Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል አራት ደስታ የሚያስገኘው መልካም ውጤት አምላካዊ ባሕርይ የሆነው ደስታ፣ በውስጣችን ከሚሰማ | ዩአንገሊዎን

ክፍል አራት
ደስታ የሚያስገኘው መልካም ውጤት
አምላካዊ ባሕርይ የሆነው ደስታ፣ በውስጣችን ከሚሰማን ስሜት ባለፈ ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል። ለምሳሌ ያህል፣ ምንም ዓይነት ችግሮች ቢያጋጥሙን ሰማያዊ አባታችንን በደስታ ማገልገላችን እሱን ይበልጥ ያስደስተዋል። (ዘዳ. 16:15፤ 1 ተሰ. 5:16-18) ከዚህም ባሻገር እውነተኛ ደስታ ሲኖረን፣ ቁሳዊ ሀብት በማሳደድ ላይ ያተኮረ ሕይወት ከመምራት ይልቅ የአምላክን መንግሥት ለማስቀደም ስንል ብዙ መሥዋዕት እንከፍላለን። (ማቴ. 13:44) ይህን ማድረጋችን የሚያስገኘውን ጥሩ ውጤት ስንመለከት ደግሞ ደስታችን የሚጨምር ከመሆኑም ሌላ ለራሳችን ጥሩ አመለካከት ይኖረናል፤ ሌሎች ይበልጥ እንዲደሰቱም እናደርጋለን።—ሥራ 20:35፤ ፊልጵ. 1:3-5
“አሁን በሕይወትህ ደስታና እርካታ ካለህ ወደፊት ጤነኛ የመሆን አጋጣሚህ ሰፊ ነው።” ይህም “ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው” ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ጋር ይስማማል። (ምሳሌ 17:22) በእርግጥም ይበልጥ ደስተኛ ስትሆን የተሻለ አካላዊ ጤንነት ይኖርሃል።
የምንኖረው አስጨናቂ በሆነ ዘመን ውስጥ ቢሆንም በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እውነተኛና ዘላቂ ደስታ ማግኘት እንችላለን፤ መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት ደግሞ መጸለያችን፣ ማጥናታችንና በይሖዋ ቃል ላይ ማሰላሰላችን አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም አሁን ባገኘናቸው በረከቶች ላይ ማተኮራችን፣ ሌሎችን በእምነታቸው መምሰላችን እንዲሁም የአምላክን ፈቃድ ለመፈጸም ጥረት ማድረጋችን ይበልጥ ደስተኞች ለመሆን ይረዳናል። ይህም በመዝሙር 64:10 ላይ የሚገኘውን “ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል፤ ልባቸውም የቀና ሁሉ እልል ይላሉ።” — መዝሙር 64፥10” የሚለውን ሐሳብ እውነተኝነት በሕይወታችን ለማየት ያስችለናል።
ይበልጥ ደስተኛ ለመሆን የሚረዱ መንገዶች
1.ኑሮህ ቀላል እንዲሆን አድርግ ያለህ እንደሚበቃም ተማር ።—ሉቃስ 13:15-34
2.ሕይወትን በጥበብ እና በጥንቃቃ መምራትን መከተል ኤፌ. 5:15, 16
3.ከራስህም ሆነ ከሌሎች በምትጠብቀው ነገር ምክንያታዊ ሁን።—ፊልጵ. 4:5
https://t.me/Yoangeliwon