Get Mystery Box with random crypto!

ተራዊሕ፣ተሀጁድ፣ለይል እና ዊትር!!! ለመሆኑ ከረመዳን ከሀያ አንደኛው ቀን ጀምሮ የሚስገድ ተ | Sunnah Media Zone 」【SMZ】

ተራዊሕ፣ተሀጁድ፣ለይል እና ዊትር!!!

ለመሆኑ ከረመዳን ከሀያ አንደኛው ቀን ጀምሮ የሚስገድ ተሀጁድ የሚባል ራሱን የቻለ ሰላት አለን????????????

በረመዳን ወር ብቻ የሚስገድ ተራዊህ የሚባል ራሱን የቻለ ሰላትስ አለን???????

በመጀመሪያ ማውቅ የሚገባን ቁምነገር ከዒሻእ ባዕዲያ ቡሀላ እስከ ፈጅር(ሱብሂ አዛን) ድረስ የሚሰገድ ማንኛውም ሰላት ቂያመለይል(ሰላተለይል) ማለትም የለሊት ሰላት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህ የሰላት አይነት በዚህ ስም መጠራቱ በሀዲስ የተረጋገጠ ነው።

በመሆኑም ነብዩ ﷺ ከረመዳን ውጪ ለየብቻ ሲሰገድ የነበረውን የለሊት ሰላትን(ሰላተለይልን) በረመዳን ወር በአንድነት እንዲሰገድ በተግባር ያሳዩት እንጂ ያው ከረመዳን ውጪ የሚሰገደው የለሊት ሰላት(ሰላተለይል) ራሱ ነው።

ከዚህ በተረፈ ግን ሰላተ ተራዊህ(የተራዊህ ሰላት) በቁርንም ሆነ በሀዲስ የለም ።

ሰላተ ተራዊህ የሚለውን ስያሜ ያገኘው ከነብዩ ﷺ ሞት ቡሀላ በአቡ በክር የኸሊፋነት ዘመን በረመዳን ወርንም ጭምር ተበታትነው ነበር የለሊትን ሰላት ሚሰግዱት።

ከአቡበክር ሞት ቡሀላ በዑመር የኸሊፋነት ዘመን ዑመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በአቡበከር በረመዳን ዘመን በረመዷን ወር ተበታትኖ ይሰግድ የነበረውን ህዝበ ሙስሊም ወደ ቀድሞው በጀምዓ ወደ መስገድ እንዲመጡ ካደረገ ቡሀላ ዑበይ ኢብኑ ካዕብንና ተሚሚኒዳርይ በአስራ አንድ ረካዕህ ኢማም ሆነው ሙስሊሞችን እንዲያሰግዱ አዟቸዋል።

ይሁንና እነኚህ ሁለት ኢማሞች ያለምንም እረፍት በተከታታይ በፍጥነት ሲያሰግዷቸው ያኔ ከሰጋጆች መሀከል አንዱ አሪሕና ያ ፉላን ማለትም እረፍት አየሰጠህን ብሎ በማለቱ የተነሳ ተራዊህ( ባለ እረፍቱ) ሰላት የሚልን ስያሜ አገኘ እንጂ ራሱን የቻለ ተራዊህ የሚባል ሰሏት እንደ ኢስላም የለም።

ሌላው ልብ መባል ያለበት ቁም ነገር ነብዩ ﷺ በረመዳንም ሆነ ከረመዷን ውጪ በለሊቱ መጀመሪያም በለሊቱ መሀከልና በለሊቱ መጨረሻ ሰላተለይልን የሰገዱ ሲሆን በመጨረሻ የሂይወት ዘመናቸው ግን በለሊቱ መጨረሻ ነበር ሚስግዱት።

ኡመር በረመዳን በጀምዓህ እንዲሰገድ ሲያደርግ ሽማግሌዎች አሮጊቶችና ህፃናት እንዲሁም ሴቶች በሙሉ እንዲሳተፉ ለማድረግ በግዜ እንዲሰገድ አድርጎ ነበር።

በመጨረሻ እድሜው አካባቢ ግን 《ነብዩ ﷺ ወደ ለሊቱ መጨረሻ አካባቢ ነውና የሰገዱት ይህቺን የለሊት ሰላት ነብዩ ﷺ ወደ ሰገዱበት ወቅት ወደ ለሊቱ መጨራሻ እመልሳታለው እያለ ሳይመልሳትም የአላህ ውሳኔ ሞት ቀድሞታል።》

ከዚህ ውጪ ግን ተራዊህ ማለት በግዜ ከዒሻእ ቀጥሎ ሚሰገድ ተሀጁድ ደግሞ በለሊቱ መጨረሻ አካባቢ ሚሰገድ አድርገን ማሰብ ተገቢ አይደለም ይህ ፍፁም ስህተት ነው።

እንደ ኢስላም ተሀጁድ ሚባል ሰላት የሌለና በቁርአንም ሆነ በሀዲስ ያልተወሳ ተግባር ነው።

﴿وَمِنَ اللَّيلِ فَتَهَجَّد بِهِ نافِلَةً لَكَ عَسى أَن يَبعَثَكَ رَبُّكَ مَقامًا مَحمودًا﴾
سورة الإسراء..(79)

《ሙሀመድ ሆይ በለሊት ሰላትህ(በሰላተለይልህ) ውስጥ ቁርአንን አርዝመህ በመቅራት ላይ ተበራታበት።》
ማለት ነው እንጂ ተሀጁድ ሚባለውን ሰላት ስገድ ማለት አይደለም
ሱረቱል ኢስራእ(79)


ሌላው ማወቅ ያለብ ዋናው ነጥብ ከረመዳን ከሀያ አንደኛው ለሊት ጀምሮ ከዒሻእ ቀጥሎ ተራዊህ ሊነጋጋ ሲል ተሀጁድ ብሎ በአንድ ለሊት ሁለቴ እሱንም ከአስራአንድ አለያም ከአስራሶስት ረካዓህ በላይ መስገድ በኢስላም ያልተደነገገ የአሰጋገድ ተግባር ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከረመዷን አንድ እስከ ሀያኛው ለሊት ከዒሻእ ቀጥሎ ተራዊሕ እየተሰገደ ቆይቶ ከሀያ አንደኛው ለሊት ጀምሮ ተራዊህ የለም ተሀጁድ ነው እየተባለ ሊነጋጋ ሲል መስገድም የሌለ ነው።

ነብዩ ﷺ የረመዷን የመጨረሻው አስር ቀናቶች ሲጀምሩ ሽርጣቸውን ጠበቅ ያደርጉ ነበር ቤተሰቦቻቸውን እንዳይተኙ ያነቁ ነበር ለሊቱን ያለ እንቅልፍ ህያው ያደርጉት ነበር ማለት በአንድ ለሊት ሁለቴ ይሰግኑ ነበር ማለት አይደለም።

ሌላ ግዜ የሚሰግዱት የለሊት ሰላት ቁጥር ያህል ከሰገዱ ቡሀላ በተለያዩ የዒባዳህ(የዓምልኮ አይነቶች ለምሳሌ ለረጅም ሰአት ኢስግፋርና ተውበት በማድረግ ፣ለረጅም ሰአት ዚክር በማድረግ፣ለረጅም ሰአት ዱዓ በማድረግ፣ ለረጅም ሰአት ቁርአን በመቅራትና በመቃራት እንዲሁም ሌሎችንም የዒባዳህ አይነቶችን በመተግበር) ለሊቱን በኢባዳ ያነጉ ነበር ለማለት ነው።

በጥቅሉ ማወቅ የሚገባን ነገር ነብዩ ﷺ በስተመጨረሻ እድሜያቸውም ሆነ በረመዷን ውስጥ የሰገዱት የለሊቱን የመጨረሻ ወቅት(ሊንጋጋት አቅራቢያ) ሲሆን ከተቻለ የረመዷንን ሰላሳውን ለሊቶች የለሊቱን መጨረሻ አካባቢ(ከሰባት ሰአት እስከ ሱሁር ባለው ሰአት አካባቢ በስብስብ መስገድ ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን ሰላሳውንም የረመዷን ለሊቶች ከዒሻእ ቀጥሎ በስብስብ አስራአንድ ረካዕህ የለሊት ሰላትን መስገድ ነው ሚገባው።

ነብዩ ﷺ 《የለሊት ሰላት በሁለት በሁለት ረካዓህ የሚስገድ ነው።》
ማለታቸው በሁለት በሁለት ረካዓህ እስከፈለጉት ያህል ድረስ መስገድ ይቻላል ማለት አይደለም።

ይህ ሀዲስ የቁጥር መጠንን ሳይሆን የአሰጋገድ እንዴታነት(ሁኔታን) ብቻ ነው ሚገልፀው።

በተጨማሪ መታወቅ ያለበት ነብዩ ﷺ የለሊት ሰላት ሌሎችን ባልረበሸ መልኩ በመጠነኛ ድምፅ ስገዱ ማለታቸውንም መርሳት የለብንም።

ስናጠቃልል ተራዊህና ተሀጁድ የሚባሉት ሁለት ስያሜዎች ለቂያመለይል(ለሰላተልለይል) ተለዋጭ እንዲሆኑ በማሰብ የተሰየሙ ስያሜዎች እንጂ ራሳቸውን የቻሉ ከለይል ሰላት የተለዩ ሰላቶች አይደሉም።

ዊትር ደግሞ የለሊት ሰላት መደምደሚያ ሲሆን በአንድ ረካዓህ፣ወይም በሶስት ረካዓህ ወይም በአምስት ረካዓህ አለያም በሰባት ረካዕህ በጎዶል ቁጥሮች የሚሰገድ የለይል ሰላት መደምደሚያ የሰላት አይነት ነው።

አቡ ኢብራሂም

ሚያዚያ 06/08/2014ዓ ው
ረመዷን 13/09/1443 ዓ ሂ

http://telegram.me/abuibrahim0102030405