Get Mystery Box with random crypto!

የሸዋል ፆምን የተመለከቱ ህግጋቶች ክፍል ሁለት ማስገንዘቢያ!!!!!! | Sunnah Media Zone 」【SMZ】

የሸዋል ፆምን የተመለከቱ ህግጋቶች

ክፍል ሁለት

ማስገንዘቢያ!!!!!!!!!!!!!!!!!!

أن الرسول ﷺ قال من صام رمضان ثم أتبعه ستاً من شوال  كان كصيام الدهر
ነብዩ ﷺ ስለሸዋል ፆም ሲነገሩ የረመዳንን ወር ሙሉ ፆሞ ከሸዋል ወር ደግሞ ስድስት ቀን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደ ፆመ ነው ሚቆጠርለት ብለዋል።

ሙስሊም ሙሁራን ይህንን ሀዲስ በመንተራስ
1ኛ:《ሱመ》የምትለው የዐረብኛ አያያዥ ቃል ተራኺ(ቅድመ ተከተልን) አመልካች ስለሆነች ረመዷንን ሙሉ ፆሞ ስድስት ቀን ከሸዋል ወር ፆም ካስከትለ ከላይ የተጠቀሰውን የአንድ አመት ሙሉ ፆም ጀዛእ የሚያገኝ ሲሆን የረመዷንን ወር ፆም ሳያሟላና ማለትም ያጓደለውን ሳያሟላ ስድስት ቀን የሸዋል ፆምን ቢያስከትልም ግን ከላይ የተጠቀሰውን ጀዛእ አያገኝም ያሉ አሉ ምክንያቱም የረመዳንን ወር ሙሉ ፆሞ ከዛው ስድስት ቀን ከሸዋል የሚለውን ቅድመተከተል አላሟላምና።

በመሆኑም በተለያየ ምክንያት ረመዷን ያጓደልን አለያም ሙሉ በሙሉ ያልፆምን ሰዎች የረመዷን ቀዷ በመክፈል ላይ ቅድሚያ እንስጥ።
2ኛ:《ሚን》ከፊልነትን ስለምታመላክት ማለትም ከሸዋል ወር ውስጥ ስድስት ቀን ያስከተለ የሚልን መልእክት ስለምታስተላልፍ ከዒደልፊጥር በበነጋው ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀን ወይም ከሙሉው ሸዋል ወር በተበታተነ መልኩም ቢሆን መፃም ይችላል ብለዋል። ﷺ

ይህ ብያኔያቸው(ሁክማቸው) ትክክል ሆኖ ሳለ ወደ ሀገራችን ተጨባጭ ስንመለስ የተወሰነው የህዝባችን ክፍል የዒዱ እለት ማግስትንና ቀጣዩንም ቀን ጨምሮ ዒድ ገና አላለቀም በሚል የሸዋል ፆምን ለተከታታይ አንድ፣ሀለትና ሶስት ቀናት ሳይፆሙ ይቀሩና ከዛው ዘግይተው ይጀምሩና አብዛኛ ከዒድ ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲፆሙ የነበሩት የህብረተሰባችን ክፍል የሸዋልን ፆም ጨርሰው እንደወትሮው መብላትና መጠጣት ሲጀምሩ ዘግይተው መፆም የጀመሩት ወገኖቻችን ግን ከፆሙዋት ሶስትና አራት ቀን በቀር ያልፆሙትን ሁለትና ሶስት ቀን በቀር ያልፆሙትን ሁለትና ሶስት ቀናት ሳይተኩ የሸዋል ወር ይጠናቀቃል።

ስለዚህ ወንድምና እህቶች ጎብዘን ለተከታታይ ስድስት ቀን በመፆም አለያም በተበታተነ መልኩ ከሆነ ደግሞ የሸዋል ወር ሳያልቅ ስድስት ቀን ቆጥርን በመፆም የተጠቀሰውን ጀዛእ ተሽቀዳድመን እንፈስ።

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 26/08/2014 ዓ ው
ሸዋል 03/10/1443 ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah