Get Mystery Box with random crypto!

Sunnah Media Zone 」【SMZ】

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuibrahim0102030405 — Sunnah Media Zone 」【SMZ】 S
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuibrahim0102030405 — Sunnah Media Zone 」【SMZ】
የሰርጥ አድራሻ: @abuibrahim0102030405
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.04K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት(ሱና) ማለት፣ የቁርኣንና ሀዲስን አስተምህሮት በቀደምቶች(በሠለፎች) ግንዛቤ ላይ በተመሰረተ መልኩ በመገንዘብ(በመረዳት) መተግበር(ማራመድ) መቻል ማለት ነው።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-26 09:52:56 ዘካተል_ፊጥር

زكاة الفطر

ክፍል _አንድ

የዘካተል_ፊጥር ግዴታነት(ዋጅብነት)

زكاة الفطر فرض بالسنة والإجماع

《ዘካተል ፊጥር: በቀደምት ሙስሊም ሙሁራን ግዴታ መሆኑ በሙሉ ድምፅ ስምምነት ላይ ተደርሶበታል(ኢጅማዕ ተደርጎበታል።》

قال العراقي رحمه الله فيه وجب ركاة الفطر وهو مجمع عليه إليه إلا ممن شذ

አልዒራቂይ አላህ ይዘንላቸውና 《ዘካተል ፊጥር ግዴታ(ዋጅብ) በመሆኑ ላይቀደምት ሙስሊም ሊቃውንቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተውበታል(ኢጅማዕ ተደርጎበታል።)

قال إبن المنذر أجمع عوام أهل العلم. على ذلك

ኢብኑል ሙንዚር አላህ ይዘንላቸውና ዘካተል ፊጥር ግዴታ(ዋጅብ) ለመሆኑ አጠቃላይ ሙስሊም ሊቃውንቶች ተስማምተውበታል(ኢጅማዕ አድርገውበታል)

قال إسحاق إبن راهويه هو كالإجماع من أهل العلم.

ኢስሐቅ ኢብኑ ራወይህ አላህ ይዘንላቸውና
《የዘካተል ፊጥር ግዴታነት አንደ አጠቃላይ የሙስሊም ሊቃውንቶች ስምምነት(እንደ ኢጀማዕ) የሚቆጠር ያህል ነው።》ብለዋል።

قال الخطابي رحمه الله قال به عامة أهل العلم

《ኸጣቢይ አላህ ይዘንላቸውናየዘካተል ፊጥር ግዴታነት(ዋጅብነት) የአጠቃላይ የሙስሊም ሊቃውንት ስምምነት(ኢጅማዕ) ነው።》ብለዋል።

የሸኽ ዐብድል ዐዚዝ አረይስ የቴሌግራም ቻናል

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 18/08/2014 ዓ ል
ረመዷን 25/09/1443 ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah
1.1K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 12:09:51 በእድሜያቸው መግፋት የተነሳ መፆም የተሳናቸው አዛውንቶችና ሊድን በማይችል ህመም ታመው መፆም የተሳናቸው ህሙማን ማድረግ ስለሚገባቸው ምትክ የዒባዳ ተግባርን የተመለከተ ዲናዊ ድንጋጌ

باب في ما يلزم من أفطر لكبر أو مرض 
قال المؤلف صالح ابن فوزان الفوزان حفظه الله :
ሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና…
《إن الله سبحانه وتعالى أوجب صوم رمضان على المسلمين ، أداء في حق غير ذوي الأعذار ،》
《ከማይገባው ጀረጃ ሁሉ የላቀው አላህ የረመዳን ወር ፆምን መፆም ላለመፆም በቂ ምክንያት በሌላቸው ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ያደረገ ሲሆን።》
《وقضاء في حق ذوي الأعذار ، الذين يستطيعون القضاء في أيام أخر 》
《ላለመፆም በቂ ኢስላማዊ ምክንያት ላላቸውና ለሚችሉ ደግም በሚችሉበት ወቅትና ሁኔታ ላይ ሲሆኑ በመፆም እንዲከፍሉ ግዴታ አድርጓል።》
《وهناك صنف ثالث لا يستطيعون الصيام أداء ولا قضاء》
《ሌሎች በወቅቱም ሆነ በሌላ ግዜ መፆም ለማይችሉ
《كالكبير الهرم والمريض الذي لا يرجى برؤه ، فهذا الصنف قد خفف الله عنه 》
《ማለትም በጣም ላረጁ አዛውንቶችና መዳን በማይችል ህመም ላይ ላሉ ህሙማን ድግሞ…》
《فأوجب عليه بدل الصيام إطعام مسكين عن كل يوم نصف صاع من الطعام . 》
《ለእያንዳንዱ ላልፆሙበት ቀን ምትክ አንድን ሚስኪን በአማካኝ ለአንድ ሰው የሚበቃ ምግብ በማብላት ያለፆሙትን ቀን ቆጥሮ መክፈልን ግዴታ አድርጓል።》
قال الله تعالى :
" 《 لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا "》
[البقرة:286]
《አላህ ባሮቹን ከአቅማቸው በላይ በሆነ ነገር አያሰስገድድም።》
وقال تعالى :
"  《وَعَلَى الَّذِينَ يُطِيقُونَهُ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ "》
[البقرة:184]
《እነዚያ መፆም የማይችሉና ለፆሙ ፋንታ ሚስኪን ማብላት የሚችሉ ወገኖች በልተው ለበሉት ቀን ምትክ ማብላት ይችላሉ።》
ሱረቱል በቀራ(184)

قال ابن عباس رضي الله عنهما : 
" هي للكبير الذي لا يستطيع الصوم "
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና
《 ይህ የቁርአን ህግ በእድሜያቸው መግፋት የተነሳ መፆም ላቃታቸው አዛውንቶች ነው።》ብለዋል
[رواه البخاري] .
ኢማሙ ቡኻሪይ መዝግበውታል።

والمريض الذي لا يرجى برؤه من مرضه في حكم الكبير ، فيطعم عن كل يوم مسكينا .
《የማይድን ህመም የያዘው ሰው ልክ በእርጅና የተነሳ መፆም እንደተሳነው ሰው ነው። ሁለቱም እየበሉ ለበሉበት እለት ምትክ ለአንድ ቀን አንድ ሚስኪን ማብላት አለያም አንድ እፍኝ(5:50—600 ግራም)ለቀለብነት ሊውል የሚችል እህል ለሚስኪኖች መለገስ አለባቸው።》
المصدر :
[الملخص الفقهي لفضيلة الشيخ العلامة صالح بن فوزان آل فوزان حفظه الله ،(الجزء الأول) قسم العبادات كتاب الصيام ((ص 314)].
ምንጭ
የሼኽ ፈውዛን አልሙለኸሱል ፊቂህይ
አንደኛ ክፍል የፆም መፅሀፍ ገፅ(314)

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 13/08/2014ዓ ው
ረመዷን 20/09/1443ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah
1.0K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 10:37:36 ኢዕቲካፍ(إلإعتكاف)

እውን ከሶስቱ(ከ3ቱ) መስጂዶች(ከመስጂደል ሐረም መካ፣ ከመስጂደ ነበዊ መዲና እና ከአቅሷ ቁድስ ፍልስጤን) ውጪ ኢዕቲካፍ ተደንግጓልን????

《وَلا تُباشِروهُنَّ وَأَنتُم عاكِفونَ فِي المَساجِدِ تِلكَ حُدودُ اللَّهِ فَلا تَقرَبوها كَذلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ آياتِهِ لِلنّاسِ لَعَلَّهُم يَتَّقونَ》
سورة البقرة(187)
《መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ተቀምጣችሁ ባለቹበት ለሚስቶቻቹህ ተቃራኒ ፆታዊ እንክብካቤ አታድርጉላቸው ይህ የአላህ የክልክልነት ወሰን ነውና እንዳትዳፈሩት(እንዳትሻገሩ)።
አላህ አንቀፆችን በዚህ መልኩ የሚያብራራላቹህ እንዲትጠነቀቁት(እንድትፈሩት) ነው።》
ሱረቱል በቀራ(187)
عن حذيفة رضي الله عنه
ሁዘይፋህ ኢብኑል የማኒ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና
قال رسول الله ﷺ:
ነብዩ ﷺ ………
《"لا اعتكاف إلا في المساجد الثلاثة . المسجد الحرام, والمسجد النبوي, والمسجد الأقصى, 》
ከሶስቱ መስጂዶች ማለትም መካ ከሚገኘው ከመስጂደል ሀረም፣መዲና ከሚገኘው ከመስጂደነበዊይ እና ፍልስጤን ከሚገኘው ከመስጂድል አቅሷ ውጪ ኢዕቲካፍ የለም።》ብለዋል።
أخرجه الطحاوي والإسماعيلي والبيهقي بإسناد صحيح عن حذيفة ابن اليمان رضي الله عنه، وهو
مخرج في "الصحيحة" رقم ٢٧٨٦،
ይህን ሀዲስ ኢማሙል በይሀቂይ በጠንካራ(በሰሒሕ) ደረጃ ሲዘግቡት፣
ኢማሙ ጣሃዊያህ እና ኢስማዒሊይ በጠንካራ(በሰሒሕ) ደረጃ ዘግበውታል።
مع الآثار الموافقة له مما ذكرنا أعلاه، وكلها صحيحة
ሌሎችም የዚህን ሀዲስ ትክክለኝነት የሚደግፉ የቀደምቶች(የሰለፎች) ገለፃና ጥቆማ ያለ ሲሆን
السلسة الصحيحة ٢٧٨٦.
ኢማሙ አልባኒ ይህን ሀዲስ ሲልሲለቱ አሰሒሐህ ሐዲስ ቁጥር(2786) ላይ
ጠንካራ(ሰሒሕ) ሐዲስ ነው ብሎታል።
قال العلامة الإمام الألباني -رحمه الله-:
ኢማሙ አልባኒይ አላህ ይዘንላቸውና ከዚህ ሐዲስ በመነሳት…
المساجد التي يُعْتَكَفَ فيها
ኢዕቲካፍ ስለሚቻልባቸው(ስለተደነገገባቸው) መስጂዶች ሲያብራሩ…

وقفت على حديث صحيح صريح يخصص "المساجد" المذكورة في الآية -«ولا تباشروهن وأنتم عاكفون في المساجد»-(١) بالمساجد الثلاثة: المسجد الحرام, والمسجد النبوي, والمسجد الأقصى, وهو قوله ﷺ:
"لا اعتكاف إلا في المساجد الثلاثة"(٢)
《ቁርአን ላይ መስጂዶች በሚል የመጣው ኢቲካፍ የሚቻልባቸው መስጂዶች በዚህ የነብዩ ﷺ ጠንካራ(ሰሂህ) ሀዲስ ሚተሮገም በመሆኑ ኢዕቲካፍ የተደነገገላቸው መስጂዶች ሶስቱ መስጂዶች ማለትም መካ የሚገኘው ካዕባህ የሚገኝበት መስጂልሀረም፣መዲና የሚገኘው የነብዩ ﷺ መስጂድ)መስጂዱ ነበዊይ እና ፍልጤን ቁድስ ከተማ የሚገኘው መስጂደል አቅሷ ብቻ ናቸው።》

وقد قال به من السلف فيما اطلعت حذيفة بن اليمان, وسعيد بن المسيب, وعطاء, إلا أنه لم يذكر المسجد الأقصى,
ይህንን ኢዕቲካፍ በሶስቱ መስጂዶች ብቻ የተደነገገ መሆኑንና ከሶስቱ መስጂዶች ውጪ የሌለ መሆኑን ከቀደምቶች(ከሰለፎች) ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ ፣ ዓጣእ እና ሌሎችም የተቀበሉት ሲሆን
ከዚህ ዘመን ሙስሊም ሙሁራን ደግሞ አቡ ኡሳማህ ሰሊም ዒዲኒል ሒላሊይ ይገኙበታል።

وقال غيرهم بالمسجد الجامع مطلقا, وخالف آخرون فقالوا: ولو في مسجد بيته.
《ሌሎች ይህን ሀዲስ ባለመቀበል በማንኛውም ጀማዕ በሚሰገድበት መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ ይቻላል ያሉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ቤታችን ውስጣ ባለች መስጂድ(መስገጂያ ስፍራ(ሙሰላ) ውስጥ እንኳን ይቻላል።》 ብለዋል።

《ولا يخفى أن الأخذ بما وافق الحديث منها هو الذي ينبغي المصير إليه, والله سبحانه وتعالى أعلم.》

በመሆኑም ይላሉ ሸይኽ አልባኒ 《ከነብዩ ﷺ ሒዲስ ጋር የሚስማማው አባባል ኢዕቲካፍ በሶስቱ መስጂዶች ማለትም በመስጂደል ሀረም፣በመስጂደ ነበዊይ እና በመስጂደል አቅሷ ብቻ የተደነገገ መሆኑ ስለሆን ራስን በነብዩ ﷺ ሀዲስ ላይ መግታት ተገቢ ነው።》ብለዋል።

《من رأى أنه لااعتكاف إلا في ثلاثة مساجد :
عن عبد الرزاق عن الثوري عن واصل الأحدب عن إبراهيم قال جاء حذيفة إلى عبد الله فقال الا أعجبك من ناس عكوف بين دارك ودار الأشعري قال عبد الله فلعلهم أصابوا وأخطأت فقال حذيفة ما أبالي أفيه أعتكف أو في بيوتكم هذه إنما الاعتكاف في هذه المساجد الثلاثة مسجد الحرام ومسجد المدينة والمسجد الأقصى وكان الذين اعتكفوا فعاب عليهم حذيفة في مسجد الكوفة الأكبر》
ሁዘይፈተል የማኒ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ዘንድ በመምጣ
《በአንተና በአቡል ሀሰነል አሽዓሪይ መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ የገቡ ሰዎችን እንዴት ዝም ትላለህ ነብዩ ﷺ ከሶስቱ መስጂዶች ከመስጂደልሀረም፣ከመስጂነበዊይ እና ከመስጂደልአቅሷ ውጪ ኢዕቲካፍ የለም እንዳሉ እያወክ ሲለው ዓብደላ ኢብኑ መስዑድም አንተ ዘንግተህ እነሱ ደግሞ አስታውሰው ከሆነስ በማለት መልሶለታል።》
ሌላው መታወቅ ያለበት ነገር ነብዩ ﷺ ከመስጂደነበዊይ(ከመዲና መስጂድ) ውጪ ኢዕቲካፍ አልገቡም ነበር።
من سلسلة الهدى والنور
ምንጭ:
ሲልሲለቱልሁዳ ወኑር

للعلامة المحدث الشيخ الألباني -رحمه الله-
سئل عن الاعتكاف وأين يكون؟
الصوتية على الرابط:
ለበለጠ መረጃ ሼኽ አልባኒ ኢዕቲካፍ የት የት መስጂድ መግባት እንደሚቻል የገለፁበትን ድምፅ ቀጥሎ አለሎትና ያድምጡ

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 12/08/2014 ዓ ው
ረመዷን 19/09/1443 ዓ ሂ

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
http://www.alalbany.net/alalbany/audio/484/484_04.mp3
726 viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 11:54:39 ተሀጁድ መስገድ ቢድዓ ነውን????

ፈትዋ ቁጥር : 252

ጥያቄ
የተሀጁድ ሶላትን በተመለከተ በላጩ አቋም ቢብራራልን ፣ በዚህ ጉዳይ እኛ አካባቢ ለሁለት ተከፍለናል ፣ ግማሹ ይቻላል ሱና ነው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ቢድዓ ነው ይላሉ ፣ በተለይ የረመዷን የመጨረሻው ቀናቶች ላይ ማታ ተራዊህ ከሰገዱ በኃላ ለሊት ድጋሜ ለተሀጁድ መሰባበሰብን በተመለከተ በላጩ የትኛው ነው ከመረጃው ጋር????

መልስ
ይህን በተመለከተ በኡለሞች መካከል ሰፋ ያለ ልዩነት ያለበት ርእስ ነው።

ማለትም ከፊል ኡለሞች ተራዊህና ተሀጁድ የተለያዪ ናቸው ይላሉ ፣ ማለትም #ተራዊህ በረመዷን የሌሊቱ መጀመሪያ ላይ ማለትም ከኢሻ በኃላ የሚሰገድ ሲሆን ተሀጁድ ደግሞ ከተኙ በኃላ የሌሊቱ መጨረሻ ላይ የሚሰገድ ነው በማለታቸው የሚፈቀድ ነው ይላሉ።

የሌሎች ኡለሞች አቋም የሆነውና ከመረጃም አንፃር በላጩና አመዛኙ አቋም ደግሞ ተራዊህም ተሀጁድም የሌሊት ሶላትም አንድን ነገር የሚጠቁሙ የተለያዩ ቃላት እንጅ እርስ በራስ የተለያዩ አይደሉም።
ማለትም ሁሉም በሌሊት የሚሰገድ ሶላትን ይጠቁማሉ።

መጀመሪያና መጨረሻ ብሎ መለያየቱ ግልፅ ማስረጃ የለውም።
ይህ ተለምዷዊ ትርጓሜ እንደ ሸሪዓዊ ትርጓሜ አይደለም።

ማለትም ጥያቄ በተለምዶ ሰዎች ዘንድ ተራዊህ ማታ ከኢሻ በኃላ የሚሰገድና ቂርአቱ አነስ ያለ ሲሆን ተሀጂድ ደግሞ የሌሊቱ መጨረሻ ላይ ሆኖ ቂርአቱ ስለሚረዝም ነው። ሆኖም ይህ የቁርአን አንቀፅ የሚያመለክተው ሁሉንም ነው።

ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በርሱ (በቁርአን) ስገድ ፣ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል።"
ሱረቱል ኢስራእ ፣ 79

ከዚህ በመነሳት በአንድ ሌሊት ሁለት ጊዜ ለሶላት መሰበሰብ ማለትም ለተራዊህ ማታ አብረው ከሰገዱ በኃላ ወደ የቤታቸው ከሄዱ በኃላ የሌሊቱ መጨረሻ ላይ ተመልሰው ተሰባስበው መስገድ መሰረት የሌለው ነገር ነው።

በጥቅሉ #ሶላተልለይል ማለት ከኢሻ በኃላ እስከ ፈጅር ድረስ ባለው ወቅት ውስጥ የሚሰገድ ፣ ቁርአን በዛ ተደርጎ የሚቀራበት ትርፍ የሆነ የሌሊት ሶላት ሲሆን ይህ ሶላት ተራዊህ ወይም ተሀጁድ ተብሎ ሊጠራ ይችላል።

ለዛም ነው የሌሊቱ መጀመሪያም ይሁን መካከል ይሁን መጨረሻ ላይ መስገድ ቢቻልም በላጩ ግን የሌሊቱ የመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ላይ መስገድ ነው።

ምክንያቱም በዙህ ወቅት በሀዲስ እንደተገለፀው አሏህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የሚወርድበትና "ማነው የሚለምነኝ የምቀበለው" የሚልበት ሰአት በመሆኑና በርካታ ኡለሞች ዘንድ ከተኙ በኀላ ተነስቶ መስገድ በላጭ ስለሆነ ይህን ሱና ለማግኘት ሲባል ነው።
ምንጭ
መጅሙዑል ፈታዊ ኢብኑ ባዝ (317/11)
ፈታዊ ዑሰይሚን ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር ፣ 271ኛው ካሴት ፣
ፈታዊ ወረሳኢል ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አልዑሰይሚን ፣ 13ኛው ሙጀለድ ፣ ርእስ ቁርአቱል ፋቲሀ
ፈታዊ አልባኒ ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር ፣ 719ኛው ካሴት ፣
ኪታቡል ሙንተቃ ሊፈታዊል ፈውዛን ፣ 3/116

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 11/08/2014 ዓ ው
ረመዷን 18/09/1443 ዓ ሂ

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
767 views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 11:32:25 ተራዊሕ፣ተሀጁድ፣ለይል እና ዊትር!!!

ለመሆኑ ከረመዳን ከሀያ አንደኛው ቀን ጀምሮ የሚስገድ ተሀጁድ የሚባል ራሱን የቻለ ሰላት አለን????????????

በረመዳን ወር ብቻ የሚስገድ ተራዊህ የሚባል ራሱን የቻለ ሰላትስ አለን???????

በመጀመሪያ ማውቅ የሚገባን ቁምነገር ከዒሻእ ባዕዲያ ቡሀላ እስከ ፈጅር(ሱብሂ አዛን) ድረስ የሚሰገድ ማንኛውም ሰላት ቂያመለይል(ሰላተለይል) ማለትም የለሊት ሰላት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህ የሰላት አይነት በዚህ ስም መጠራቱ በሀዲስ የተረጋገጠ ነው።

በመሆኑም ነብዩ ﷺ ከረመዳን ውጪ ለየብቻ ሲሰገድ የነበረውን የለሊት ሰላትን(ሰላተለይልን) በረመዳን ወር በአንድነት እንዲሰገድ በተግባር ያሳዩት እንጂ ያው ከረመዳን ውጪ የሚሰገደው የለሊት ሰላት(ሰላተለይል) ራሱ ነው።

ከዚህ በተረፈ ግን ሰላተ ተራዊህ(የተራዊህ ሰላት) በቁርንም ሆነ በሀዲስ የለም ።

ሰላተ ተራዊህ የሚለውን ስያሜ ያገኘው ከነብዩ ﷺ ሞት ቡሀላ በአቡ በክር የኸሊፋነት ዘመን በረመዳን ወርንም ጭምር ተበታትነው ነበር የለሊትን ሰላት ሚሰግዱት።

ከአቡበክር ሞት ቡሀላ በዑመር የኸሊፋነት ዘመን ዑመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በአቡበከር በረመዳን ዘመን በረመዷን ወር ተበታትኖ ይሰግድ የነበረውን ህዝበ ሙስሊም ወደ ቀድሞው በጀምዓ ወደ መስገድ እንዲመጡ ካደረገ ቡሀላ ዑበይ ኢብኑ ካዕብንና ተሚሚኒዳርይ በአስራ አንድ ረካዕህ ኢማም ሆነው ሙስሊሞችን እንዲያሰግዱ አዟቸዋል።

ይሁንና እነኚህ ሁለት ኢማሞች ያለምንም እረፍት በተከታታይ በፍጥነት ሲያሰግዷቸው ያኔ ከሰጋጆች መሀከል አንዱ አሪሕና ያ ፉላን ማለትም እረፍት አየሰጠህን ብሎ በማለቱ የተነሳ ተራዊህ( ባለ እረፍቱ) ሰላት የሚልን ስያሜ አገኘ እንጂ ራሱን የቻለ ተራዊህ የሚባል ሰሏት እንደ ኢስላም የለም።

ሌላው ልብ መባል ያለበት ቁም ነገር ነብዩ ﷺ በረመዳንም ሆነ ከረመዷን ውጪ በለሊቱ መጀመሪያም በለሊቱ መሀከልና በለሊቱ መጨረሻ ሰላተለይልን የሰገዱ ሲሆን በመጨረሻ የሂይወት ዘመናቸው ግን በለሊቱ መጨረሻ ነበር ሚስግዱት።

ኡመር በረመዳን በጀምዓህ እንዲሰገድ ሲያደርግ ሽማግሌዎች አሮጊቶችና ህፃናት እንዲሁም ሴቶች በሙሉ እንዲሳተፉ ለማድረግ በግዜ እንዲሰገድ አድርጎ ነበር።

በመጨረሻ እድሜው አካባቢ ግን 《ነብዩ ﷺ ወደ ለሊቱ መጨረሻ አካባቢ ነውና የሰገዱት ይህቺን የለሊት ሰላት ነብዩ ﷺ ወደ ሰገዱበት ወቅት ወደ ለሊቱ መጨራሻ እመልሳታለው እያለ ሳይመልሳትም የአላህ ውሳኔ ሞት ቀድሞታል።》

ከዚህ ውጪ ግን ተራዊህ ማለት በግዜ ከዒሻእ ቀጥሎ ሚሰገድ ተሀጁድ ደግሞ በለሊቱ መጨረሻ አካባቢ ሚሰገድ አድርገን ማሰብ ተገቢ አይደለም ይህ ፍፁም ስህተት ነው።

እንደ ኢስላም ተሀጁድ ሚባል ሰላት የሌለና በቁርአንም ሆነ በሀዲስ ያልተወሳ ተግባር ነው።

﴿وَمِنَ اللَّيلِ فَتَهَجَّد بِهِ نافِلَةً لَكَ عَسى أَن يَبعَثَكَ رَبُّكَ مَقامًا مَحمودًا﴾
سورة الإسراء..(79)

《ሙሀመድ ሆይ በለሊት ሰላትህ(በሰላተለይልህ) ውስጥ ቁርአንን አርዝመህ በመቅራት ላይ ተበራታበት።》
ማለት ነው እንጂ ተሀጁድ ሚባለውን ሰላት ስገድ ማለት አይደለም
ሱረቱል ኢስራእ(79)


ሌላው ማወቅ ያለብ ዋናው ነጥብ ከረመዳን ከሀያ አንደኛው ለሊት ጀምሮ ከዒሻእ ቀጥሎ ተራዊህ ሊነጋጋ ሲል ተሀጁድ ብሎ በአንድ ለሊት ሁለቴ እሱንም ከአስራአንድ አለያም ከአስራሶስት ረካዓህ በላይ መስገድ በኢስላም ያልተደነገገ የአሰጋገድ ተግባር ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከረመዷን አንድ እስከ ሀያኛው ለሊት ከዒሻእ ቀጥሎ ተራዊሕ እየተሰገደ ቆይቶ ከሀያ አንደኛው ለሊት ጀምሮ ተራዊህ የለም ተሀጁድ ነው እየተባለ ሊነጋጋ ሲል መስገድም የሌለ ነው።

ነብዩ ﷺ የረመዷን የመጨረሻው አስር ቀናቶች ሲጀምሩ ሽርጣቸውን ጠበቅ ያደርጉ ነበር ቤተሰቦቻቸውን እንዳይተኙ ያነቁ ነበር ለሊቱን ያለ እንቅልፍ ህያው ያደርጉት ነበር ማለት በአንድ ለሊት ሁለቴ ይሰግኑ ነበር ማለት አይደለም።

ሌላ ግዜ የሚሰግዱት የለሊት ሰላት ቁጥር ያህል ከሰገዱ ቡሀላ በተለያዩ የዒባዳህ(የዓምልኮ አይነቶች ለምሳሌ ለረጅም ሰአት ኢስግፋርና ተውበት በማድረግ ፣ለረጅም ሰአት ዚክር በማድረግ፣ለረጅም ሰአት ዱዓ በማድረግ፣ ለረጅም ሰአት ቁርአን በመቅራትና በመቃራት እንዲሁም ሌሎችንም የዒባዳህ አይነቶችን በመተግበር) ለሊቱን በኢባዳ ያነጉ ነበር ለማለት ነው።

በጥቅሉ ማወቅ የሚገባን ነገር ነብዩ ﷺ በስተመጨረሻ እድሜያቸውም ሆነ በረመዷን ውስጥ የሰገዱት የለሊቱን የመጨረሻ ወቅት(ሊንጋጋት አቅራቢያ) ሲሆን ከተቻለ የረመዷንን ሰላሳውን ለሊቶች የለሊቱን መጨረሻ አካባቢ(ከሰባት ሰአት እስከ ሱሁር ባለው ሰአት አካባቢ በስብስብ መስገድ ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን ሰላሳውንም የረመዷን ለሊቶች ከዒሻእ ቀጥሎ በስብስብ አስራአንድ ረካዕህ የለሊት ሰላትን መስገድ ነው ሚገባው።

ነብዩ ﷺ 《የለሊት ሰላት በሁለት በሁለት ረካዓህ የሚስገድ ነው።》
ማለታቸው በሁለት በሁለት ረካዓህ እስከፈለጉት ያህል ድረስ መስገድ ይቻላል ማለት አይደለም።

ይህ ሀዲስ የቁጥር መጠንን ሳይሆን የአሰጋገድ እንዴታነት(ሁኔታን) ብቻ ነው ሚገልፀው።

በተጨማሪ መታወቅ ያለበት ነብዩ ﷺ የለሊት ሰላት ሌሎችን ባልረበሸ መልኩ በመጠነኛ ድምፅ ስገዱ ማለታቸውንም መርሳት የለብንም።

ስናጠቃልል ተራዊህና ተሀጁድ የሚባሉት ሁለት ስያሜዎች ለቂያመለይል(ለሰላተልለይል) ተለዋጭ እንዲሆኑ በማሰብ የተሰየሙ ስያሜዎች እንጂ ራሳቸውን የቻሉ ከለይል ሰላት የተለዩ ሰላቶች አይደሉም።

ዊትር ደግሞ የለሊት ሰላት መደምደሚያ ሲሆን በአንድ ረካዓህ፣ወይም በሶስት ረካዓህ ወይም በአምስት ረካዓህ አለያም በሰባት ረካዕህ በጎዶል ቁጥሮች የሚሰገድ የለይል ሰላት መደምደሚያ የሰላት አይነት ነው።

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 06/08/2014ዓ ው
ረመዷን 13/09/1443 ዓ ሂ

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
1.2K viewsedited  08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 14:05:42 እምነትን በሀይል የማስቀየር ተግባር!!!!

የአንድን ህዝብ ወይም ግለሰብ እምነቱን በሀይል የማስቀየር ተግባር የሚጀምረው ግለሰቡ ወይም ህዝቡ እምነቱን በእምነቱ ስርአት መሰረት ማከናወን በመከልከል ይጀምራል።

ሰሞኑኑ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ተማሪዎች ሰላት እንዳይሰግዱ መከልከላቸው ህዝበ ሙስሊሙን እምነት የማስቀየር እንደ አንድ እርምጃ ሊወሰድ የሚችል ነውረኛ ተግባር ነው!!!!!!።

አሁን አሁን ገዢው ፓርቲ ውስጥ ያላቸውን ስልጣን ተጠቅመው በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የበደል በትራቸውን ለማሳረፍ የሚደረጉ ተደጋጋሚ ሙከራዎችና ሩጫዎች ውጤቱ ዘሎ ጥልቅ መውጪያ ጭንቅ》 እንዳይሆን።

ሰይፍን ማን እንደመዘዘው ብቻ ነው ሚታወቀው ማንን እንደሚሰይፍና ማንን እንደሚበላ ግን ከፍልሚያ ቡሀላ እንጂ ከፍልሚያው በፊት አይታወቅም።

ገዢው ፓርቲ ኢስላምን በተመለከተ ጤናማ ፕሮግራም እንደሌለው ከቅርብ ግዜ ጀምሮ በቱሪዝም ሚኒስቴሩ እና በትምህርት ሚኒስቴሩ ብርሀኑ ነጋ አማካኝነት ግልፅ እያደረገ እየመጣ ነው!!!!!

ማንም ይምጣ ማን ምንም ይታሰብ ምን ህዝበ ሙስሊሙ የትኛውንም መሰዋአትነት ከፍሎ ይቀለብሰዋል!!!።

ካቲብ

ሚያዚያ 02/08/2014 ዓ ል

ረመዷን 09/09/1443 ዓ ሂ

https://t.me/zekatib11
878 views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 13:35:29 ረመዷንና የፆም ህግጋት

ክፍል አራት

ፆምን የሚያበላሹ ነገራት
ትምህርት_ሁለት

3ኛ: በፆም እለት ወሲባዊ ግንኙነት መፈፀም(ጂማዕ ማድረግ)።

الجماع، وهو أغلط أنواع المفطرات، لوجوب الكفارة فيه، والكفارة هي عتق رقبة، فإن لم يجد فصيام شهرين متتابعين،فإن لم يستطع فإطعام ستبن مسكيا.

《ፆምን ከሚያበላሹ ነገራት በወንጀልነቱ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ወሲባዊ ግንኙነት ሲሆን አንደ ሰው በረመዷን ፆም በቀን አውቆና ፈቅዶ ወሲባዊ ግንኙነት ከፈፀም ፆሙ ይበላሻል።
ለፈፀመውም ወንጀል ማስማሪያ አንድ ባሪያ ነፃ ማውጣት ግዴት የሚሆንበት ሲሆን ይህንን የሚያደርግበት አቅም ካጣ ሁለት ወር በተከታታይ መፆም ግዴታ ይሆንበታል። ይህንን ማድረግ ማይችል ከሆነ ደግሞ ስልሳ(60) ሚስኪን ይመግባል(ያበላል)

4ኛ: የወር አበባ(የሐይድ) ደም እና የአራስነት ደም መታየት(መምጣት) ነው።

خروج دم الحيض او النفاس
فإذا خرج.من المرأت دم الحيض إو النفاس ولو قبل الغروب بلحظة فسد الصوم وإن خرج دم النفاس أو الحيض بعد الغروب بلحظة واحدة صح صومها.

የሐይድ ወይም የአራስነት ደም መታየት(መምጣት) ፆምን ያበላሻል።

አንድ ሴት ልጅ ፆማ ውላ ለፈጥር ጥቂት ሰአት ሲቀረው የወር አበባዋ ወይም የአራሰነት ደም ከታያት ፆሟ የሚበላሽ ሲሆን ፀሐይ እንደገባች ወዲያው የወር አበባዋ ወይም የአራስነት ደሟ ብቅ ካለ ፆሟ ትክክል ይሆናል።
مجموع فتاوى إبن عثيمين(19/142) سؤال رقم(641)
መጅሙዕል ፈታዋ ኢብኑ ዑሰይሚን(19/142) ፈትዋ ቁጥር(641)

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 01/08/2014 ዓ ል
ረመዷን 08/09/1443ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah
936 views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 13:41:41 የረመዷንና የፆም ህግጋት

ክፍል_ሶስት

ፆምን የሚያበላሹ ነገራት

ትምህርት_አንድ

1ኛ: መብላትና መጠጣት

በረመዷን ወይ በፆም እለት ከፈጅር መግባት ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ማምኛውንም ምግብና መጠጥ ሀላል ይሁን ሐራም፣ ለተመጋቢው የሚጠቅም ይሁን አይሁን እንዲሁም በምግብነቱ የታወቀ ይሁን አይሁን መመገብና መጠጣት ፆምን ሙሉ በሙሉ ያበላሻል ።

ማስረጃውም ይህ የቁርአን አንቀፅ ነው።

كلوا واشربوا حتى يتبين لكم الخيط الأبيض من الخيط الأسود من الفجر ثم أتموا الصيام إلى الليل 》
سورة البقرة (187)

《ጥቁር ክር ከነጭ ክር እስከሚለይ ድረስ ፈጅር መግባቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ብሉም ጠጡም።》
ሱረቱል በቀራህ(187)


ابن.قدامة رحمه الله أجمع إهل العلم على إفطار بالاكل والشرب لما يتغذى به
فأما أكل ما لا يتغذى به فيحصل به الفطر في قول عامة أهل العلم.
الشرح الكبير《لابن قدامة رحمه الله (3/36)

ኢብኑ ቁዳማህ አላህ ይዘንላቸውና《ለምግብነት የሚውሉ ነገራትን በፆም ምድር መመገብ ፆምን የሚያበላሽ በመሆኑ ላይ ሙስሊም ሊቃውንት ያለአንዳች ልዩነት ተስማምተውበታል( ኢጅማዕ አድርገውበታል) እንደዚሁም
ለምግብነት የማይውልም ሆነ የተመጋቢውን አካል አንዳችን ጥቅም የማያስገኝ ነገር በፆም ምድር በአፍ ወይም በአፍንጫ በኩል መመገብ ፆምን በማበላሸቱ ላይ አብዛኛው ሙስሊም ሊቃውንት ተስማምተውበታል።》

2ኛ:ምግብንና መጠጥን ተክቶ ሊያገለግል የሚችል ነገር በአጠቃላይ በአፍና በአፍንጫ በኩል ባይወሰድም በመርፌ መልክ በቆዳ፣በስጋና በደምስር በኩል መውሰድ ፆምን ያበላሻል።》

《الإبر والحقن العلاجية ما يقصد به التغذية ويستعنى به عن الأكل والشرب يفسد الصوم لأنه بمعنى الأكل والشرب》
مجموع فتاوى ابن عثيمين (19/154) سوال رقم(951)

《በጉሉኮስ መልኩ በደምስር የሚውሰድ የምግብነት ይዘት ያለው የህክምና መርጃና እንደ ቫይታሚን ፣ሚነራል(ማዓድን)ና ምግብን ተክቶ የሚያገለግል መርፌ መወጋት ፆምን ያበላሻል። ምክንያቱን ምግብና መጠጥ የሚያሰገኘውን አገልግሎት ያስገኛሉና》
መጅሙዕል ፈታዋ ኢብኑ ዑሰይሚን(19/154)
ፈትዋ ቂጥር(951)

አቡ ኢብራሂም

28/07/2014 ዓ ል
ረመዷን 05/09/1443ዓ ሂ
https://telegram.me/alfikhul_islamiyah
934 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 10:29:36 ረመዷንና የፆም ህግጋት

ክፍል_ ሁለት

የፍጡር(ማፍጠሪያ)ወቅት
እና
ሲፈጠር የሚባል ዚክር

《 ثم أتموا الصيام إلى الليل》
سورة البقرة(187)
አምላካችን አላህ ሱረቱል በቀራ ቁጥር 187 ላይ(ፆምን እስከምሽት ድረስ በመፆም አሙሉ።》 ብሎናል።

በዚህ የቁርአን አንቀፅ ውስጥ ምሽት በሚል የተገለፀው ትክከለኛ ወቅት በሚቀጥለው ትክክለኛ(ሰሒህ) ሐዲስ ተብራርቷል።

وعن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال قال رسول الله ﷺ 《إذا أقبل الليل من ها هنا، وأدبر النهار من ها هناوغربت الشمس فقد أفطر الصائم》
متفق عليه
ዑመር ኢብኑል ኸጣብ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና በዘገበው ሐዲስ ነብዩﷺ《ምሽቱ ከዚህ በኩል ሲመጣ፣ ከዚህ በኩል ደግሞ ቀኑ ሲሄድና ፀሐይ ስትጠልቅ ፆመኛ ያፍጥር።》ብለዋል
ስለዚህ ትክከለኛው የፉጥር ወቅት ፀሐይ እንደጠለቀች ነው።

ስለሆነም ፆመኞች ልብ ልንለው የሚገባው ነገር ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መብላት፣ መጠጣትና ወሲባዊ ግንኙነት መፈፀም ፆምን ሚያበላሽ መሆኑንና ፀሐይ ከጠለቀች በኀላ በቶሎ አለማፍጠር የተጠላ ሲሆን ከዚህም ባለፈ ክልክል(ሐራም) ይሆናል።

وعن ابن عمر رضي الله عنه قال كان رسول الله ﷺ إذا أفطر قال《ذهب الظمأ وابتلت العروق وثبت الأجر إن شاء الله》
أخرجه أبو داود في سننه برقم (2357). وصححه الألباني رحمه الله

ፆመኞች ሲያፈጥሩ ሊሉት(ሊያነቡት) የሚገባ ዚክር የተደነገገ ሲሆን ከመጡት ዚክሮች ውስጥ ትክክለኝነቱ በሐዲስ ሊቃውንት የታመነበት ይህ ከላይ የተጠቀሰው ሲሆን ንባቡም
《ዘሀበ_ዘማኡ, ወብተለቲል_ዑሩቁ ወሰበተል_አጅሩ ኢንሻአላህ።》

ትርጉሙም:
《ጥማቱም ተወገድ፣ጉሮሮዎችም ረጠቡ በአላህ መልካም ፍቃድ ምንዳውም ተረጋገጠ?》ማለት ነው።
ይህን ሐዲስ አቡዳውድ በሱነናቸው ቀጥር(2357) ላይ ሲዘግቡት ኢማሙ አልባኒይ ትክክለኛ(ሰሒህ) ሐዲስ ነው ብለውታል።

ይህንንም ሐዲስ ራሱ ደካማ ነው ያሉ የሐዲስ ሊቃውንተ አልጠፉም።

አቡ ኢብራሂም

መጋቢት 26/07/2014 ዓ ል
ረመዷን 03/09/1443ዓ ሂ

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah
682 views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 11:14:29 ኢርሻዱል በሪያህ

إرشاد البرية إلى شرعية الإنتساب للسلفية ودحض الشبه البدعية》
《 ኢርሻዱል በሪያህ ኢላ ሸርዒየቲል ኢንቲሳቢ ሊሰለፊያ》
ክፍል አምስት

መቅድም (المقدمة)

قال أبو عبد السلام حسن بن قاسم الحسني الريمي السلفي في إرشاد البريته
አቡ ዓብድሰላም ሐሰን ቢን ቃሲም......

قال ابن كثير عند قوله تعالى《﴿يَومَ نَدعو كُلَّ أُناسٍ بِإِمامِهِم )(ألإسراء 71)
ኢብኑ ከሲር አላህ ይዘንላቸውና ይህንን የቁርአን አንቀፅን(ሁሉንም ትውልድ በኢማሙ(በመሪው) አማካኝነት በምንጠራው ቀን) በተመለከተ ሲያብራሩ…

يخبر تبارك وتعالى عن يوم القيامة أنه يحاسب كل أمة بإمامهم،
ልቅናው የተባረከው አላህ በዚህ የቁርአን አንቀፅ ውስጥ በእለተ ቂያማ እያንዳንዱን ትውልድ በኢማሙ(መሪው) አማካኝነት አስጠርቶ እንደሚያስበው እየተናገረ ነው።

وقد اختلفوا في ذالك فقال مجاهد وقتادة أي نبيهم،
የቁርአን ሊሒቃን ለዚህ የቁርአን አንቀፅ ምንም እንኳን የተለያየ ትርጓሜን የሰጡት ቢሆንም ሙጃሂድና ቀታዳህ ግን በእለተ ቂያማ ሁሉም ትውልድ በተላከለት ነብይ አማካኝነት ነው የሚጠራው ብለዋል።

وهذا كقوله تعالى(﴿وَلِكُلِّ أُمَّةٍ رَسولٌ فَإِذا جاءَ رَسولُهُم قُضِيَ بَينَهُم بِالقِسطِ وَهُم لا يُظلَمونَ﴾(بونس 47)
ይህ የእነ ሙጃሂድና የቀታዳህ ትርጉም ከዚህ የቁርአን አንቀፅ ጋር የሚጣጣም ነው።
(ለእያንዳንዱ ትውልድ መልዕክተኛ ልከናል በእለተ ቂያማም በመልእክተኛቸው መሪነት እየመጡ ነው ሚፈረድባቸው።》

وقال بعض السلف: هذا أكبر شرف لأصحاب الحديث لأن إمامهم النبي ﷺ
ይህ ትውልዱ በሙሉ በእለት ትንሰኤ በተላከለት ነብይ ኢማምነት መጠራቱ ለሐዲስ ባለቤቶች ለሱኒዮች ትልቅ ክብር ነው።》ብለዋል።

وقال الشيخ مقبل ابن هادي الوادعي 《مؤسس الدعوة السلفية وهو رسول الله ﷺ
ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሀዲ አልዋዲዒይ 《የሰለፊያ አስተምህሮት መስራች ነብዩ ﷺ ናቸው።》ብለዋል።
ኢርሸዱል በሪያህ(11_12)

መጋቢት 25/07/2014 ዓ ል

ረመዷን 02/09/1443 ዓ ል

አቡ ኢብራሂም

http://telegram.me/abuibrahim0102030405
585 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ