Get Mystery Box with random crypto!

ዩአንገሊዎን

የቴሌግራም ቻናል አርማ yoangeliwon — ዩአንገሊዎን
የቴሌግራም ቻናል አርማ yoangeliwon — ዩአንገሊዎን
የሰርጥ አድራሻ: @yoangeliwon
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

,እንኳን ደና መጡ ! ይህ የዩአንገሊዎን ቻናል የክርስቶስን ወንጌልና ዳግም ምጽአት እያስተማረ ወንጌል እየሰበከ ለእግዚአብሔር መንግስት ትውልድን የማብቃት ዓላማን ሰንቆ የያዘ በመሆኑ ወቅታቸውን በጠበቁ መልክትች በማስታጠቅ ለእግዝአብሔር ስራ የተዘጋጀ ቻናል ነው።
ዩአንገሊዎን አቤኔዘር ዳዊት

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-15 21:30:21 ክፍል አራት
ደስታ የሚያስገኘው መልካም ውጤት
አምላካዊ ባሕርይ የሆነው ደስታ፣ በውስጣችን ከሚሰማን ስሜት ባለፈ ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል። ለምሳሌ ያህል፣ ምንም ዓይነት ችግሮች ቢያጋጥሙን ሰማያዊ አባታችንን በደስታ ማገልገላችን እሱን ይበልጥ ያስደስተዋል። (ዘዳ. 16:15፤ 1 ተሰ. 5:16-18) ከዚህም ባሻገር እውነተኛ ደስታ ሲኖረን፣ ቁሳዊ ሀብት በማሳደድ ላይ ያተኮረ ሕይወት ከመምራት ይልቅ የአምላክን መንግሥት ለማስቀደም ስንል ብዙ መሥዋዕት እንከፍላለን። (ማቴ. 13:44) ይህን ማድረጋችን የሚያስገኘውን ጥሩ ውጤት ስንመለከት ደግሞ ደስታችን የሚጨምር ከመሆኑም ሌላ ለራሳችን ጥሩ አመለካከት ይኖረናል፤ ሌሎች ይበልጥ እንዲደሰቱም እናደርጋለን።—ሥራ 20:35፤ ፊልጵ. 1:3-5
“አሁን በሕይወትህ ደስታና እርካታ ካለህ ወደፊት ጤነኛ የመሆን አጋጣሚህ ሰፊ ነው።” ይህም “ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው” ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ጋር ይስማማል። (ምሳሌ 17:22) በእርግጥም ይበልጥ ደስተኛ ስትሆን የተሻለ አካላዊ ጤንነት ይኖርሃል።
የምንኖረው አስጨናቂ በሆነ ዘመን ውስጥ ቢሆንም በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እውነተኛና ዘላቂ ደስታ ማግኘት እንችላለን፤ መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት ደግሞ መጸለያችን፣ ማጥናታችንና በይሖዋ ቃል ላይ ማሰላሰላችን አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም አሁን ባገኘናቸው በረከቶች ላይ ማተኮራችን፣ ሌሎችን በእምነታቸው መምሰላችን እንዲሁም የአምላክን ፈቃድ ለመፈጸም ጥረት ማድረጋችን ይበልጥ ደስተኞች ለመሆን ይረዳናል። ይህም በመዝሙር 64:10 ላይ የሚገኘውን “ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል፤ ልባቸውም የቀና ሁሉ እልል ይላሉ።” — መዝሙር 64፥10” የሚለውን ሐሳብ እውነተኝነት በሕይወታችን ለማየት ያስችለናል።
ይበልጥ ደስተኛ ለመሆን የሚረዱ መንገዶች
1.ኑሮህ ቀላል እንዲሆን አድርግ ያለህ እንደሚበቃም ተማር ።—ሉቃስ 13:15-34
2.ሕይወትን በጥበብ እና በጥንቃቃ መምራትን መከተል ኤፌ. 5:15, 16
3.ከራስህም ሆነ ከሌሎች በምትጠብቀው ነገር ምክንያታዊ ሁን።—ፊልጵ. 4:5
https://t.me/Yoangeliwon
226 viewsedited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 21:30:21 ክፍል ሶስት
ለደስታችን ምክንያት የሆኑ ነገሮች
ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ዝምድና የበለጠ ለደስታችን ምክንያት የሚሆን ምን ሊኖር ይችላል? እስቲ አስበው፦ የአጽናፈ ዓለሙን ሉዓላዊ ጌታ እናውቃለን። እሱ አባታችን፣ አምላካችንና ወዳጃችን ነው!—መዝ. 71:17, 18
ሕይወታችን እግዚአብሔር ያገኘነው ስጦታ ነው፤ በተጨማሪም እግዚአብሔር በሕይወታችን መደሰት እንድንችል አድርጎ ፈጥሮናል። (መክ. 3:12, 13) እግዚአብሔር ወደ ራሱ ስለሳበን አምላክ ለእኛ ያለውን ፈቃድ አውቀናል፤ እንዲሁም ሕይወታችንን እንዴት መምራት እንዳለብን ተገንዝበናል። (ቆላ. 1:9, 10) በመሆኑም ሕይወታችን እውነተኛ ትርጉም ያለው መሆን ችሏል። በሌላ በኩል ግን አብዛኛው የሰው ዘር ስለ ሕይወት ዓላማ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ የለውም። ጳውሎስ ይህን ልዩነት ጎላ አድርጎ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “‘አምላክ ለሚወዱት ያዘጋጃቸውን ነገሮች ዓይን አላየም፣ ጆሮም አልሰማም፣ የሰውም ልብ አላሰበም።’ . . . አምላክ እነዚህን ነገሮች በመንፈሱ አማካኝነት የገለጠው ለእኛ ነውና።” (1 ቆሮ. 2:9, 10) በእርግጥም የእግዚአብሔርን ፈቃድና ዓላማ ማወቃችን የሚያስደስት አይደለም?
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያደረገውን ሌላም ነገር እንመልከት። ኃጢአታችን ይቅር ሊባልልን በመቻሉ ደስተኞች አይደለንም? (1 ዮሐ. 2:12) አምላክ መሐሪ በመሆኑ በቅርቡ አዲስ ዓለም እንደሚመጣ እርግጠኛ የሆነ ተስፋ ሊኖረን ችሏል። (ሮም 12:12) በአሁኑ ጊዜም እንኳ እግዚአብሔር ፣ ጥሩ የእምነት አጋሮች ሰጥቶናል። (መዝ. 133:1) ከዚህም ሌላ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከሰይጣንና ከአጋንንቱ እንደሚጠብቅ ሕያው ቃል ዋስትና ይሰጠናል። (መዝ. 91:11) ከአግዚአብሔር ባገኘናቸው በእነዚህ ሁሉ በረከቶች ላይ የምናሰላስል ከሆነ ደስታችን እየጨመረ ይሄዳል።—ፊልጵ. 4:4
ይበልጥ ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ ትችላለህ?
በሕይወቱ ደስተኛ የሆነ ክርስቲያን የበለጠ ደስታ ማግኘት ይችላል? ኢየሱስ “እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ እኔ ያገኘሁትን ደስታ እንድታገኙና የእናንተም ደስታ የተሟላ እንዲሆን ነው” ብሏል። (ዮሐ. 15:11) ይህ አባባል ደስታችን እንዲጨምር ማድረግ እንደምንችል የሚጠቁም አይደለም? ደስታችን እንዲጨምር ማድረግ፣ እሳትን ይበልጥ ለማቀጣጠል ማገዶ ከመጨመር ጋር ሊመሳሰል ይችላል። እሳቱ ይበልጥ እንዲቀጣጠል እንጨት መማገድ አለብህ። በተመሳሳይም ደስታህ እንዲጨምር መንፈሳዊነትህን ማሳደግ አለብህ። መንፈስ ቅዱስ፣ ደስታ ለማግኘት እንደሚረዳ አስታውስ። በመሆኑም የእግዚአብሔርን መንፈስ እርዳታ ለማግኘት አዘውትረህ በመጸለይና በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃሉ ላይ በማሰላሰል ደስታህ እንዲጨምር ማድረግ ትችላለህ።—መዝ. 1:1, 2፤ ሉቃስ 11:13
ከዚህም ሌላ እግዚአብሔርን በሚያስደስቱ ሥራዎች በትጋት በመካፈል ደስታህ እንዲጨምር ማድረግ ትችላለህ። (መዝ. 35:27፤ 112:1) እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም የተፈጠርነው ‘እውነተኛውን አምላክ እንድንፈራና ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ’ ነው፤ “ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነው።” (መክ. 12:13) በሌላ አባባል የተፈጠርነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናደርግ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ስናገለግል በሕይወታችን ከሁሉ የላቀ ደስታ እንደምናገኝ የተረጋገጠ ነው።
https://t.me/Yoangeliwon
181 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 21:29:11 ክፍል ሁለት
በተስፋ እና በታማኝነት ውስጥ ያለህ ደስታ
# አንድ ሰው፣ የሚረብሽ ነገር ቢያጋጥመውም እንኳ ልቡ በደስታ ሊሞላ ይችላል። ደግሞም ይሞላል ለምሳሌ ያህል፣ ሐዋርያቱ ስለ ክርስቶስ በመናገራቸው ምክንያት ተገርፈው ነበር። ሆኖም ከሳንሄድሪን ሸንጎ ሲወጡ “ስለ ስሙ ውርደት ለመቀበል ብቁ ሆነው በመቆጠራቸው ደስ እያላቸው” ነበር። (ሥራ 5:41) ሐዋርያቱ ደስ ያላቸው ስለተገረፉ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ይሁንና የእግዚአብሔር አምላክ አገልጋዮች እንደመሆናቸው መጠን ለእርሱ ያላቸውን ታማኝነት በመጠበቃቸው እውነተኛ ደስታ አግኝተዋል።
#እንዲህ ያለው ደስታ ስንወለድ ጀምሮ የሚኖረን አሊያም ያለምንም ጥረት የምናገኘው ነገር አይደለም። ለምን? ምክንያቱም እውነተኛ ደስታ ከመንፈስ ፍሬ ገጽታዎች አንዱ ነው። በእግዚአብሔር አምላክ በቅዱስ መንፈስ እርዳታ “አዲሱን ስብዕና” በተሟላ ሁኔታ መልበስ የምንችል ሲሆን ይህም ደስታን በሙሉነት ያካትታል። ደግሞም በእውነተኛው ደስታ እንሞላለን ። “ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።”ኤፌሶን 4፥24 . “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።” ገላትያ 5፥22 #በአጠቃላይ ደስታ ሲኖረን ደግሞ የሕይወትን ውጣ ውረዶች በተሻለ ሁኔታ በታማኝነት መቋቋም እንችላለን። አሜን
ለመሆኑ ደስታን እንዴት አድርገን ነው የምናስባት? ማንን ነው የምትመስለው? ፈንጠዚያ ደስታ ናት? ያለማቋረጥ በሳቅ መንከትከት ደስተኝነት ነው? በምቾት መንገላታትስ? ምንድናት ደስታ? እንዴት ነው የደስታን ጅራቷን መያዝ የሚቻለው?
እኛ ነገሮች እንደጠበቅነው በማይሆኑበት ጊዜ ከልክ በላይ ባለመጨነቅ በታማኝነት ይሖዋን መምሰል እንችላለን። ደስታችንን ከማጣት ይልቅ አሁን ባሉን ጥሩ ነገሮች ላይ ማተኮርና ወደፊት የምናገኛቸውን የተሻሉ ነገሮች በትዕግሥት መጠበቅ ተስፋችን በታማኝነት ከደስታ ጋር መያዝ እንችላለን።
ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም ደስታቸውን ሳያጡ በታማኝነት የተሰጣቸውን ተስፋ አጽንተው በመያዝ መኖር የቻሉ በርካታ ምሳሌዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። አብርሃም የደረሱበትን ለሕይወት አስጊ የሆኑ ሁኔታዎችና ችግሮች በጽናት እና በታማኝነት ተቋቁሟል። (ዘፍ. 12:10-20፤ 14:8-16፤ 16:4, 5፤ 20:1-18፤ 21:8, 9) አብርሃም፣ ሌሎች ሰዎች እንደዚህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢፈጥሩበትም ደስታውን ጠብቆ መኖር ችሏል። ይህን ማድረግ የቻለው እንዴት ነው? በመሲሑ አገዛዝ ሥር በአዲሱ ዓለም ውስጥ የመኖር ተስፋው በአእምሮው ውስጥ ብሩህ ሆኖ ይታየው ስለነበረ ነው። (ዘፍ. 22:15-18፤ ዕብ. 11:10) ኢየሱስ “አባታችሁ አብርሃም ቀኔን እንደሚያይ ተስፋ በማድረግ እጅግ ተደሰተ” በማለት ተናግሮ ነበር። (ዮሐ. 8:56) እኛም ወደፊት በምናገኘው ደስታ ላይ በማሰላሰል አብርሃምን ልንመስለው እንችላለን።—“ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው።”ሮሜ 8፥21
እንደ አብርሃም ሁሉ ሐዋርያው ጳውሎስና ጓደኛው ሲላስም አምላክ በሰጣቸው ተስፋዎች ላይ ያሰላስሉ ነበር። ጠንካራ እምነት የነበራቸው ሲሆን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም እንኳ የተጠሩበትን የሕይወት ዓላማ በታማኝነት በመያዝ ደስታቸውን ሳያጡ መኖር ችለዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበው ወደ ወህኒ ከተጣሉ በኋላ “እኩለ ሌሊት ገደማ . . . እየጸለዩና አምላክን በመዝሙር እያወደሱ” እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ሥራ 16:23-25) ጳውሎስና ሲላስ ብርታት እንዲያገኙ የረዳቸው አንዱ ነገር ተስፋቸው ነው፤ ከዚህም በተጨማሪ መከራ የደረሰባቸው በክርስቶስ ስም የተነሳ መሆኑ ደስተኞች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። እኛም አምላክን በታማኝነት ማገልገል ደስታን እንድሆን የሚያስገኘውን መልካም ውጤት ማስታወሳችን የጳውሎስንና የሲላስን ምሳሌ ለመከተል ያስችለናል።—ፊልጵ. 1:12-14 https://t.me/Yoangeliwon
177 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 22:39:22 ክፍል አንድ
ደስታ

ደስታ ምንድን ነው?

#ደስታ አንድ ሰው በግል ሕይወቱ በየቀኑ በሚሰማው የአእምሮ ደህንነት መካከል ባለው እርካታ መካከል ሊተረጎም ይችላል ፡፡ደስተኛ መሆን ማለት በደስታ እስከ ደስታ ድረስ በአዎንታዊ ስሜቶች በተዋቀረ በጥሩ ስሜት ውስጥ መሆን ማለት ነው ፡፡

#ደስታን ለመግለጽ ሞክረው ያውቃሉ ወይም በመዝገበ ቃላቱ ውስጥ ትርጓሜውን ተመልክተዋል? መልሱ አዎ ከሆነ ፣ ለተመሳሳይ ቃል ተመሳሳይነት የማያካትት የዚህ ፅንሰ-ሀሳብ ፍቺ ማግኘት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አስተውለው ይሆናል ፡፡ ያ በቂ እንዳልሆነ ፣ አንድ ሰው የሚሰማውን የደስታ መጠን በትክክል መለካት ለእኛም ፈጽሞ የማይቻል ነው።በአሁኑ ጊዜ እና ከዘመናዊው ዓለም ልማት ጋር ባለው ከፍተኛ የደስታ መጠን የተነሳ ደስታን የሚያጠና ሳይንስ ትልቅ ጠቀሜታ አግኝቷል ምክንያቱም ደስተኛ መሆን የማይፈልግ ሰው ማን ነው? በጣም አስደሳች ከሆኑት ትርጓሜዎች መካከል ጠቢባኖች እንዲህ ብለዋል -

ጥበብ ትልቁ የደስታ ክፍል ነው - - Sophocles.
ሁል ጊዜ ደስተኛ መሆን የሚችለው በሁሉም ነገር እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችል የሚያውቅ ብቻ ነው--ኮንፊሺየስ።-
ደስታ ነፃነትን ፣ ማለትም ማንኛውንም ነገር አለመፈለግን ያጠቃልላል። - ኤፒፔቲተስ።-
ደስታ የሚለው ቃል በሀዘን ሚዛናዊ ካልሆነ ትርጉሙን ያጣል - - ካርል ጁንግ
ዳክዬ ባሕሩን ስለማያውቅ በቆሸሸው ገንዳ ውስጥ ደስተኛ ነው - - አንቲን ደ ሴንት-ኤክስፒሪ።
ደስታ በእኛ ላይ የተመካ ነው-አሪስቶትል።
እውነተኛ ደስታ ለወደፊቱ ላይ ያለ ጭንቀት ጥገኛ ሆኖ የአሁኑን መደሰት ነው - ማርኮ ኦሬሊዮ
ብዙ ሰዎች እራሳቸውን ለመሆን እንደወሰኑ ደስተኞች ናቸው - - አብርሃም ሊንከን።
ገንዘብ ሰውን በጭራሽ አያስደስተውም ፣ ወይም አያስደስትም ፣ በተፈጥሮው ውስጥ ደስታን የሚያመጣ ምንም ነገር የለም። የበለጠ ባላችሁ ቁጥር የበለጠ ይፈልጋሉ ፡፡ - ቤንጃሚን ፍራንክሊን ፡፡

እኔ ግን ትንሹ አቤኑ እላለሁ ደስተኛ መሆን፣ ተጫዋች ወይም ፍልቅልቅ መሆንን ብቻ እንደሚያመለክት አድርገን ልናስብ አይገባም። ሁኔታውን በምሳሌ ለማስረዳት ልሞክር ፦ ሰካራም የሆነ ሰው ብዙ ሲጠጣ ሳቅ ሳቅ ሊለው ይችላል። ስካሩ ሲበርድለት ግን መሳቁን አይቀጥልም፤ ምክንያቱም በሐዘንና በችግር ከተሞላው ሕይወቱ ማምለጥ አይችልም። ይህ ሰው ለጊዜው ቢፈነድቅም እውነተኛ ደስታ ነበረው ማለት አይቻልም።ምሳሌ 14¹² ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።¹³ በሳቅ ደግሞ ልብ ያዝናል፥ የደስታም ፍጻሜ ልቅሶ ነው።

#ስለዚህ #ደስታ ከልብ የመነጨ ጥልቅ ስሜት ነው። ደስታ “ጥሩ ነገር ከማግኘት ወይም አገኛለሁ ብሎ ከማሰብ የሚመጣ ስሜት” ነው ። # ደስተኛ መሆን ሲባል በሕይወታችን ውስጥ ጥሩም ሆኑ መጥፎ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙን ደስታችንን ሳናጣ መቀጠል ማለት ነው። “ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤”1ኛ ተሰሎንቄ 1፥6 # ስለዚህ የደስታን ጅራት የጨበጠ እጁን ያውጣ እንደሚለው የሀገሬ አባባል ለብዙዎች ደስታ የምርጫ ጉዳይ ነው። በእዚህ ምክንያት ደስተኛነት የጥረት ፍሬ ናት። ደስተኛ ለመሆን የፈለገ ልክ በፈተና እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚታትር ተማሪ ቀን ተሌት መልፋት መድከም አለበት። ምክንያቱም በብዙ መከራ ውስጥ ስንጸና ስናልፍ ስንጓዝ ነው መንፈስ ቅዱስም ገና ሊገለጥ ያለሁን ክብር ከአሁኑ ከገጠመን ከጨበጭነው ካለንበት ከሕይወት ምልልስ ጋር በማነጻጸር ነገን ይበልጥ ማለትም አዲሱን የሚገለጠውን ክብር በብዙ እየናፈቅን በብዙ ደስታ የሚያበረታታን አሜን
ይቀጥላል
አገልጋይ አቤነዘር ዳዊት
https://t.me/Yoangeliwon
234 viewsedited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 12:15:28
171 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 06:11:16 በፋሲካ .............
በፋሲካው እኛን ከእርሱ እኛን በእርሱ እኛን ለእርሱ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ከአብ ጋር አስታርቆ የጥልን ግርግዳ በሥጋው አፍርሶ የድነታችን ቤዛነት በመስቀል ላይ በመሞት ፈፅሞ ዘላለማችንን አሳመረው ወደ አብ መሄጃ (መድረሻ) እውነተኛ መንገድ ሆኖ ኢየሱስ ተነስቶል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለዓመፀኞች ማልዶ።

ወዳጆቼ በየአመቱ የምንሰቅለው ኢየሱስ የለንም ትንሳኤውን ስናስብ እግዚአብሔር አብ ለእኛ ያሳየን ፍቅር እግዚአብሔር ወልድ የታገሰለን የትግስትን ጥግ መረዳት እድንችል እመኛለሁ ለዚህም ነው ቃሉ እንዲህ የሚለን “ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።” የሚለን 2ኛ ተሰሎንቄ 3፥5

ስለዚህ ወዳጆቼ መልካም የትንሳኤ መታሰብያ ቀን እንዲሆንላችሁ በእዚህም ቀን ይህን እንድታስብ “የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። “እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤” የእግዚአብሔርን አብ ፍቅር እና የእግዚአብሔርን ወልድን (የክርስቶስን) መስዋዕትነት እንድታስብ ብርቱ ምኞቴ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 5፥7 1ኛ ዮሐንስ 3፥1
መልካም የትንሳኤ መታሰቢያ ቀን ይሁንላችሁ

አገልጋይ አቤነዘር ዳዊት
ቀን 16/8/2814 ዓ/ም


https://t.me/Yoangeliwon
234 viewsedited  03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 04:02:59 Watch "በፍፁም ልብ መከተል | Halwot Emmanuel United Church | Prophet Zenebe Girma" on YouTube




https://t.me/Yoangeliwon
234 viewsedited  01:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 03:56:58 Watch "Way Maker - Darlene Zschech & William McDowell | REVERE (Official Live Video)" on YouTube



https://t.me/Yoangeliwon
214 viewsedited  00:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ