች በትንሽ ጊዜ አድገዋል ሆኖም የጊዜ ሥርአት ረቂቅ ከመሆኑ የተነሳበዓይነ ስጋችን ልንቆጣጠረው አንችልም።
ሁላችንም ራሳችን እንፈትሽ

ጊዜውን ለአሏህ ያላደረገ ከህወት ይልቅ ሞት ለሱ የተሻለ ነው። ( ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ)
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

724 views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ