2022-06-30 13:10:03
የዱንያ በላጭ ቀናቶች
ሁለት ወይም አንድ ቀን ብቻ ቀርተውታል
"ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ" የተባሉ የ ዙል—ሒጃ አስርቱ ቀናቶች ሊገቡ በር በማንኳኳት ላይ ናቸው።
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በሓዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
«أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ»
«ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናቶች አስርቱ ቀናቶች ናቸው። =>የዙል_ሒጃ አስር ቀናቶች»
በሌላም ሓዲስ እንዲህ በማለት በእነዚህ ቀናቶች የሚሰራ ስራ ያለውን ደረጃ ያስቀምጣሉ፦
«ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر،
قالوا ولا الجهاد في سبيل الله؟ قال
ولا الجهاد في سبيل الله، إلاّ رجلا خرج بنفسه وماله فلم يرجع من ذلك بشيء»
«ከእነዚህ ከአስር ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ ወደ አላህ የሚወደድበት ቀን የለም አሉ።
ሰሓቦችም
በአላህ መንገድ ላይ መታገል (መጋደል) ቢሆንም? ብለው ሲጠይቋቸው
አዎን! በአላህ መንገድ መታገል ቢሆንም; ግን አንድ ሰው ሲቀር አሉ
እሱም በአላህ መንገድ ለመታገል ነፍሱንም ንብረቱንም ይዞ ወጥቶ እስከ ንብረቱ እዛው የቀረ አሉ።»
እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! እነዚህ ቀናቶች ናቸው እንግዲህ ከፊት ለፊታችን እየመጡ ያሉት።
እንግዲያውስ ለራሱ የሚጨነቅና ንቃተ ህሊና ያለው የሆነ ሰው እንዲህ ዓይነት ብርቅዬ አጋጣሚዎች በከንቱ አያሳልፋቸውም።
እኛንም አላህ ደርሰው ከሚጠቀሙ ያድርገንና ለእነዚህ ቀናቶች አላህ ካደረሰን ከዚህ በፊት ስናደርገው ከነበረው ለየት ባለ መልኩ ለመስራትና ለመጠቀም ራሳችንን ካሁኑ እናዘጋጅ
አላህን አብዝተን በማውሳት
ተህሊል
ተክቢር
ተስቢህ እና
ተህሚድ በማድረግ
ሰደቃን በማብዛት
ቁርኣን አብዝተን በማንበብ
አላህን አብዝተን በመለመን
የጀምዐ ሰላትን በመጠባበቅ
ተጨማሪ(ሱና) የሆኑ ሰላቶችን በመስገድ
የቻልነውን በመፆምእና
አጠቃላይ ኸይር ከተባለ ነገር ሰብስበን ተጠቃሚ ለመሆን ካሁኑ ልንዘጋጅ ይገባናል
ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዳሉት፦
"ብዙሀን ሰዎች የሚገርሙ ናቸው ከረመዷን አሽረል አዋሂር ላይ የቻሉትን ያህል እየታገሉና እየሰሩ ይታያሉ ዙል_ሒጃ ላይ ግን ምንም የተለየ ነገር ሲያከናውኑ አይታዩም።"
ከፊል ዑለማዎች ከረመዷን አሽረል አዋሂር የዙል_ሒጃ አስር ቀናቶች እንደ ሚያስበልጡስ ስንቶቻችን እናቃለን
ምንም እንኳ መስዐላው ሸይኹል ኢስላም ኢብኑል ቀይም እንዳስቀመጡት
«ከለሊቶቻቸው አንፃር የረመዷን አሽረል አዋሂር ሲበልጡ፤
ከቀኖቻቸው አንፃር የዙል_ሒጃ አስር ቀናቶች የሚበልጡ ቢሆንም።
ማለት የፈለኩት ግን
ምን አልባት አላህ በዚህኛው ካደረሰን በቀጣዩ ዓመት ላንደርስበት እንችላለን
ብዙኃን ለአምናው ደርሰው ለዘንድሮው መድረስ እንደ ተሳናቸው
እናም; አላህ ካደረሰን እድሉን ሳንጠቀምበት ሊያልፈን አይገባም።
ማሳሰቢያ
በመጨረሻም ዙል_ቂዕዳ አልቆ ዙል_ሒጃ ሊገባ የተዳረሰ በመሆኑ
ለዒደል_አድሀ ኡዱህያ ማድረግ የሚፈልግ ሰው ካሁኑኑ ዝግጅቱን መርሳት የለበትም
ምክንያቱም ዙል_ሒጃ ከገባ ከፀጉሩና ከጥፍሩ መንካት ስለ ማይፈቀድለት መጨረስ ያለበት ጣጣው ካሁኑ መጨረስ አለበት።
ልክ መልዕክተኛው እንዳሉት
«فأراد أحدكم أن يضحي فلا يأخذن من شعره ولا من بشرته ولا من ظفره شيئا»
«ከእናንተ አንዳቹ ኡዱህያ ለማድረግ ከፈለገ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ ምንም እንዳይነካ (እንዳይቆርጥ)»
አላህ ሚጠቅመንን ያሳውቀን ባወቅነውም ያስጠቅመን
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN
@Adnan567mh
393 views10:10