Get Mystery Box with random crypto!

Aß Mustefa

የቴሌግራም ቻናል አርማ ab_mustefa — Aß Mustefa A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ab_mustefa — Aß Mustefa
የሰርጥ አድራሻ: @ab_mustefa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 854
የሰርጥ መግለጫ

ለማንም ስል ያልጀመርኩትን መንገድ ለማንም ስል አላቆምም ።
©ABDURAHIMAN
Amuwa Production😎

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2020-11-14 14:56:48 #ደስ_የሚል_ዜና
90 በመቶ ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ ከመያዝ ታድጓል የተባለው ክትባት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሁለት ኩባንያዎች ይፋ የተደረገው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት 90 በመቶ ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ ከመያዝ ታድጓል ተብሏል፡፡

ክትባቱን ይፋ ያደረጉት የአሜሪካው ፋይዘር እና የጀርመኑ ባዮንቴክ ሲሆን ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ አበርክቶ ነው ብለዋል፡፡

ኩባንያዎች ክትባቱን በስድስት የተለያዩ ሃገራት በ43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሃገራቱ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ቱርክ መሆናቸው ነው መረጃው የሚያመላክተው፡፡

በሙከራውም በሰዎች ላይ እስካሁን አሳሳቢ የጤና ችግር ያለመታየቱን ነው ባለሙያዎቹ ያነሱት፡፡

ኩባንያዎቹ ክትባቱን በህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡

በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን የአሁኑ ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካው ኩባንያ 50 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ እንደሚያቀርብ የገለፀ ሲሆን በ2021 ደግሞ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን እንደሚያመርት ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

@Ab_Mustefa
639 viewsAß Mustefa, 11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-10 16:08:32
ይህ ከታች የምታዩት የመስጂደል ሐረም በመካ የሚገኘው መስጂድና የአካባቢው ምስል ሲሆን ወጥ ከሆነ እንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ ነው ለቦታው ያለህ ፍቅር ሲጨምር ሲንር እንዲህ ለፈጠራ ያነሳሳኻል።
እንደምታዩት የእውነት ይመስላል ኢስላሚክ አርክቴክቸርና ዲዛይን ለዛሬው የስነ ህንፃ ዲዛይን ዕድገት ትልቁን ድርሻ አበርክቷል።

@Ab_Mustefa
806 viewsAß - Mustefa, 13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-26 07:53:11
864 viewsAß - Mustefa, edited  04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-24 06:47:49
ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር ነው!

ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር እንደሆነ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ትምህርቱ መሰጠት የጀመረበትን ይፋዊ የመክፈቻ ስነ ስርዓት የተመለከተ መረጃን በማህበራዊ ገጹ ያጋራው ኤምባሲው ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት እንደጀመረ ገልጿል፡፡

በስነ ስርዓቱ የኤምባሲው የሚኒስትር አማካሪ አቶ ሳሙዔል ፍጹም ብርሃን እና የዩኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጂያን ውንጂን ንግግር አድርገዋል፡፡

Via Al Ain News/Elias Meseret
@Ab_Mustefa
718 viewsAß - Mustefa, edited  03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-24 06:47:13
በስልክ ቁጥራችሁ ሊፈጸም ከሚችል ወንጀሎች ተጠንቀቁ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አሳሰበ!

በተጠናቀቀው የበጀት አመትም በ130 ሺህ የኩባንያው ደንበኞች የመስመር ስልክ ላይ የማጭበርበር ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ኢትዮቴሌኮም አስታውቋል፡፡

በተጠቀሰው የማጭበርበር ወንጀል የተነሳ ደንበኞች ለአንግልትና ለወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት እየተዳረጉ መሆኑን የጠቀሱት የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ኩባንያውም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጸዋል።

የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል መከላከል እንዲቻል ደንበኞች በተለያየ አጋጣሚ የሞባይል ስልካቸው በሚጠፋበት ወቅት በአቅሪያባቸው በሚገኙ የሽያጭ ማዕከላት በማሳወቅና የስልክ መስመራቸውን በማዘጋት ምትክ ሲም ካርድ መውስድ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ደንበኞች የስልክ መስመራቸውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ባለመስጠትና ለወንጀለኞች ተባባሪ ባለመሆን በስልክ መስመራቸው አማካኝነት ከሚፈጸም ወንጀል እንዲጠነቀቁ ማሳሰባቸውን አስታውቀዋል፡፡

@Ab_Mustefa
650 viewsAß - Mustefa, edited  03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-22 08:41:33
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ለ100 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ!

ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን 20 ሚለየን ብር በጀት የያዘለትንና በ7 ኢንድስትሪ ፓርኮች ውስጥ አንድ መቶ ሺ ወጣቶች የስራ እድል እንዲያገኙ እንዲሁም ሙሉ የመረጃ ሲስተም ለመዘርጋት የሚያስችለውን ስምምነት ከኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በትላንትናው ዕለት ተፈራርሟል፡፡

በፕሮጀክቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች 100 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ያሉ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ያሉትን የስራ እድሎች፣ ጥቅሞቹን፣ ለስራው ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ምን እንደሆነና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያገኙበት ሲስተም በመዘርጋት የመረጃ ችግሩን ለመቅረፍ ያስችላል ተብሏል፡፡

ፋውንዴሽኑ ድጋፍ የሚደርግባቸው ኢንድስትሪ ፓርኮችም በአዳማ፣ ድሬደዋ ፣ባህርዳር፣ ደብረ ብርሀን፣ሀዋሳ፣ መቀሌ እና ኮምቦልቻ የሚገኙት ሲሆኑ በቀጣይ 3 ኢንድስትሪ ፓርኮች ላይም ድጋፍ እንደሚደርግ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

@Ab_Mustefa
685 viewsAß - Mustefa, edited  05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-08-21 07:31:14 Channel name was changed to «Aß Mustefa»
04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-08-06 07:27:03 አንዲት አንገቷ ላይ መስቀል ያረገች ሴት ታላቁን የአላህን የተከበረውን ቁርዓን ስትረግጥ እና ስትገነጣጥል ሁሉም ይሳደብና ያልፋታል።አንዱ ግን በብሄሩ ምክንያት ሲገደል አክራሪ ሙስሊም ገደለው ተብሎ ታርጋ ይለጠፋል።
አርሲ ላይ ከ100 65% ሻሸመኔ ላይ ደሞ ከ100 58% ንብረት የወደመው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ነው ማሀበረቅዱሳኑ ግን ክርስቲያኖችን ለይቶ ለማጥቃት ሙስሊሞች ነው ጥቃቱን ያደረሱት ብሎ ፕሮፖጋንዳ ይሰራልሃል።
በሞጣው የሽብር ጥቃት ላይ ያ ሁሉ ንብረት ሲወድም ጥቃቱ እንዲፈፀምም በሚዲያ ሲያነሳሱ የነበሩት ሰዎች ምን ተባሉ?!
እሱስ ይሁን መስጊዱን አቃጥለው የቤተክርስቲያን መዝሙር ሲዘምሩ የነበሩትስ አክራሪ ክርስቲያኖች ማን አላቸው?!።
ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ውጪ ያለው ሲጎዳ በአክራሪ ሙስሊሞች ተጎዳ ይሉሃል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሲገደልና ንብረት ሲወድምበት ግን
አንድም ሚዲያ አክራሪ ክርስቲያን አይልም! እዚጋ ክላሽ አላረገም

አንተን በደበረህ ቁጥር እስልምናዬን ላንተ ፖለቲካ ማራመጃ ልታረገው አትችልም።
ዛሬም ነገም ከከነጎዲያም እስልምናዬን በማንም የፖለቲካ ዲስኩር ልታጠለሸው አትችልም።
እኔ ስወለድ እማቀው ኢትዮጲያዊ ሙስሊም መሆኔን ነው። ኢትዮጲያዊ ሙስሊም ሆኜ ነው መኖርም መሞትም ምፈልገው። ያንተን የተግማማውን ፖለቲካ እዛው

ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa
2.0K viewsAß - Mustefa, 04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-25 11:35:17 በነቢዩ (ዐሰወ) ዘመን አንዲት በጌጣጌጥ የተሸለመች ሴት በመንገድ ስትሄድ አይሁዳዊ ያገኛትና ለወርቋ ሲል ጭንቅላቷን በድንጋይ መትቶ ገደላት። ነቢዩም (ዐሰወ) የሴቲቱ ነፍስ ልትወጣ ስትቃረብ ደረሱባትና ማን እንደመታት ይጠይቋት ጀመር። «እገሌ ነው?» አሏት። «አይደለም» በማለት በምልክት ነገረቻቸው። ሌላም ሰው ጠሩ። «አይደለም» አለች። በመጨረሻ የአይሁዳዊውን ስም ጠሩላት። «አወ!» አለቻቸው። ከዚያም ነፍሷ ወጣች።

ነቢዩም (ዐሰወ) አይሁዳዊውን አስመጥተው ጥያቄዎችን ጠየቁት። እሱም ወንጀሉን መፈፀሙን ተናዘዘ። ከዚያም ሴቲቱን በገደላት መልኩ እንዲገደል አዘዙ። በድንጋይ ተወግሮም ተገደለ።
(አንነሳዒ 4742)

የሴቶች መብት ነቢዩ (ዐሰወ) ከሄዱበት መንገድ ውጭ ሊከበር አይችልም።

@Ab_Mustefa
1.4K viewsAß - Mustefa, 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-21 09:14:29 ሰላተል ኩሱፍ ( የፀሀይ ግርዶሽ ሰላት )

ፀሀይ በጨረቃ ግርዶሽነት ምክንያት ብርሀኗ ከመሬት ሲጋረድ የሚሰገደው ሱና የሆነው ሰላት (ሰላት ኩሱፍ) (صلاة الكسوف) ይባላል ። ጨረቃ ደሞ በመሬት አማካኝነት ስትጋረድ የሚሰገደው ሰላት (ሰላተል ኹሱፍ) (صلاة الخسوف ) ይባላል።

የፀሀይ ኩሱፍ ሰላት በሸሪዐ የተደነገገው በሁለተኛው አመተ ሂጅራ ሲሆን ፤ የጨረቃ ኹሱፍ ሰላት ደሞ በአምስተኛው አመተ ሂጅራ ነው። (ሁለቱም ሰላቶች ሱና ናቸው ለወንድም ለሴትም ። በጀመዐ መስገዱ የተወደደ ቢሆንም ለብቻም መስገድ ይቻላል። )

አሰጋገዱ
ሁለት አይነት አሰጋገድ አለው

አንደኛው - ሁለት ረክዐ እንደማንኛው ረክዐተይን ሰላት ። ኡሰሊ ሱነተ ሰላተል ኩሱፍ ብሎ መስገድ ይቻላል።

ሁለተኛው - በሁለት ቂያምና በሁለት ሩኩዕ ይሰገዳል ።
- ነይቶ በተክቢር ወደ ሰላት ይገባል። መክፈቻ ዱዐውን ይላል
- ፋቲሀና ሱራ ይቀራል ( ረጅም ሱራ ቢሆን ይመረጣል )
- ሩኩዕ ይወርዳል
- ከሩኩዕ ይነሳል፤ ረበና ለከል ሀምድ ብሎ ዱዐውን ይላል
- ከዛ ድጋሚ ፋቲሀና ሱራ ይቀራል ( ከመጀመርያው ሱራ አነስ ያለ ቢሆን ይመረጣል )
- ሩኩዕ ይወርዳል
- ከሩኩዕ ይነሳል
- ረበና ለከል ሀምድ ብሎ የኢዕቲዳል ዱዐ ይላል
- ሱጁድ ይወርዳል ፤ ይነሳል፤ ሁለተኛ ሱጁድ ያደርጋል
- ከዛ ተነስቶ ሁለተኛውንም ረክዐ በእንደዚህ አይነት ይጨርሳል።

በሁለተኛው አሰጋገድ ላይ አምልጦት የመጣ ረክዐዋን ለማግኘት የመጀመርያዋን ሩኩዕ ማግኘት አለበት ። ከአንዱ ረክዐ የመጀመርያው ሩኩዕ ያመለጠው ረክዐው አምልጦታል።

ከሰላት ቡሀላ እንደ ጁምዐ አይነት ሁለት ኹጥባ ማድረግ ይወደዳል።

የሰላቱ ግዜ የሚወጣው .. የፀሀዩ ግርዶሽ ሙሉ በሙሉ ሲወገድ ወይም ደሞ ምሽት ደርሶ ፀሀይዋ ስትጠልቅ ነው
የጨረቃውም ግርዶሹ ሙሉ ለሙሉ ከተወገደ ወይም ደሞ ነግቶ ፀሀይ ከወጣች ጊዜው ይወጣል።

ሰይዳችን ሰ.ዐ.ወ. ከስር የተጠቀሰው ሀዲሳቸው ላይ : '' ፀሀይና ጨረቃ ሁለቱ ከአላህ ተዐምራቶች ውስጥ ናቸው። ለማንም መሞት ወይም መኖር አይደለም የሚጋረዱት። ይሀንን ካያቹ ወደ ሰላት ሽሹ '' ብለዋል።

عن عائشة زوج النبي صلى الله عليه وسلم قالت : خسفت الشمس في حياة رسول الله صلى الله عليه وسلم فخرج رسول الله صلى الله عليه وسلم إلى المسجد فقام وكبر وصف الناس وراءه فاقترأ رسول الله صلى الله عليه وسلم قراءة طويلة ثم كبر فركع ركوعا طويلا ثم رفع رأسه فقال سمع الله لمن حمده ربنا ولك الحمد ثم قام فاقترأ قراءة طويلة هي أدنى من القراءة الأولى ثم كبر فركع ركوعا طويلا هو أدنى من الركوع الأول ثم قال سمع الله لمن حمده ربنا ولك الحمد ثم سجد ثم فعل في الركعة الأخرى مثل ذلك حتى استكمل أربع ركعات وأربع سجدات وانجلت الشمس قبل أن ينصرف ثم قام فخطب الناس فأثنى على الله بما هو أهله ثم قال إن الشمس والقمر آيتان من آيات الله لا يخسفان لموت أحد ولا لحياته فإذا رأيتموها فافزعوا للصلاة }

رواه مسلم

@elmeewa
@Ab_Mustefa
1.4K viewsAß - Mustefa, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ