Get Mystery Box with random crypto!

የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ adnan567mh — የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች
የሰርጥ አድራሻ: @adnan567mh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.89K
የሰርጥ መግለጫ

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን✔
JOIN 👇
@Adnan567mh
🌐💚💛❤️

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-09 21:31:24 ለአላህ ትእዛዝ ሁለየም ዝግጁ ሁን!!

قال رجلٌ لزهير بن نعيم رحمه الله:-أتوصيني بشيء, قال:- نعم احذر أن يأخذك الله وأنت على غفلة.

አንድ ሰው ወደ ዙሀይር ቢን ኑአይም አላህ ይዘንለትና ዘንድ መጥቶ እስቲ በሆነ ነገር ምከሩኝ አላቸው።

እሳቸውም

የተዘናጋህና ችላ ያልክ ሆነህ አላህ እንዳይዝህ ፍራ (ተጠንቀቅ) ብለው አሉት።

(صفة الصفوة ٩/٤)

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

591 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 22:15:14 ለሞተ ሰው ብለን ቁርአን ብንቀራ አጅሩ ይደርሰዋልን

የዚህ ጥያቄ መልስ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ያብራሩታል።

ይህ ተግባር መሰረት የለውም። ለሟች ዱአ ቢደረግለት ይደርሰዋል። ለሱ ተብሎ ቁርአን መቅራት ግን መሰረት የለውም። የሚደነገግ ተግባርም አይደለም። አንድ ሰው ለሟች ሳይሆን ለራሱ አጅር ማግኘትን አስቦ መቅራት አለበት።»

ለሙታኖች አላህ እንዲያዝንላቸውና እንዲምራቸው ዱአ ይደረግላቸዋል። ሰደቃም ይሰጥላቸዋል። ሀጅም ይደረግላቸዋል። እነዚህ ይደርሳቸዋል። አልፎም ይጠቅማቸዋል።

ነገር ግን ለሙታን ተብሎ ቁርአን መቅራትና ሶላት መስገድ ግን መሰረት የሌለው ተግባር ነው። ቢፈፀም ራሱ ለነሱ አይደርሳቸውም። ምክንያቱም ለሞተ ሰው ቁርአን እንደሚቀራለት የሚያሳይ አንድም መረጃ የለምና።

አምልኮቶች በቁርአንና በሀዲስ የተገደቡ ናቸው። የአላህ መልእክተኛ በሀዲሳቸው (የኛን ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ,ስራው, ተመላሽ ነው) ብለዋል። ከነብዩም ሆነ ከአንድም ሶሀባ ለሞተ ሰው ቁርአን ይቀሩ ነበረ የሚል ነገር አልፀደቀም።

ለሞተ ሰው ይበልጥ በላጭና የሚጠቅመው ነገር ምንድ ነው? ተብለው ተጠይቀው «ዱአ ማድረግና ሰደቃ መስጠት ነው። ይህ እጅግ በጣም ይጠቅመዋል» ብለው መልሰዋል።
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

640 views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 12:35:11 ። የነብዩ ”ﷺ” አመጋገብ

1~ነብዪ ሰ ዐ ወ መብላት ከመጀመራቸው በፊት እጃቸውን ይታጠቡ ነበር የሚበሉትም በቀኝ እጃቸው ሲሆን ከፊታቸው ካለው ምግብ ነበር የሚበሉት ፡፡
2>" ነብዩ ሰ ዐ ወ ተደግፈው በልተው አያውቁም ፣
ምግብ ሲበሉ የተለያየ አቀማመጥ ነበራቸው
ሀ/ልክ ተሽሁድ ላይ እንደሚቀመጡ አይነት አቀማመጥ ነበር
ለ/ልክ እንደዚሁ ይቀመጡና የአንድ እግራቸው ጉልበት ደረታቸው ጋር ይደርስ ነበር
ሐ/የውስጥ እግራቸው መሬት ላይ ተለጥፎ ቁጢጥ ይሉ ነበር
3> ነብያችን ሰ ዐ ወ በጠረቤዛም ተደግፈውም ሆነ ወንበር ላይ ተቀምጠው በልተው አያውቁም(ቆዳ ወይም ጨርቅ )መሬት ላይ አንጥፈው ይመገቡ ነበር
4> አብዛኛው ጊዜ ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው (አውራ ጣት ጠቋሚ ጣት እና የመሃል ጣታቸው) በመጠቀም ነው ፡፡ ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ግን የቀለበት ጣታቸውን ጨምረው ይመገቡ ነበር ፡፡
5~ ተመግበው ሲጨርሱ ጣቶቻቸውን አፋቸው ውስጥ ከተው ያፀድዋቸው ነበር ከመሃል ጣታቸው ጀምረው አውራ ጣታቸው ላይ ያቆማሉ ፡፡
6~በገበታው ላይ ያለው ምግብ ከመሃል ጀምሮ የተደረደረ ከሆነ ከፊታቸውና ከስር ካለው ይጀምሩ ነበር
የምግብ በረካ ወደ መሃል እየቀነሰ ይሄዳል ብለዋል ፡፡
7~የነብዩ ሰ,ዐ,ወ በብዙ ሳህን የሚቀርብ የተለያየ አይነት ምግብ አይወዱም ነበር ፡፡
8~የነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሃላዋ (ጣፋጭ)ማር፣ቆምጣጤ፣ተም
ር፣ሀብሀብ፣ኪያር እና
ዝኩኒ ይወዱ ነበር፡፡
9~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የሽንጥ ፣የአንገት አና የትከሻ ስጋ ይወዱ ነበር ፡፡
10~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ከንዳንድ ጊዜሁለት ምግቦችን ይመገቡ፡ነበር ሀባብ እና ተምር ኪያር እና ተምር ..
11~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገቡን ይተውት ነበር፡፡
12~ነብዪ ሰ,ዐ,ወ ያልበሰለ ነጭም ቀይም ሽንኩርት ተመግበው አያውቁም ፡፡
13~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የተነፋ ዱቄት አይበሉም ነበር (ግን
አልከለከሉም )
14~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ተምር ወይም ዳቦ፡ንፁህ ቦታ ላይ ከወደቀ ጠርገው ይበሉ ነበር ፡፡
15~በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም መጀመሪያ ያቀዘቅዙት ነበር አላህ እሳት፡አይመግበንም ይሉ ነበር፡፡
በጣም የሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል ፡፡
, , ,
16~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግብ አሽትተው አያውቁም ጥሩ ያልሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል ፡፡
17~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሲበሉም ሆነ ሲጠጡ ተቀምጠው ነው ፍራፍሬዎችን ቆመውም እየተራመዱ በልተው ነበር፡፡
18~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ አንዳንዴ የበሰለ ስጋን በቢላዋ ቆርጠው ይበሉ ነበር፡፡
, , ,
19~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግብ የያዘን እቃም ሆነ መጠጥ የያዘ መጠጫን ይከድኑ ነበር ፡፡ የሚከድኑት ነገር ካጡ ከላዩ ላይ ስንጥር ያስቀምጡ ነበር፡፡
20~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ማታ የተሰራን ምግብ እስከ ጠዋት ጠዋት፡የተሰራን ምግብ እስከ ማታ፡አያቆዩም ነበር፡፡
(ለሚቀጥለው ምግባቸው በአላህ ይተማመኑ ነበር፡፡)
21~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ስጋ ወደ ቤት ሲያመጡ ለጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያዙ ነበር ፡፡
22~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግብም ላይ መጠጥ ላይ ተንፍሰው (እፍ) ብለው አያውቁም፡፡ ምግብ ላይ መተንፈስ መጥፎ ልማድ አድርገው ይቆጥሩት ነበር፡፡
23~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር ፡፡
* ሼር ይቀጥላል
https://t.me/Adnan567mh
593 views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 09:17:07 ምንኛ ልብ የሚነካ ሀዲስ ነው !!!

------------------------------------------------------
-------------------------------------------------------

አቡዘር አል-ገፋሪ በዘገበው ሓዲስ ነብዩ (ﷺ) ከጌታቸው ሲዘግቡ እንዲህ አሉ፡-

አላህ እንዲህ አለ “ እናንተ ባሮቼ ሆይ! እኔ በደል መፈጸምን በራሴ ላይ እርም አድሪጌዋለሁ። በናንተ መካከልም በደልን መፈጸም እርም አድርጌዋለሁ። ስለዚህ አትበዳደሉ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመራሁት ሲቀር ሁላችሁም ጠማሞች ናችሁ። ስለዚህ ቀጥተኛ መንገድ እንድመራችሁ ለምኑኝ እመራችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመገብኩት ሲቀር ሁላችሁም ረሃብተኞች ናችሁ። እንድመግባቹህ ጠይቁኝ እመግባችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ ያለበስኩት ሲቀር ሁላችሁም እርቃናችሁ ናችሁ። እንዳለብሳቹህ ጠይቁኝ አለብሳችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ ቀንና ለሊት ትሳሳታላችሁ እኔ ደግሞ ወንጀሎችን ሁሉ እምራለሁ። ስለዚህ መሃርታን ጠይቁኝ እምራችኋለሁ።

---------------------------------------------------

-------------------------------------------------------

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተኮ እኔን የመጉዳት ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጉዳት አትችሉም ደግሞም እኔን የመጥቀም ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጥቀም አትችሉም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ጌታን ፈራሂ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይጨምርም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያቹህ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ወንጀለኛ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይቀንስም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ አንድ ሜዳ ላይ ቆመው ቢጠይቁኝና ሁሉንም የጠየቁኝን ብሰጣቸው፥ ይህ ስልጣኔ ላይ ልክ መርፌ ባህር ላይ ገብቶ ከባህሩ እንደሚያጎድለው ቢሆን እንጂ ምንም አያጎድልም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!ስራችሁን ነው የምቆጥርላችሁ ከዛም በስራችሁ መሰረት እከፍላችኋለሁ። መልካምን ያገኘ አላህን ያመስግን ከዚህ ውጭ ሌላን ነገር ያገኘ ግን ራሱን እንጂ ሌላን አይውቀስ።”

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።


=========
=====================

አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን !!!!!!
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

510 views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 13:55:41
የዘንድሮ ታሱዓና ዓሹራ ፆም የፊታችን እሁድና ሰኞ ስለሆነ እሁድንና ሰኞን ወይም ሰኞንና ማክሰኞን ለመፆም እንነይት :: የአሹራ ቀን አላህ ነብዩሏህ ሙሳንና ተከታዮቻቸውን ከፊርዓውን አምባገነናዊ
አገዛዝ ነፃ ያወጣበት ዕለት ነው ።
488 views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 13:42:42 አልሀምዱሊላህ በጧትም በማታ
ቁርኣን ለሰጠኸን ለአዓማቱ ለጌታችን አሏሁ ሱብሃናው ወተዓላ ምስጋና ይገባው
ልብን የሚያርስ ጭንቅን የሚረታ
መቼም ማይጠገብ የአላህ ስጦታ
وَلَقَدْ نَادَانَا نُوحٌ فَلَنِعْمَ الْمُجِيبُونَ
ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!
وَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ
እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡
وَجَعَلْنَا ذُرِّيَّتَهُ هُمُ الْبَاقِينَ
ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ
በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡
سَلَامٌ عَلَىٰ نُوحٍ فِي الْعَالَمِينَ
«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ
እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡
ثُمَّ أَغْرَقْنَا الْآخَرِينَ
ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
۞ وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِ لَإِبْرَاهِيمَ
ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡
إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡
إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَاذَا تَعْبُدُونَ
«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡
أَئِفْكًا آلِهَةً دُونَ اللَّهِ تُرِيدُونَ
«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

545 views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 18:24:11 አንድ ሰው ቤቱን ሳይረከብ፣ የሱ የቱ እንደሆነ ሳያውቅ በፊት በካርታ ወይም በፕላን ላይ ያለን ቤት መሸጥ አይፈቀድለትም። መልዕክተኛው ﷺ "ያንተ ያልሆነን ነገር አትሽጥ" ብለዋል።

105/ የተወሱልን ትርጉም እያወቀ በመልዕክተኛውም ﷺ ሆነ በተከበሩ ወራቶች ለመጥፎ ነገር ተወሱል የሚያደርግ (የሚመጀን) ሰው ይከፍራል።

106/ ሶላት ግዴታ ባይሆን ኖሮ! ብሎ የተመኘ ሰው ፍርዱ ምንድነው? ሸይኽ ረሒመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ "ሶላትን ጠልቶ ከሆነ ይከፍራል፣ ነገር ግን በጣም ከመሳነፉ የተነሳ ከሆነ አይከፍርም"።

107/ ሸይኽ ረሒመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ አንድ ሰው በፎቶው አማካኝነት የሰው ዓይን ሊበላው ይችላል። እናም የናንተንም ሆነ የቤተሰቦቻችሁን ፎቶ አታሰራጩ።

108/ የመልዕክተኛው ﷺ የቀብር አፈር እና የዘመዘም ውሃ መድሃኒቶች ናቸው። ሁለቱም ግን የሚበላለጡበት መንገድ አለ።

109/ መላኢካዎች በፈረስ ወይም በግመል ሊመሰሉ ይችላሉ። ነገር ግን መግደላችን ሱና በሚሆንልን እንስሳዎች አይመሰሉም።

110/ ፉቀሃዎች "እንስሳን በክብደት መሸጥ አይፈቀድም" ብለዋል።

111/ ቁርአን ላይ የጽፈትም ሆነ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ የመሳሰሉትን ማስቀመጥ ሐራም ነው።

.......ይቀጥላል .......

#ምንጭ፦ ከክቡር ዶ/ር ሸይኽ ነቢል ሸሪፍ
አል-ሑሰይኒይ (ሐፊዘሁሏህ)
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

664 views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 17:21:07 የቀብር ሲህር
(በ ዶ/ር አቡ ፈርሀን)
አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ከጅኖች ትንኮሳ ሸይጧናትን ከሚያዙት ሷሂሮች ሸር ይጠብቀን። አሏህም ለነኚህ ለከሀዲያን ጀሀነምን እንደሚኖሯት ቃል ገባ።
       የቀብር ሲህር እጅግ በጣም ሰቅጣጭና አደገኛ የሚባል አይነት ሲሆን በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተው በስራችን በአሏህ ቃል ከማረክናቸው የቀድሞ ሷሂሮች እና በስራው ላይ በተደረገ ጥናት አደገኝነቱ የተረጋገጠ ሲህር ነው።
እነኚህ ሷሂሮች ከ ቀብር ቦታ ላይ ከሟች ገላ ብስባሽ አፈር ቆፍረው በማውጣት የ ሟቹን ሰው ቀሪን የተሰኘውን ሸይጧን ያዛሉ ። ይህ ሸይጧንም አፈሩን ተከትሎ ሲህር ለመሰራት በሚፈለገው ሰው ላይ ያዛሉ ። ወናኡዙቢሏህ
የነኚህ ሲህር ተጠቂ ሰዎች ምልክቶች
1.እረፍት የለሽ የተረበሹ ናቸው ፡፡ መውጣት መግባት መንቀዥቀዥ በስራ ላይ ስራ መደረብ ይጀምራሉ።
2.እጅግ ሱሰኞች ናቸው ሲጃራ ጫት ሱሰኞች ናቸው ።
3. ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በተለይ ከአሱር ቡሀላ ፍርሀት ጭንቅ  ጥብብ ማለት መረበሽ
4.ከሰው መራቅ ጓደኛ አለመቅረብ ፊት የሚያውቋቸውን ሚግባቧቸውን ሰዎች ልጆቻቸውን ሳይቀር (እንዲህ ሊያደርጉኝ ነው) ብለው ይጠረጥራሉ።
5.በቀን እያረፉ በቀጣዩ ቀን ታማሚዎች ናቸው። የህመማቸው ምክንያት ግን ግልፅ አደለም።
6.ከፍተኛ እራስ ምታት አለባቸው። ይህ ራስምታት ልክ እንደማይግሪን አድርጎ የሚመጣ ቢሆንም ቅሉ በምንም መድሀኒት አይድንም።
7.አንዴ በቀኝ አንዴ በግራ ጉልበታቸውን እግራቸውን እየለዋወጠ ይይዛቸዋል።
8. ሰውነታቸው ከመጠን በላይ መሽተት ይጀምራል ይህ ሽታ ከዚህ ቀደም እንደሌለው አይነት ነው።
9. ድብርት ይኖራቸውል። ይህ ድብርት ከሌላው የሚጠነክረው ጥዋት ላይ ሲሆን በሌላው ክፍለግዜ ሊጠፋ ይችላል።
10. ብቻቸውን አልፎ አልፎ ማውራት ይጀምራሉ ። ልክ ሌላ ሰው ያለ ይመስላቸዋል።
11.ሰውነታቸው ውስጥ የሚሄድ የሚርመሰመስ ነገር አለ።
12 . ለነሱ ብቻ የሚያለቅስ ሰው ድምፅ የሚስቅ አልያም የሚያቃስት ሰው ድምፅ ይሰማቸዋል።
13.ቤት ውስጥ ሌላ ሰው ያለ የሚሯሯጥ ነገር ያለ ይመስላቸዋል።

ይህ በቀላሉ በራስ ህክምና የሚለቅ አይደለም ይሁንና እራሳቸውን ታማሚዎች ከመታመማቸው በፊት ሊጠብሹ ይገባል ለዚህም መጠበቅያ ህክምናው

1.ሲተኙ በሱና መተኛት ውደእ ያድርጉ

2.ከእንቅልፎ ሲባንኑ ዱአ አድርገው መተኛት

3.አያተል ኩርሲ መቅራት በተደጋጋሚ መቅራት
4.ቤት ውስጥ ቁርአን ድምፅ ከፍ አድርጎ መክፈት


ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ
https://t.me/Adnan567mh
569 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 09:25:10 አይነጣጠሉም

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ በጣም ሩህሩህ። የአላህ ሰላትና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ይሁን።

1) ቁርአን የአላህ ቃል ነው፣
2) አላህ ቁርአንን በታማኙ የመላእክቶች አለቃ ጂብሪል አማካኝነት ነብዩ ሙሐመድ ላይ አወረደው፣
3) ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለሰሀባዎቻቸው ይህንን መልክት አላህ በሚፈልገው መንገድ በደንም አብራሩላቸው። ይህም ሱና ነበውያ (የነብዩ ሱና) ይባላል።
4) ሙስሊሞች የመተዳደሪያቸው ምንጭ የትም አለም ላይ ይኑሩ ከነዚህ ከሁለቱ አይወጡም።
ከአላህ ቃል ቁርአን እና ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና።
5) ቁርአንን ተቀብሎ ሀዲስ ያልተቀበለ ከኢስላም ይወጣል። ምክንያቱም አላህ ቁርአን ላይ እንዲህ ስለሚል
{وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلذِّكۡرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ }
[Surah An-Nahl: 44]
ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና (ልታብራራላቸው) ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡
ሀዲስ አልቀበልም ያለውን ግለሰብ ከሀዲ ያደረገው አላህ አብራራላቸው ብሎ ያዘዛቸው ነብይ ማብራሪያ አልቀበልም በማለቱ ነው።

አላህ ቁርአን ላይ ያዘዘን ትእዛዛት አፈፃፀማቸውን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ነው ያብራሩት።

በየቀኑ የምንሰግደው 5 ወቅት ሶላት አላህ እንድንሰግድ ሲያዘን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አላህ የሚቀበላት ስግድት እያንዳንዱ ሶላት ስንት ረከአ እንዳለው፣ በውስጡ ምን እንደሚባል፣ ከሶላት በኀላ ምን እንደሚባል ያስተማሩት እኝህ መልክተኛ ናቸው።

6) ይህ ቁርአን ሲወርድ ቦታው ላይ የነበሩት ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት ቁጭ ብለው የተማሩ፣ ያልተረዱትን ነገር አላህ በሌላ የቁርአን አንቀፅ መልክቱን እየገለፀላቸው፣ ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እያብራሩላቸው፣ የአላህን ውዴታ ያገኙት ሰሃባዎች ናቸው።
7) አላህ ሰሀባዎች በመልካም ፈለጋቸው ከተከተል የእሱን (የአላህ ውዴታ) እንደምናገኝ ነግሮናል።
8) የእነሱ ፈለግ ማለት ቁርአንና ሀዲስን ሰሀባዎች በተረዱበት መንገድ መረዳት ነው። ይሄ ከጥመት ይጠብቃል። የአላህ ውዴታም ያስገኛል። ወደ ጀነት ለመዳረስ አጭሩ መንገድ ይሄ ነው።
9) ያማረ ህይወት በዱናያ መኖር ከፈለግን፣ በአኸይራ ጀነትን በአላህ ፍቃድ ለመጎናፀፍ፣ ከእሳት ለመጠበቅ
– የመጨረሻው መልክተኛ ነበዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ የወረደውን ቁርአን ማክበር፣ የህይወት ህግ አድርጎ መውሰድ፣
– የእሳቸውን ሱና ከቁርአን ህግ አለመነጠል፣
– የሶሀባዎች አረዳድ መከተል።

አላህ ለህጉ ከሚያድሩት፣ መልክተኛውን ሙሉ ለሙሉ ከሚከለቱት፣ የወደዳቸው ሰሀባዎችን አረዳድ ከሚረዱት ያድርገን።☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

913 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 17:47:14 ሰባት ነገሮችን አይተህ ሰባት ነገሮችን ፈፅም


ሁሉም ሰው በሕይወት ዘመኑ ጓደኞች ቢኖሩትም ቀብር ሲገባ እንደሚተውት አይተህ መልካም ተግባርን ጓደኛ አድርግ ። መልካም ስራህ እስከመቼውም አይለይህምና ።

《ነፍሱን ከስሜቱ የከለከለ በእርግጥ ጀነት መቀመጫው ናት》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ ስሜትህን በአሏህ መንገድ ምራት ። ስሜትህ በመጥፎ እንጅ በጥሩ አታዝህምና ።

《አሏህ ዘንድ በላጩ አሏህን ይበልጥ የሚፈራው ነው》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ አሏህ ዘንድ ቦታ እንድኖርህ ነፍስህን የአሏህን ፍራቻ አስለምዳት ።

《እኛ አኗኗራቸውን ከፋፍልነው (በሀብት ለያየነው) 》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ ያንተም አሏህ የወሰነልህ ብቻ መሆኑን አውቀህ ምቀኝነትን ራቅ ።

《 በርግጥ ሸይጧን የናንተ ግልፅ ጠላት ነው》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ ከሰዎች ጋር መናቆርህን ትተህ ጠላትህን ሸይጧንን ብቻ አድርገው ።

《መሬት ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ (ህይወት ያለው) ነገር የለም ፤ የሱ ሲሳይ (ሪዝቅ) አሏህ ጋር ቢሆን እንጅ》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ አንተ አሏህ ጋር ያለህን አሏህ ራሱ እንደሚሰጥህ አረጋግጠህ እሱ አንተ ላይ ያለውን አደራ (የዲኑን ህግጋት) ፈፅም ።

《በአሸናፊውና በመሀሪው (ጌታህ) ተመካ》 የሚለውን የአሏህ ቃል አይተህ መመኪያህን አሏህን ብቻ አድርገው ።

《ወንድሜ (እህቴ) ሆይ ከነዚያ ከዝንጉዎች አትሁኑ ። ከነዚያ አሏህን ረስተው አሏህ ነፍሳቸውን ካስረሳቸው እንድሁም ከአዱኒያና ከአኼራ በጎ ነገሮች አሏህ ካራቃቸው አትሁኑ ።》【ያህያ ቢን ሙዓዝ አለይሂ ራህመቱሏህ】

《ለወላጆች ኡፍ ከማለት የበለጥ ወንጀል ቢኖር ኖሮ አሏህ በቁርኣኑ ይከለክለው ነበር ።》【ሰይድና አሊይ ኢብን አቢጧሊብ ረድየሏሁ አንሁ ወአርዷህ 】

《ለወላጆች ዱዓን መተው (ዱዓ አለማድረግ) የልጅን ህይወት ያጣብባል ።》

《ወንድሜ ሆይ አንተ ስትሞት ዓለምን ትገላገላታለህ ወይስ እሷ አንተን ትገላገልሃለች? 》

《ጊዜን ያለምንም ኢባዳ ካሳለፍከው ፥ በዚያ ባለፈው ጊዜም ካልተቆጨህ ልብህ መድረቁን (መበላሸቱን) እወቅ ።》

ጥሩ መፅሀፍ የከፍተኛ መንፈስ ውድ የህይወት ደም ነው ። ከህይወትህ ባሻገር ህይወት በሚሰጥ መዓዛ የተሞላ ታላቅ ሀብት ነው ።》
አላህ ይዘንልን!!!!

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

884 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ