Get Mystery Box with random crypto!

Sunnah Media Zone 」【SMZ】

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuibrahim0102030405 — Sunnah Media Zone 」【SMZ】 S
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuibrahim0102030405 — Sunnah Media Zone 」【SMZ】
የሰርጥ አድራሻ: @abuibrahim0102030405
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.04K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት(ሱና) ማለት፣ የቁርኣንና ሀዲስን አስተምህሮት በቀደምቶች(በሠለፎች) ግንዛቤ ላይ በተመሰረተ መልኩ በመገንዘብ(በመረዳት) መተግበር(ማራመድ) መቻል ማለት ነው።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-03 11:56:24 ኢርሻዱል በሪያህ

إرشاد البرية إلى شرعية الإنتساب للسلفية ودحض الشبه البدعية》
《 ኢርሻዱል በሪያህ ኢላ ሸርዒየቲል ኢንቲሳቢ ሊሰለፊያ》
ክፍል ሰባት

መቅድም (المقدمة)

ولقد أحسن الإمام الأصبهان عند ما قال《 وكان السبب في إتفاق أهل الحديث أنهم أخذوا الدين من الكتاب والسنة وطريق النقل، فأورثهم الاتفاق والائتلاف،
ኢማሙ ሐሰነል በስሪይ አላህ ይዘንላቸውና 《 ሱኒዮች በትክክለኛው የዲን አስተምህሮት በሱና ላይ በአንድ ላይ ያለምንም መጣረስ የመጓዛቸው ምስጢር ዲናቸውን ከቁርአንና ከትክክለኛ(ሰሒህ) ሐዲስ በትክክለኛው ከሱና ሊቃውንት ቅብብሎሽ የያዙ መሆናቸው ሲሆን።

وأهل البدعة أخذو ا الدين من المعقولات والآراء فأورثهم الافتراق والاختلاف.》
إرشاد البرية إلى شرعية الانتساب إلى
السلفية(12_13)

የቢዳዓ አራማጆች ደግሞ በኢስላም ውስጥ በቁርአንና በትክክለኛ ሐዲስ ያልተደነገገን የስዎችንና የቡድኖችን አመለካከት በማራመዳቸው ምክንያት ይህ የተሳሳተ አካሄዳቸው መለያየትንና መከፋፈልን አውረሷቸዋል።》ብለዋል።

ኢርሸዱል በሪያህ(12_13)

ግንቦት 26/09/2014 ዓ ል

ዙልቃዕዳ 03/11/1443 ዓ ል

አቡ ኢብራሂም

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
584 views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 10:44:11 ኢርሻዱል በሪያህ

إرشاد البرية إلى شرعية الإنتساب للسلفية ودحض الشبه البدعية》
《 ኢርሻዱል በሪያህ ኢላ ሸርዒየቲል ኢንቲሳቢ ሊሰለፊያ》
ክፍል ስድስት

መቅድም (المقدمة)

قال أبو عبد السلام حسن بن قاسم الحسني الريمي السلفي في إرشاد البريته
አቡ ዓብድሰላም ሐሰን ቢን ቃሲም......

و هكذا قام بالدعوة من بعده صحابته الكرام رضوان الله عليهم
የትክክለኛው የኢስላም አስተምህሮት ሱና(ሰለፊያ) ከነብዩ ﷺ በወኋላ በተከበሩት በነብዩ ﷺ ሷሐቦች ሲተገበርና ሲሰበክ(ዳዕዋ) ሲደር የቆየ ሲሆን

ثم في عصرنا هذا من أمثال الشيخ ابن باز رحمه الله والشيخ ابن عثيمين، والشيخ الفوزان، والشيخ ربيع المدخلي، والشيخ، محمد أمان الجامي رحمه الله، والشيخ الألباني رحمه الله، والشيخ مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله، والشيخ حمدي بن عبد المجيد السلفي، وغيرهم ممن ترسم خطاهم… كلهم يدعون إلى منهج واحد وعقيدة واحدة.
አሁን ላይ ደግሞ እንደ ሸይክ ኢብኑ ባዝ፣ኢብኑ ዑሰይሚን፣ሸይክ ፈውዛን ፣ሸይክ ረቢዕ አልመድኸሊይ፣ ሸይክ አልባኒ፣ሸይክ ሙቅቢል፣ ሸይኽ ሀምዲ ኢብኑ ዐብድል መጂድ እና ሌሎችም ወደ ተውሒድ መንገን በሚጣሩ ሱኒይ ኢማሞች የሚመራ ሚንሀጅ ነው።

ኢርሸዱል በሪያህ(12)

ግንቦት 23/09/2014 ዓ ል

ሸዋል 30/10/1443 ዓ ል

አቡ ኢብራሂም

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
653 views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 11:21:45 ሱና
السنة
قال عمر بن.عبد العزيز رحمه الله《 لا تكن ممن يتبع الحق إذا وافق هواه ويخالفه إذا خالف هواه》فتاوى بن تينية(480/10)

《ዑመር ኢብኑ ዐብድል ዐዚዝ አላህ ይዘንላቸውና
ሐቅን ሲመስለው(ከዝንባሌውና ከስሜቱ ጋር ሲገጥምለት) የሚቀበልና ሳይመስለው(ከዝንባሌውና ከስሜቱ ጋር ሳይገጥምለት ) ሲቀር ማይቀበል ሰው እንዳትሆን።》ብለዋል።

ኢብኑ ተይሚያህ(10/480)

ግንቦት 19/09/2014 ዓ ል

አቡ ኢብራሂም

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
752 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 14:06:32 ሱና
السنة

قال العلامة الشيخ ربيع هادي المدخلي حفظه الله
《فلا تتحقق السلفية والسنية حتى تفارق أهل البدع والتحزب قلبا وقالبا》
مجموع الردود(276)

ሸይኽ ረቢዕል መድኸሊይ አላህ ይጠብቃቸውና 《 ከቢዳዓ አራማጆች እና ከሒዝቢዮች(ቡድንተኞች) ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አንዳች ግንኙነት እስካለ ግዜ ድረስና ሱኒዮች(ሰለፊዮች) ነን የሚሉ ወገኖች ከቢዳዓ አራማጆች እና ከሒዝቢዮች(ከቡድንቶች) ጋር በሪኦተ አለማዊም(በአስተሳሰባዊም) ይሁን በተግባራዊ ነገሮች ላይ ሙሉ በሙሉ ያላቸውን ግንኙነት እስካላቋረጡ ድረስ ሱኒይነትና ሰለፊይነት በፍፁም ሊኖር አይችልም ከንቱ ምኞትም ብቻ ነው።

መጅሙዕ አሩዱዱ(276)

ግንቦት 13/09/2014 ዓ ል

ሸዋል 21/10/1443 ዓ ሂ

አቡ ኢብራሂም

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
959 views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 11:31:11 ኢርሻዱል በሪያህ

إرشاد البرية إلى شرعية الإنتساب للسلفية ودحض الشبه البدعية》
《 ኢርሻዱል በሪያህ ኢላ ሸርዒየቲል ኢንቲሳቢ ሊሰለፊያ》
ክፍል አምስት

መቅድም (المقدمة)

قال أبو عبد السلام حسن بن قاسم الحسني الريمي السلفي في إرشاد البريته
አቡ ዓብድሰላም ሐሰን ቢን ቃሲም......

و هكذا قام بالدعوة من بعده صحابته الكرام رضوان الله عليهم
የትክክለኛው የኢስላም አስተምህሮት ሱና(ሰለፊያ) ከነብዩ ﷺ በወኋላ በተከበሩት በነብዩ ﷺ ሷሐቦች ሲተገበርና ሲሰበክ(ዳዕዋ) ሲደር የቆየ ሲሆን

ثم تلاهم التابعون وأتباعهم من أمثالهم: الحسن البصري وسعيد بن المسيب وعروة بن الزبير، وعبد الله بن المبارك، ومالك بن أنس والليث بن سعد،
ታዓቢዮች ደግሞ የሷሐቦችን እግር ተክትለው ሱናን(ሰለፊያን) ተግብራው ሰብከዋል።

والشافعي، وأبي إسحاق الفزاري، ووكيع بن الجراح، وإسماعيل بن علية، والسفيانين، والأوزاعي، وأحمد بن حنبل، والبخاري، ومسلم، والترمذي وأبي داود، والنسائي، وبن ماجه، وبن تيمية، وبن القيم، وبن كثير، ومحمد بن عبد الوهاب، وأبنائه وأحفاده، والشوكاني

ታዓቢዮችን ተከትለው በየዘመኑ የነበሩ ታላላቅ ሙስሊም ሊቃውንትና የዲን መሪዎች እንደነ ኢማሙ ሻፊዒይ፣ አቡ ኢስሐቅ አልፈዛሪዩ፣ ወኪዕ ኢብኑል ጀራሕ፣ ኢስማዒል ኢብኑ ዑለያህ፣ ሁለቱ ሱፊያኖች፣ ኢማሙል አውዛዒይ፣ አህመድ ኢብኑ ሀንበል፣ ኢማሙል ቡኻሪይ፣ ሙስሊም፣ ቲርሚዚይ፣ አቡ ዳውድ፣ ነሰኢ፣ ኢብኑ ማጅህ፣ ኡብኑ ተይሚያህ፣ ኢብኑልቀይም፣ ሸይኽ ሙሀመድ ዐብዱልወሀብ፣ የእሳቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ኢማሙ ኢማሙ ሸውካኒ በየዘመናቸው ሱናን ሲተገብሩ ፣ሲያስተገብሩና ሲያሰራጩ ኖረው ለተተኪያቸው ኦርጂናሊቲውን እንደጠበቀ አስተላልፈዋ።

ኢርሸዱል በሪያህ(12)

ግንቦት 10/09/2014 ዓ ል

ሸዋል 17/10/1443 ዓ ል

አቡ ኢብራሂም

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
903 viewsedited  08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 07:19:53
1.2K views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 15:40:20 ሸዋል ፍች(ትንሿ ፍች) የሚባል በዓል በኢስላም አለን????

ሸዋል ፍች(ትንሿ ፍች) በኢስላም
(በቁርአንና በሐዲስ) እይታ

فإن الله شرع للمسلمين عيدين عيد الفطر وعيد الأضحى.

《አላህ በኢስላም ውስጥ ሁለት አመታዊ በዓልንና አንድ ሳምንታዊ በዓልን ብቻ ነው የደነገገው። ለዚህም ማስረጃው…

ودليل ذلك ما رواه أبو داود في سننه عن أنس رضي الله عنه قال قدم رسول الله صلى الله عليه وسلم المدينة ولهم يومان يلعبون فيهما فقال: "ما هذان اليومان؟ قالوا: كنا نلعب فيهما في الجاهلية فقال يا رسول إن الله قد أبدلكم بهما خيراً منهما يوم الأضحى ويوم الفطر "
رواه أبوا داود.

《ነብዩ ﷺ ወደ መዲና በተሰደዱበት ወቅት የመዲና ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው በመጨፈር የሚያከብሯቸው ሁለት አመታዊ በዓላት(ዒዶች) ነበሯቸው።
ነብዩﷺ እነዚህ ሁለት የምታከብሯቸው ቀናት ምንድናቸው ብለው ሲጠይቋቸው የመዲና ነዋሪዎችም ከድንቁርና(ከጃሂሊያ) ዘመን ጀምሮ እናከብራቸው ነበር አሏቸው ነብዩም ﷺ አላህ እነዚህን ሁለት አመት_በዓሎችን በተሻለ ሌላ ሁለት አመት_በዓላት(ኢዶች) ቀይሮላቹሀል እነሱም ዒደል ፊጥርና ዒደል አድሐ ናቸው። ብለዋቸዋል።》
አቡዳውድ ዘግበውታል።

ከዚህ የምንረዳው በኢስላም ውስጥ የተደነገጉ አመታዊ በዓላት ሁለት ብቻ እንደሆኑና እነሱም ዒደልፊጥርና ዒደል አድሐ ብቻ እንደሆኑ ነው።

ሳምንታዊው ዓመት_በዓል ደግሞ አንድ ብቻ ሲሆን እሱም የጁምዓ እለት ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ግን በቁርአንም ሆነ በትክክለኛ(በሰሒህ) ሐዲስ ያልተደነገጉ ኢ_ኢስላማዊ በዓላት ሲከበሩ ይስተዋላል።

ከእነዚህ በኢስላም ካልተደነገጉ በዓላት መካከል መውሊድ፣ሸዋል ፍችና ዐሹራ ናቸው።

እነዚህ ሶስቱ በዓላት መውሊድ፣ሸዋል ፍችና ዐሹራ በቁርአንና በትክክለኛ ሐዲስ(በሰሒህ) ያልተነገጉ ነገር ግን ሰዎች ስሜታቸውን በመከተል የፈበረኳቸው የአላህ ሳይሆኑ የሰዎች በዐላት ናቸው።

ይህ ማለት መውሊድ፣ዐሹራ እና ሸዋል ፍች ኢስላማዊ በዐላት ሳይሆኑ ኢ_ኢስላማዊ በዐላትና ኢስላም ውስጥ ከሚተገበሩ ከቢዳዓ ተግባራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

እስኪ ነብዩ ﷺ ኹጥባ ሲያነቡ ሁሌም ሳያነቡ ማያልፏትን ዐረፍተ ነገርን እናስታውስ…

وشر الامور محدثاتها وكل محدثة بدعة وكل بدعة ضلالة وكل ضلالة في النار》

《በዲን ውስጥ የነገራቶች ሁሉ መጥፎ(ሸር) ተግባር ማለት ከመሰረቱ በዲን ያልነበረና ወደ በወኋላ አዲስ የሚፈጠር መጤ ነገር ነው፣ አዲስ ነገር ሁሉ ደግሞ መጤ(ሰርጎ ገብ) ነው፣ በዲን ውስጥ ከጅምሩ ያልነበረ አዲስ መጤ ተግባር ደግሞ ጥመት ነው፣ እያንዳንዱ የጥመት ተግባር ደግሞ የእሳት ድርሻ ነው(ለእሳት የሚያበቃ ነው》ብለዋል።

መውሊድ፣ዓሹራና ሸዋል ፍች በቁርአንና በትክክለኛ ሐዲስ እስካልተደነገገ ድረስ ማንም አለ ብሎ ይናገር ማን ንግግሩ ውድቅ(ረድ) ሊደረግ ግድ ነው።

عن أم المؤمنين عائشة رضي الله عنها قالت : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد ) رواه البخاري ومسلم ،

《ዓኢሻህ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ባስተላለፈችው ሐዲስ ነብዩ ﷺ《በዚህ ዲናችን ውስጥ ከጅምሩ ያልነበረን ነገር ያስገኘ ሰው ያ ያስገኘው ነገር ሊስተባበል(ረድ) ሊደረግ የሚገባ ነው።》ብለዋል።

ኢማሙ ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

وفي رواية لمسلم : ( من عمل عملاً ليس عليه أمرنا فهو رد ) .

《በሌላ የነብዩ ﷺ ንግግር《አንድ ሰው የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ነገር በዲን ውስጥ ከተገበረ ይህ ተግባሩ ሊስተባበል(ውድቅ) ሊደረግ የሚገባ ተግባር ነው።》 ብለዋል።

ሙስሊም ዘግበውታል።

ነገ በአብዛሀኛው ባህልን ዲን አድርገው በሚገነዘቡና ዲንን በባህላዊ መንገድ በዘልማድ በሚያራምዱ የህብረተሰባችን ክፍል ዘንድ የሚከበረው የሸዋል ፍች በዲን ስም ከሚከበሩ ሰው ሰራሽ አመት_ በዓሎች(ዒዶች) መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ይህንን የቢዳዓ በዓልን የሚያከብሩ ሰዎች ከዲን የሚፃረር ባህላዊ እምነት እያከበሩ መሆናቸውን በሚገባ ሊያውቁ ይገባል።

ማንኛውም ከዲን ተፃራሪ አስተምህሮትና ተግባር ደግሞ በኢስላም ውስጥ አፍራሽ አመለካከት ነው።

በመሆኑም በቁርአንና በትክክለኛ የነብዩ ﷺ ሐዲስ የተደነገገውን ብቻ በመከተልና በመተግበር እንዲሁም በቁርአንና በትክክለኛ(በሰሒህ) በነብዩ ﷺ ሐዲስ ያልተደነገገን ነገር በሙሉ በመፀየፍና በመራቅ የትክክለኛው የኢስላም አስተምህሮት የሱና(የሰለፊያህ) ተከታይና አራማጅ መሆን የእያንዳንዱ ሙስሊም የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነወ።

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 27/08/2014ዓ ል

ሸዋል 05/10/1443 ዓ ሂ

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
2.4K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 15:32:03 የሸዋል ፆምን የተመለከቱ ህግጋቶች

ክፍል ሁለት

ማስገንዘቢያ!!!!!!!!!!!!!!!!!!

أن الرسول ﷺ قال من صام رمضان ثم أتبعه ستاً من شوال  كان كصيام الدهر
ነብዩ ﷺ ስለሸዋል ፆም ሲነገሩ የረመዳንን ወር ሙሉ ፆሞ ከሸዋል ወር ደግሞ ስድስት ቀን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደ ፆመ ነው ሚቆጠርለት ብለዋል።

ሙስሊም ሙሁራን ይህንን ሀዲስ በመንተራስ
1ኛ:《ሱመ》የምትለው የዐረብኛ አያያዥ ቃል ተራኺ(ቅድመ ተከተልን) አመልካች ስለሆነች ረመዷንን ሙሉ ፆሞ ስድስት ቀን ከሸዋል ወር ፆም ካስከትለ ከላይ የተጠቀሰውን የአንድ አመት ሙሉ ፆም ጀዛእ የሚያገኝ ሲሆን የረመዷንን ወር ፆም ሳያሟላና ማለትም ያጓደለውን ሳያሟላ ስድስት ቀን የሸዋል ፆምን ቢያስከትልም ግን ከላይ የተጠቀሰውን ጀዛእ አያገኝም ያሉ አሉ ምክንያቱም የረመዳንን ወር ሙሉ ፆሞ ከዛው ስድስት ቀን ከሸዋል የሚለውን ቅድመተከተል አላሟላምና።

በመሆኑም በተለያየ ምክንያት ረመዷን ያጓደልን አለያም ሙሉ በሙሉ ያልፆምን ሰዎች የረመዷን ቀዷ በመክፈል ላይ ቅድሚያ እንስጥ።
2ኛ:《ሚን》ከፊልነትን ስለምታመላክት ማለትም ከሸዋል ወር ውስጥ ስድስት ቀን ያስከተለ የሚልን መልእክት ስለምታስተላልፍ ከዒደልፊጥር በበነጋው ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀን ወይም ከሙሉው ሸዋል ወር በተበታተነ መልኩም ቢሆን መፃም ይችላል ብለዋል። ﷺ

ይህ ብያኔያቸው(ሁክማቸው) ትክክል ሆኖ ሳለ ወደ ሀገራችን ተጨባጭ ስንመለስ የተወሰነው የህዝባችን ክፍል የዒዱ እለት ማግስትንና ቀጣዩንም ቀን ጨምሮ ዒድ ገና አላለቀም በሚል የሸዋል ፆምን ለተከታታይ አንድ፣ሀለትና ሶስት ቀናት ሳይፆሙ ይቀሩና ከዛው ዘግይተው ይጀምሩና አብዛኛ ከዒድ ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲፆሙ የነበሩት የህብረተሰባችን ክፍል የሸዋልን ፆም ጨርሰው እንደወትሮው መብላትና መጠጣት ሲጀምሩ ዘግይተው መፆም የጀመሩት ወገኖቻችን ግን ከፆሙዋት ሶስትና አራት ቀን በቀር ያልፆሙትን ሁለትና ሶስት ቀን በቀር ያልፆሙትን ሁለትና ሶስት ቀናት ሳይተኩ የሸዋል ወር ይጠናቀቃል።

ስለዚህ ወንድምና እህቶች ጎብዘን ለተከታታይ ስድስት ቀን በመፆም አለያም በተበታተነ መልኩ ከሆነ ደግሞ የሸዋል ወር ሳያልቅ ስድስት ቀን ቆጥርን በመፆም የተጠቀሰውን ጀዛእ ተሽቀዳድመን እንፈስ።

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 26/08/2014 ዓ ው
ሸዋል 03/10/1443 ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah
836 views12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 06:53:42 የሸዋል ፆም ህግጋት

ክፍል አንድ

ቀዷ መክፈል ወይስ ሸዋል መፆም ይቀድማል?????

የረመዳን ክፍያም(ቀዷም) ሆነ ሌላ የግዴታ ክፍያ (ቀዷ) ፆም እያለብን ሸዋልንም ሆነ ሌላ ማንኛውንም የሱና (ተጨማሪ) ፆም መፆም ነው ያለብን ወይስ ያለብንን የክፍያ ፆም(የቀዷ ፆም)
መክፈል ነው ያለብን????።

ﻗﻀﺎﺀ ﺭﻣﻀﺎﻥ مقدم من التطوع بصيام بشوال
وجاء رجل الى رسول الله
ﻓﻘﺎﻝ :
《ﻳﺎ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺇﻥ ﺃﻣﻲ ﻣﺎﺗﺖ ﻭﻋﻠﻴﻬﺎ ﺻﻮﻡ ﺷﻬﺮ ﺃﻓﺄﻗﻀﻴﻪ ﻋﻨﻬﺎ؟》
ﻗﺎﻝ : ‏( ﻧﻌﻢ ﺩﻳﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺣﻖ ﺃﻥ ﻳﻘﻀﻰ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ﻭﻣﺴﻠﻢ،.
አንድ ሰው ወደ ነብዩ ﷺ
ዘንድ መጣና እናቴ የአንድ ወር ሙሉ ያልፆመችው የግዴታ(የረመዳን) ፆም እያለባት ሞተች እኔ ልክፈልላት? ብሎ ሲጠይቃቸው
ነብዩም ﷺ
አዎ ክፈልላት ያለተከፈለ የአላህ እዳ ከምንም ነገር በፊትና ቅድሚያ መከፈሉ ተገቢና አማራጭ ማይኖረው ግዴታ ነው ብለው።》 መልሰውለታል።
ይህን ሀዲስ
ኢማሙ ቡኻሪይና ሙስሊም መዝግበውታል።
وقال النبي قال الله تعالى في حديث القدسي
《وما تقرب إلي عبدي بشيء احب إلي مما افترضته عليه 》
رواه البخا ي
ነብዩﷺ
ሀዲሰልቁይ ላይ እንደገለፁት አላህ እንዲህ አለ ብለዋል
《ባሪያዬ ግዴታ ያደረኩበትን አምልኮ(ዒባዳህ) ከመተግበር የላቀ ወደኔ የሚቃረብበት ትልቅና ወደኔም ተወዳጅ የሆነ የዲን ተግባር የለም።》
ይህን ሀዲስ
ኢማሙ ቡኻሪይ መዝግበውታል።
قال ابن رجب رحمه الله :
《فمن كان عليه قضاء من شهر رمضان فليبدأ بقضائه في شوال فإنه أسرع لبراءة الذمة .》
لطائف المعارف : (٢٢٣
ኡብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸውና
「አንድ ሰው የረመዳን የክፍያ ፆም(ቀዷ) ካለበት የሸዋልን ፆም ፆሞ ከዛው ያለበትን የረመዳን የቀዷ ክፍያ ይክፈል ወይስ መጀመሪያ በቀጥታ የረመዳንን የቀዷ ክፍያ ይክፈል???」ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱ:
《መጀመሪያ ረመዳን ላይ ያጠፋውን ቁጥር ያህል ቀናት በሸዋል ቀናቶች አስቀድሞ ይክፈልና ቀዳውን ከፍሎ ሲጨርስ የሸዋል ወር ካላለቀ ሸዋልን ስድስት ቀን መፆም ይችላል ብለዋል።》
ለጣኢፉል አልመዓሪፍ(223)

በመሆኑም በተለያየ አጋጣሚ ያልፆምነው የረመዳን እዳ ያለብን ወንዶችም ሆን ሴቶች ከሸዋልም ሆነ ከሌሎች የተጨማሪ(ሱና) ፆሞች አስቀድመን ያልፆምነውን የረመዳን እዳ በመክፈል ላይ መጎበዝና መበርታት አለብን።

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 25/08/2014 ዓ ል
ሸዋል 01/10/1443 ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah
1.0K views03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 06:11:44
685 views03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ