Get Mystery Box with random crypto!

Abel Birhanu የወይኗ ልጅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abe11 — Abel Birhanu የወይኗ ልጅ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abe11 — Abel Birhanu የወይኗ ልጅ
የሰርጥ አድራሻ: @abe11
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.46K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!
@abel21bot

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-08-03 12:15:37 የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ በእስያ ጉዟቸው ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ዩናይትድ ስቴትስ “ዋጋ ትከፍላለች” ስትል ቻይና ዛሬ አስጠንቅቃለች። ፔሎሲ በይፋ ወደ ታይዋን መጓዛቸውን ባያረጋግጡም የዩናይትድ ስቴትስ እና ታይዋን መገናኛ ብዙኃን ይህንን እየዘገቡ ይገኛሉ። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሀው ቹንይንግ ቤጂንግ ላይ ዛሬ በሰጡት መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት “የቻይናን ሉዓላዊ የፀጥታ ጥቅሞች ለማዳከም አሜሪካ ለምትወስደው ርምጃ ኃላፊነቱን ትወስዳለች» ብለዋል። ፔሎሲ በርግጥ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ከ 25 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎነኙ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ይሆናሉ። ቻይና ታይዋንን የራሷ አንድ አካል አድርጋ የምታይ ሲሆን ታይዋን ግን ራሷን እንደ ነፃ እና ዲሞክራሲያዊት ሀገር አድርጋ ታያለች። የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝትን በተመለከተ ዩናይትድ ስቴትስ ቤጂንግን ለማስቆጣት ሆን ብላ ያደረገችው ነው ስትል ሩሲያ ዛሬ ለቻይና ድጋፏን አሳይታለች። ፔሎሲ ዛሬ ማሌዢያ ኩዋላ ላምፑርን ጎብኝተው ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስማኢል ሳብሪ ጋር እንደተገናኙ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል። የታይዋን የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ናንሲ ፔሎሲ ዛሬ ማምሻውን ታይዋን ይገባሉ።

# DW Amharic
22.4K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 12:14:58 የአልቃይዳ መሪ አይማን አል ዛዋሂሪ አፍጋኒስታን ውስጥ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መገደሉን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሳካ ያሉት ይኽው ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ጠላቶች ሁሉ ግልጽ መልዕክት ነው ሲሉ ዋሽንግተን ውስጥ ተናግረዋል ። የሀገራቸው የስለላ ድርጅት ሲአይ ኤ የኦሳማ ቢን ላደን ተተኪ የተባለውን አል ዛዋሂሪ በያዝነው በጎርጎሮሳዊው 2022 ካቡል አፍጋኒስታን ውስጥ እንዳለ እንደተደረሰበት እና ከሳምንት በፊት፣ በአል-ዛዋሂሪ ላይ "ርምጃ" እንዲወሰድ መፍቀዳቸውን የተናገሩት ባይደን ጥቃቱ መድረሱን ማረጋገጣቸውንም ገልጸዋል። « ከቤተሰቦቹ መካከል አንዳቸውም አልተጎዱም። በሰላማዊ ሰዎች ላይም ምንም ጉዳት አልደረሰም። አሁን ይህን ዜና ለአሜሪካ ህዝብ የማካፍለው የተልእኮውን ስኬት ከፈጸሙ የፀረ ሽብር ማህበረሰብ እና ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ ቁልፍ አጋሮች ካረጋገጥኩ በኋላ ነው።»
ግብፅ ሀገር የተወለደው አል ዛዋሂሪ አይማን እጎአ መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ ም ኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ ከተፈፀመው የሽብር ጥቃት ጀርባ እጁ እንዳለ ይታመናል። እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ገልፃ ቢን ላደንን የተካው የአልቃይዳ መሪ የተገደለው እሁድ ጠዋትነው። 71 ዓመቱ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ በጥብቅ የምትፈልገውን ይህ ሰው ያለበትን ቦታ ለጠቆመ 25 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቃ ነበር።

# DW Amharic
17.0K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 12:41:45

17.5K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 15:27:33

17.4K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 16:33:29

17.0K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:17:38
የሲራላካ ወታራዊ ሀይል የተቃውሞ ካምፖችን ወሯል ..የተቃውሞ መሪዎችንም ማሰራቸው ተሰምቷል፡፡

➩ ተቃዋሚዎች አርብ ማለዳ ላይ ወታደሮች የዋና ከተማዋ ኮሎምቦ አከባቢዎችን ከተቁጣጠሩ በኃላ፣ በአንዳንዱች ላይ 'በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት ደርሶባቸዋል' ብለዋል።
➩ በስሪላንካ የሚገኘው ጦር በተቃዋሚዎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሆኔታ ድብደባን ከፈጸመ በኋላ በዋና ከተማው የሚገኘውን የፕሬዚዳንቱን ሴክሬታሪያት ተቆጣጥሯል።
በጎታጎጋማ የተቃውሞ ቦታ ላይ በወታደሮቹ በርካታ ድንኳኖች ወድመዋል፣ከ100 በላይ የተቃውሞ ሰልፈኞች ታስረዋል፤ በርካቱችም ተከበዋል ብሏል፤ የአልጀዚራ ዘገባ፡፡
የሲሪላንካው አዲሱ ፕሬዝዳንት ራኒል ዊክርሜሲንግህ በመላው አገሪቱ የሚጸና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር።

➩ ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተላልፈውታል። በወቅቱ ዊክርሜሲንግህ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉትን “ፋሺስቶች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

➩ ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ወታደራዊ ኃይሉ የሀገሪቱን ሰላም እና ጸጥታ እንዲያስጠብቅ መመሪያ ማሳለፋቸውን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

#Ethio Fm
22.5K views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 16:51:30
ኢትዮጵያ የግድቡን ሦስተኛ ዙር ሙሌት ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው አብዱል ፈታህ አልሲሲ ገለፁ

➩ በየሄዱበት ሀገር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በማንሳት የሚታወቁት የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በሳምንቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ሰርቢያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ባደረጉት ንግግር በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።

➩ ፕሬዝዳንቱ አክለውም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሶስቱ ሀገራት መካከል ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ የህግ ስምምነት መኖሩ የኢትዮጵያን የልማት እና የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን የግብፅን እና የሱዳንን የውሃ መብት ለማስጠበቅ ያስችላል ብለዋል።

➩ ህጋዊ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ሙሌት በማጠናቀቅ በያዝነው አመት መጀመሪያ የግድቡን ተርባይን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ጀምራለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሦስተኛውን ሙሌትም በመጭው ነሀሴ እና መስከረም ወር ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው መግለፃቸውን አልሃራም የተባለውን የግብፅ ጋዜጣ ጠቅስ ዶቼቨለ ዘግቧል።
16.1K views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 13:26:22
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሕከምና ወደ ውጪ ሀገር እንደሚሄዱ አስታወቁ

➩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአስቸጋሪ የጤና ሁኔታ መቆየታቸውን ጠቅሰው ለሕክምና ከሀገር ውጪ መጓዝ ማሰባቸውን በማስመልከት ዛሬ ከብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለኢኦተቤ ቴቪ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

➩ የዐይን ሕክምና ጨምሮ ሙሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው አስኪመለሱ አባቶችና ምእመናን በጸሎት ያስቡኝ ያሉት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ክብር አስጠብቀው ሥራቸውን በኃላፊነት እንዲያከናውኑ አደራ ብለዋል።
13.9K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 13:24:48
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኮቪድ 19 መያዛቸዉ ተነገረ፡፡

ነጩ ቤተመንግስት በትላንትናው እለት እንዳስታወቀዉ፣ባይደን በኮቪድ 19 መያዛቸዉ ተረጋግጧል::

ፕሬዝዳንቱ የኮቪድ 19 ክትባትን በተሟላ መልኩ መዉሰዳቸዉና ማጠናከሪያ/ቡስተር/ ወስደዉ እንደነበርም ተነግሯል፡፡

የ79 ዓመቱ ባይደን በአሁኑ ወቅት ደረቅ ሳል፣ድካምና ሌሎች የህመም ስሜቶች እንደሚታዩባቸዉም ሲ ኤን ቢሲ ዘግቧል፡፡

#Ethio Fm
12.4K views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 11:54:23
ቻይና አሜሪካ በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታቆም አሳሰበች::

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ዋሽንግተን በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅሰቃሴ እንድታቆም አሳስበዋል፡፡
አሜሪካ በህዋ ላይ ትጥቅ በመታጠቅ ላይ ነች ያሉት ቃል አቀባዩ፣ከድርጊቷ በመቆጠብ የህዋ ደህንነትን ማስጠበቅ አለባት ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ በህዋ ላይ የበላይነትን የማስፈን ስትራቴጅንና እንደ ዳይሬክት ኢነርጅ፤የተቆጣጣሪ ኮሙኒኬሽን ሲስተም በመዘርጋት ላይ እንደምትገኝም ተነግሯል፡፡
አገሪቱ አደገኛ የውጭ ጠፈር መሳሪያዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማዘጋጀትና በማሰማራት ላይ ትገኛለች ስትልም ቻይና ከሳለች፡፡
በተጨማሪም ዋሽንግተን በአለም አቀፍ ስትራቴጂካዊ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል በተባለዉ ጠፈር ላይ ስለላ ስለመጀመሯም ቤጂንግ ማስታወቋን ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡

#Ethio Fm
16.8K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ