Get Mystery Box with random crypto!

Abel Birhanu የወይኗ ልጅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abe11 — Abel Birhanu የወይኗ ልጅ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abe11 — Abel Birhanu የወይኗ ልጅ
የሰርጥ አድራሻ: @abe11
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.46K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!
@abel21bot

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-06-24 14:42:41

14.2K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 14:56:06

16.6K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 13:07:28
አፍጋኒስታን ባጋጠማት የመሬት መንቀጥቀጥ ከአንድ ሺህ በላይ ዜጎቿን አጥታለች፡፡

➪ከ6 ነጥብ 1 ሬክተር ስኬል በላይ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰሜናዊ አፍጋን እና ፓኪስታን የሚገኙ ተራራማ አካባቢዎችን አጥቅቷል፡፡

➪ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን ተጎጂዎችን የማዳን እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ የታሊባን አደጋ ጊዜ ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡

➪አደጋው የተከሰተው ገጠራማ አካባቢዎች ላይ በመሆኑ ፈጣን እርዳታ ለማድረስ ፈተና ገጥሞት እንደነበርም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

➪የታሊባን አየር ሃይል ተጎጂዎችን ለመርዳት እና አስፈላጊ ድጋፎችን ለማቅረብ ግዳጅ ላይ እንደሚገኝም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

# Ethio Fm
13.8K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 12:56:55

11.6K views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 08:25:05
ብሪታንያ ለአፍሪካ ቀንድና ለቀይ ባሕር ቀጠና አዲስ ልዩ ልዑክ ሾመች

➪ ብሪታንያ ለአፍሪካ ቀንድና የቀይ ባሕር ቀጠና ሳራ ሞንትጎመሪን አዲስ ልዩ ልዑክ አድርጋ መሾሟን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤቷ በኩል አስታውቃለች። ልዩ ልዑኳ በቀይ ባሕር አካባቢ ትኩረት ያደረጉ ዓለማቀፍ ኃይሎች ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጋር የብሪታንያን ፖሊሲና ምላሾች ያቀናጃሉ።

➪ሳራ ሞንትጎመሪ ላለፉት 8 ወራት በቀጠናው የአገሪቱ ልዩ ልዑክ የሆኑትን ፊሊፕ ፓራምን ይተካሉ። አዲሷ መልዕክተኛ ቀደም ሲል በኬንያ፣ የመን እና ኢራን ተመድበው ሰርተዋል።

Ethiopia insider
12.0K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 11:17:29
ሩስያ ላይ የተጣሉ ማእቀቦች የምግብ እና የግብርና ማዳበሪያን እንደማይመለከቱ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ::

➪የህብረቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፍ ቦሬል እንዳስታወቁት፣ከሩስያ ጋር የትኛውንም አይነት የምግብ እና የግብርና ግብአቶችን የሚገበያይ አካል የሚጣልበት ማእቀብ የለም፡፡
በመሆኑም የዘርፉን ግብይት የሚፈፅሙ አካላት ያለምንም መሳቀቅ ይፋዊ ግብይትን ማድረግ ይችላሉ ብለዋል፡፡

➪የጣልናቸው የኢኮኖሚ ማእቀቦች ግባቸው የሩስያን ኢኮኖሚ ማዳከም እንጂ የዓለምን የምግብ እና ተያያዥ ችግሮችን ለማባባስ ያለሙ አይደሉም፣ መሰናክልም አይሆኑም ብለዋል ጆሴፍ ቦሬል፡፡

➪በመሆኑም ከምግብ እና ማዳበሪያ ጋር የተያያዙ ግዢዎች ያለ ድብብቆሽ በይፋ መዋዋል መገበያየት እንዲሁም ከሩስያ ወደቦች መጫን እና የገንዘብ ዝውውርን ማካሄድ ይችላሉ ነዉ ያሉት፡፡

➪የህብረቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፍ ቦሬል በአለም አቀፍ ደረጃ ለተከሰተው የምግብ ቀውስ እና የዋጋ መናር የአውሮፓ ህብረት እና ማእቀቡን ተጠያቂ ማድረግ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ በበኩሏ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በሰጠቻቸዉ መግለጫዎች በዓሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተከሰተዉ የኑሮ ዉድነትና ኢኮኖሚያዊ ጫና አሜሪካና ምዕራባዊያን የጧሏቸዉ ማዕቀቦች መሆናቸዉን ገልጻለች፡፡

# Ethio Fm
13.2K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 10:08:39
አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

➯ በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ የእጽዋት ማእከል እየተካሄደ በሚገኘው መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ሚኒስትሮች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም አትሌቶችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

➯ባልፉት ሶስት አመታት በሶስት ዙር 20 ሚሊየን ዜጐችን በማሳተፍ 18 ቢሊዮን ችግኞች መተከሉ ተገልጿል።
11.1K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 10:07:50
የተምች ወረርሽኝ በ111 ሺሕ ሄክታር የእርሻና የከብት ግጦሽ መሬት ላይ መከሰቱ ተገለጸ

➯በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጥበቃ ዳይሬክተር በላይነህ ንጉሤ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ በሰባት ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል፣ በአማራ ክልል፣ በሲዳማ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተምች ወረርሽኝ መከሰቱን ተናግረዋል።

➯በተጠቀሱት ክልሎች በ25 ዞኖች፣ በ113 ወረዳዎች የተምቹ ወረርሽኝ እንደተከሰተ እና በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የግብርና ሚኒስቴር በቴርሞ ሜትር አማካኝነት ቀድሞ መተንበይ የተቻለ ሲሆን፣ የተምቹ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ የፀረ ተባይ ኬሚካሎችን፣ የኬሚካል መርጫ መሣሪያዎችን እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ወደ ክልሎች ቀድሞ መላክ መቻሉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

አዲስ ማለዳ
10.8K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 18:22:46
ሱዳን 21 የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ለግብፅ አሳልፋ ሰጠች።

➪የሱዳን ባለስልጣናት 21 የግብፅን መንግስት ተቃዋሚዎችን አሳልፈው ሰጥተዋል።

➪አል አረቢያ ቻናል እንደዘገበው የሱዳን ባለስልጣናት ከ21 በላይ ግብፃውያንን ለካይሮ የደህንነት ቢሮ አሳልፈው ሰጥተዋል።
ባለፈው መጋቢት የሱዳን ባለስልጣናት አንድን ተቃዋሚ ለደህንነት ባለስልጣናት አሳልፈው የሰጡ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደብዛቸው ጠፍቷል።

# Ethio Fm
10.6K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ