የሰርጥ አድራሻ:
ምድቦች:
ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች:
29.46K
የሰርጥ መግለጫ
ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!
@abel21bot
Ratings & Reviews
Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.
5 stars
0
4 stars
0
3 stars
0
2 stars
0
1 stars
2
የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6
2022-07-12 14:24:34
#Iran Russia
ኢራን ሰው አልባ ድሮኖችን ለሩሲያ ለማቅረብ ማቀዷ ተነገረ
➪ሩሲያ ከኢራን የምትረከባቸው ድኖሮች በዩክሬይኑ ውጊያ ጥቅም ላይ እንደምታውላቸው የዋይት ሐውስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን መናገራቸውን ዘ ጋርዲያን ፅፏል፡፡ በዚህም ኢራን ለሩሲያ በመቶዎች የሚቆጠሩ አጥቂ ድሮኖችን ለማቅረብ ተሰናድታለች ተብሏል፡፡
➪ለኢራን ስሪቶቹን አጥቂ ድሮኖች የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በሳውዲ አረቢያ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እንደሚገለገሉባቸው ይነገራል። በሌላኛው ወገን ምዕራባዊያን እና አጋሮቻቸው ለዩክሬይን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እያጎረፉላት እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡
7.7K views11:24
2022-07-05 13:44:18
ሊሲቻንስክ ከተማ በሩሲያ ጦር መያዟን ዩክሬን አመነች
➪የሩሲያ ጦር ሊሲቻንስክ ጨምሮ ዶንባስ ክልልን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ከቀናት በፊት መናገሩ የሚታወስ ሲሆን የዩክሬን መከላከያም የሩሲያ ጦር በክልሉ የመጨረሻ ዩክሬን ይዞታ የነበረችውን ሊስቻንስክን ተቆጣጥሯል ብሏል፡፡
➪የዩክሬን ወታደሮች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ያለው የዩክሬን መከላከያ በቀጣይ በሩሲያ ጦር ስር የገቡ ቦታዎችን ሙሉ ለሙሉ ማስለቀቅ የሚያስችሉ ዘመቻዎችን እንጀምራለን ሲልም አስታውቋል።
17.1K views10:44
2022-07-03 19:30:15
#Monkeypox
(Africa)
➪የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት በአህጉሪቱ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን በመጠቆም እንደ #ድንገተኛ ሁናቴ እያስተናገዱት መሆኑን ገልፀዋል።
➪በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚታዩትን የፍትሃዊነት ችግሮች ለማስወገድ የበለፀጉ ሀገራት ውስን የክትባት አቅርቦቶችን እንዲያካፍሉም ጠይቀዋል።
➪እስካሁን ባለው በአፍሪካ 1,800 የሚጠጉ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠሩ ኬዞች ያሉ ሲሆን ከ70 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ተነግሯል ፤ ነገር ግን በላብራቶሪ ምርመራ የተረጋገጠው 109 ኬዝ ብቻ ነው ተብሏል።
➪ለበሽታው ምርመራ የሚያስፈልጉ የላብራቶሪ ምርመራ ገብአቶች እጦት እና ደካማ የሆነ የክትትል ስርዓት ብዙ ኬዞች ሳይታወቁ እንዲቀሩ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
16.3K views16:30
2022-07-01 10:35:13
15.2K views07:35
2022-06-30 11:31:23
ሱዳን ኢንተርኔት ዘጋች።
➪ሱዳን ዛሬ ሀሙስ ከሚካሄደው ታላቁ የ #June30 የተቃውሞ ሰለፍ ጋር በተያያዘ ከጥዋት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጣለች።
➪የኢንተርኔት ጉዳይን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ ፤ ዛሬ #June30 ሊካሄድ ከታሰበው የሱዳን ፀረ ጁንታ (ወታደራዊ አገዛዝ) ተቃውሞ እና የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ከሚጠይቀው ሰልፍ ጋር በተገናኘ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ገልጿል::
17.0K views08:31
2022-06-28 11:55:08
ፌስቡክና ዲዝኒን ሠራተኞቻቸው ፅንስ ማቋረጥ ከፈለጉ የጉዞ ወጪያቸውን እንደሚሸፍኑላቸው አስታወቁ
➭ዲዝኒ፣ ጄፒ ሞርጋን፣ ፌስቡክ (ሜታ) እና ሌሎችም ታዋቂ መሥሪያ ቤቶች
የተቀጣሪዎቻቸውን የጉዞ ወጪ ለመሸፈን ቃል ገብተዋል። የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፅንስ ማቋረጥ የሚፈቅደውን የሕገ መንግሥት አንቀጽ መሻሩ ይታወሳል።
➭ውሳኔውን ተከትሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ሴቶች የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ ፅንስ ማቋረጥን ሕገ ወጥ ያደረጉ የአሜሪካ ግዛቶች አሉ። በሌላ በኩል ፅንስ ማቋረጥ ሕጋዊ ሆኖ እንደሚቀጥል ያስታወቁ ግዛቶችም አሉ።
15.7K views08:55
2022-06-28 11:54:14
ስሪላንካ ባጋጠማት የነዳጅ ቀውስ የተነሳ ትምህርት ቤቶችን ዘጋች
➭የስሪላንካ ጦር በትላንት ዕለት ለነዳጅ የሚሰለፉ ሰዎች ብዛት በማስመልከት በዋና ከተማዋ ኮሎምቦ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ያደረገ ሲሆን የህዝብ አገልግሎት ሠራተኞች የነዳጅ ፍጆታቸውን ለማቃለል ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ጠይቋል ።
➭ አንዳንዶች ወደ ቤት እንኳን ለመድረስ ምንም ቤንዚን ስላልነበራቸው ለነዳጅ ሰልፍ ከ4 ቀናት በላይ ወረፋ ጠብቀዋል። ስሪላንካ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ቀውስ ያጋጠማት ሲሆን አይኤምኤፍ ለሀገሪቱ ሶስት ቢሊዮን ድጋፍ ለማድረግ እስከ ሃሙስ ድረስ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
RT News
12.8K views08:54
2022-06-27 13:17:43
12.9K views10:17
2022-06-26 16:35:59
የዩክሬይን ወታደሮች ከሴቬሮ ዳኔስክ ከተማ እንዲያፈገፍጉ መታዘዛቸው ተሰማ
➪የዩክሬይን ወታደሮች ውጊያ በርትቶባት ከሰነበተችው ሴቬሮ ዳኔስክ ከተማ እንዲያፈገፍጉ መታዘዛቸውን የሉሃንስክ ግዛት አስተዳዳሪ እንደተናገሩ ፍራንስ 24 ፅፏል፡፡
➪የሲሲቪሮ ዳንስክ መንትያ የሆነችው ሊሲቻንስም በሩሲያ ጦር ሙሉ ከበባ ውስጥ መግባቷ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
➪በአሁኑ ወቅት ዶንባስ ተብሎ የሚታወቀው የምስራቃዊ ዩክሬይን ክፍል በሩሲያ ጦር እጅ የሚገኝ ሲሆን የሩሲያ ጦር በከበባ ውስጥ ያስገባትን ሊሲቻንስንም ከተቆጣጠረ ሙሉ የሉሃንስክ ግዛትን በእጁ ያስገባ ያህል እንደሚቆጠር ታውቋል፡፡
14.3K views13:35
2022-06-25 13:13:34
13.4K views10:13