Get Mystery Box with random crypto!

የሸዋል ፆም ህግጋት ክፍል አንድ ቀዷ መክፈል ወይስ ሸዋል | Sunnah Media Zone 」【SMZ】

የሸዋል ፆም ህግጋት

ክፍል አንድ

ቀዷ መክፈል ወይስ ሸዋል መፆም ይቀድማል?????

የረመዳን ክፍያም(ቀዷም) ሆነ ሌላ የግዴታ ክፍያ (ቀዷ) ፆም እያለብን ሸዋልንም ሆነ ሌላ ማንኛውንም የሱና (ተጨማሪ) ፆም መፆም ነው ያለብን ወይስ ያለብንን የክፍያ ፆም(የቀዷ ፆም)
መክፈል ነው ያለብን????።

ﻗﻀﺎﺀ ﺭﻣﻀﺎﻥ مقدم من التطوع بصيام بشوال
وجاء رجل الى رسول الله
ﻓﻘﺎﻝ :
《ﻳﺎ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺇﻥ ﺃﻣﻲ ﻣﺎﺗﺖ ﻭﻋﻠﻴﻬﺎ ﺻﻮﻡ ﺷﻬﺮ ﺃﻓﺄﻗﻀﻴﻪ ﻋﻨﻬﺎ؟》
ﻗﺎﻝ : ‏( ﻧﻌﻢ ﺩﻳﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺣﻖ ﺃﻥ ﻳﻘﻀﻰ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ﻭﻣﺴﻠﻢ،.
አንድ ሰው ወደ ነብዩ ﷺ
ዘንድ መጣና እናቴ የአንድ ወር ሙሉ ያልፆመችው የግዴታ(የረመዳን) ፆም እያለባት ሞተች እኔ ልክፈልላት? ብሎ ሲጠይቃቸው
ነብዩም ﷺ
አዎ ክፈልላት ያለተከፈለ የአላህ እዳ ከምንም ነገር በፊትና ቅድሚያ መከፈሉ ተገቢና አማራጭ ማይኖረው ግዴታ ነው ብለው።》 መልሰውለታል።
ይህን ሀዲስ
ኢማሙ ቡኻሪይና ሙስሊም መዝግበውታል።
وقال النبي قال الله تعالى في حديث القدسي
《وما تقرب إلي عبدي بشيء احب إلي مما افترضته عليه 》
رواه البخا ي
ነብዩﷺ
ሀዲሰልቁይ ላይ እንደገለፁት አላህ እንዲህ አለ ብለዋል
《ባሪያዬ ግዴታ ያደረኩበትን አምልኮ(ዒባዳህ) ከመተግበር የላቀ ወደኔ የሚቃረብበት ትልቅና ወደኔም ተወዳጅ የሆነ የዲን ተግባር የለም።》
ይህን ሀዲስ
ኢማሙ ቡኻሪይ መዝግበውታል።
قال ابن رجب رحمه الله :
《فمن كان عليه قضاء من شهر رمضان فليبدأ بقضائه في شوال فإنه أسرع لبراءة الذمة .》
لطائف المعارف : (٢٢٣
ኡብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸውና
「አንድ ሰው የረመዳን የክፍያ ፆም(ቀዷ) ካለበት የሸዋልን ፆም ፆሞ ከዛው ያለበትን የረመዳን የቀዷ ክፍያ ይክፈል ወይስ መጀመሪያ በቀጥታ የረመዳንን የቀዷ ክፍያ ይክፈል???」ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱ:
《መጀመሪያ ረመዳን ላይ ያጠፋውን ቁጥር ያህል ቀናት በሸዋል ቀናቶች አስቀድሞ ይክፈልና ቀዳውን ከፍሎ ሲጨርስ የሸዋል ወር ካላለቀ ሸዋልን ስድስት ቀን መፆም ይችላል ብለዋል።》
ለጣኢፉል አልመዓሪፍ(223)

በመሆኑም በተለያየ አጋጣሚ ያልፆምነው የረመዳን እዳ ያለብን ወንዶችም ሆን ሴቶች ከሸዋልም ሆነ ከሌሎች የተጨማሪ(ሱና) ፆሞች አስቀድመን ያልፆምነውን የረመዳን እዳ በመክፈል ላይ መጎበዝና መበርታት አለብን።

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 25/08/2014 ዓ ል
ሸዋል 01/10/1443 ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah