Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ሶስት ለደስታችን ምክንያት የሆኑ ነገሮች ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ዝምድና የበለጠ ለደስታችን | ዩአንገሊዎን

ክፍል ሶስት
ለደስታችን ምክንያት የሆኑ ነገሮች
ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ዝምድና የበለጠ ለደስታችን ምክንያት የሚሆን ምን ሊኖር ይችላል? እስቲ አስበው፦ የአጽናፈ ዓለሙን ሉዓላዊ ጌታ እናውቃለን። እሱ አባታችን፣ አምላካችንና ወዳጃችን ነው!—መዝ. 71:17, 18
ሕይወታችን እግዚአብሔር ያገኘነው ስጦታ ነው፤ በተጨማሪም እግዚአብሔር በሕይወታችን መደሰት እንድንችል አድርጎ ፈጥሮናል። (መክ. 3:12, 13) እግዚአብሔር ወደ ራሱ ስለሳበን አምላክ ለእኛ ያለውን ፈቃድ አውቀናል፤ እንዲሁም ሕይወታችንን እንዴት መምራት እንዳለብን ተገንዝበናል። (ቆላ. 1:9, 10) በመሆኑም ሕይወታችን እውነተኛ ትርጉም ያለው መሆን ችሏል። በሌላ በኩል ግን አብዛኛው የሰው ዘር ስለ ሕይወት ዓላማ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ የለውም። ጳውሎስ ይህን ልዩነት ጎላ አድርጎ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “‘አምላክ ለሚወዱት ያዘጋጃቸውን ነገሮች ዓይን አላየም፣ ጆሮም አልሰማም፣ የሰውም ልብ አላሰበም።’ . . . አምላክ እነዚህን ነገሮች በመንፈሱ አማካኝነት የገለጠው ለእኛ ነውና።” (1 ቆሮ. 2:9, 10) በእርግጥም የእግዚአብሔርን ፈቃድና ዓላማ ማወቃችን የሚያስደስት አይደለም?
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያደረገውን ሌላም ነገር እንመልከት። ኃጢአታችን ይቅር ሊባልልን በመቻሉ ደስተኞች አይደለንም? (1 ዮሐ. 2:12) አምላክ መሐሪ በመሆኑ በቅርቡ አዲስ ዓለም እንደሚመጣ እርግጠኛ የሆነ ተስፋ ሊኖረን ችሏል። (ሮም 12:12) በአሁኑ ጊዜም እንኳ እግዚአብሔር ፣ ጥሩ የእምነት አጋሮች ሰጥቶናል። (መዝ. 133:1) ከዚህም ሌላ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከሰይጣንና ከአጋንንቱ እንደሚጠብቅ ሕያው ቃል ዋስትና ይሰጠናል። (መዝ. 91:11) ከአግዚአብሔር ባገኘናቸው በእነዚህ ሁሉ በረከቶች ላይ የምናሰላስል ከሆነ ደስታችን እየጨመረ ይሄዳል።—ፊልጵ. 4:4
ይበልጥ ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ ትችላለህ?
በሕይወቱ ደስተኛ የሆነ ክርስቲያን የበለጠ ደስታ ማግኘት ይችላል? ኢየሱስ “እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ እኔ ያገኘሁትን ደስታ እንድታገኙና የእናንተም ደስታ የተሟላ እንዲሆን ነው” ብሏል። (ዮሐ. 15:11) ይህ አባባል ደስታችን እንዲጨምር ማድረግ እንደምንችል የሚጠቁም አይደለም? ደስታችን እንዲጨምር ማድረግ፣ እሳትን ይበልጥ ለማቀጣጠል ማገዶ ከመጨመር ጋር ሊመሳሰል ይችላል። እሳቱ ይበልጥ እንዲቀጣጠል እንጨት መማገድ አለብህ። በተመሳሳይም ደስታህ እንዲጨምር መንፈሳዊነትህን ማሳደግ አለብህ። መንፈስ ቅዱስ፣ ደስታ ለማግኘት እንደሚረዳ አስታውስ። በመሆኑም የእግዚአብሔርን መንፈስ እርዳታ ለማግኘት አዘውትረህ በመጸለይና በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃሉ ላይ በማሰላሰል ደስታህ እንዲጨምር ማድረግ ትችላለህ።—መዝ. 1:1, 2፤ ሉቃስ 11:13
ከዚህም ሌላ እግዚአብሔርን በሚያስደስቱ ሥራዎች በትጋት በመካፈል ደስታህ እንዲጨምር ማድረግ ትችላለህ። (መዝ. 35:27፤ 112:1) እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም የተፈጠርነው ‘እውነተኛውን አምላክ እንድንፈራና ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ’ ነው፤ “ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነው።” (መክ. 12:13) በሌላ አባባል የተፈጠርነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናደርግ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ስናገለግል በሕይወታችን ከሁሉ የላቀ ደስታ እንደምናገኝ የተረጋገጠ ነው።
https://t.me/Yoangeliwon